Harari Finance & Economic Cooperation Bureau

Harari Finance & Economic Cooperation Bureau

Share

Government organization

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 11/05/2026

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

ግንባት 3/2018

* * * *


የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በጄኔላ በሶፊ፣ በአሚር ኑርና በአቦከር ወረዳዎች ከሚገኙ የማብረተሰብ ተወካዮች፥ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አመራሮችና ጋር በማኅበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ የገፅ-ለገፅ የወይይት መድረክ አካሄደ።


በውይይቶቹ ላይ በጤና፣ በትምህርት፣ በመንገድ እና በውሃ አገልግሎት ዙሪያ የተለዩ ችግሮች ተነስተው የተወያዩ ሲሆን፥ በመድረኩም የተገኙት የሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ከወረዳና ከቀበሌ የማህበራዊ ተጠያቂነት መድረክ ሰብሳቢዎችና ፀሃፊዎች፣ ከማህበረሰብ ተወካዮች እና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር ገንቢ ውይይት ተካሂዷል።


የመድረኩ ዋና ዓላማ ማህበረሰቡን በውሳኔ ሂደት ውስጥ በንቃት ማሳተፍ፣ በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ማጠናከር፣ እንዲሁም ተቋማትና ማህበረሰቡ በጋራ ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው።


በቀጣይም በውይይቶቹ የተለዩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ችግሮች በጋራ የተግባር እቅድ (Joint Action Plan) ውስጥ ተካተው እንዲፈፀሙ ክትትልና ግምገማ ይካሄዳል።

በተጨማሪም ከህብረተሰቡ ጋር ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በማካሄድ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የህዝብ እምነትን ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል።


Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 07/05/2026

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

ሚያዝያ 29/2018

* * * *

የማህበራዊ ተጠያቂነት (SA) የመስክ ጉብኝት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ!


በኢትዮጵያ የማህበራዊ ተጠያቂነት (SA) ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ የማህበራዊ ተጠያቂነት አፈጻጸምን ለማጠናከር እና የምክር ቤት አባላት የቁጥጥር ሚናን ለማበረታታት በተዘጋጀ ቼክ ሊስት መሰረት፣ በወረዳ ደረጃ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።


የጉብኝቱ ዋና ትኩረት በወረዳዎችና በስሩ ላሉት ት/ቤቶች የማህበራዊ ተጠያቂነት ስራዎች አፈጻጸምን በተግባር መመልከት፣ ያሉ ችግሮችን መለየት እና ለቀጣይ ማሻሻያ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ላይ ነበር።


🎯 የጉብኝቱ ዋና ዓላማዎች:-

> የSA ተግባራት በወረዳ ደረጃ እንዴት
እየተፈጸሙ እንደሆነ ማረጋገጥ
> የምክር ቤት አባላት የቁጥጥር ሚናን
ማጠናከር
> ችግሮችን መለየት እና ተገቢ መፍትሄዎችን
ማቅረብ

👥 በጉብኝቱ የተሳተፉ አካላት

የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢና የማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ እንዲሁም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ናቸው ።


ጉብኝቱም የተካሄደው የመስክ ጉብኝት የማህበራዊ ተጠያቂነት ስርዓትን ለማጠናከር፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማሳደግ እንዲሁም የህዝብ ተሳትፎን ለማበረታታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በመግለፅ በቀጣይም ሩብ አመት ጉብኝቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሰታቀውቀዋል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Government communication affairs Office's post 03/05/2026
29/04/2026

*[በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መቆራረጥ ጉዳዩ እስኪሰክን ዜጎች ምን ማድረግ ይችላሉ?]*

- ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን በመለየት፣ ሁኔታውን መረዳትና መንግስት ከጎናችሁ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።
- ከሀሰተኛ ወሬዎች እና ከተሳሳቱ መረጃዎች ራስዎን ይጠብቁ
- አጋጣሚውን በመጠቀም ለማትረፍ የሚሞክሩትን ያጋልጡ
- አሁን ያለውን የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብ በትዕግስት እና በጥንካሬ ለማለፍ ይሞክሩ
- አላስፈላጊ ጉዞዎችን በመቀነስ ነዳጅንና ሌሎች ውስን ሀብቶችን በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

ምንም እንኳን ትልልቅ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ አቅርቦት እንዳይቋረጥና ዜጎችን ከእንግልት ለመከላከል አተኩሮ እየሰራ ነው።

በትብብር እና በትዕግስት ይህንን አስቸጋሪና ተለዋዋጭ የዓለም አቀፍ ሁኔታ፤ በጋራ ማለፍ እንችላለን!

🇪🇹

29/04/2026

ስለ ነዳጅ ይህን ያውቁ ኖሯል?
******

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ዝቅተኛ የነዳጅ ዋጋ ካላቸው ሀገራት አንዷ ነች።

- አንድ ሊትር ናፍጣ ኢትዮጵያ ውስጥ 1 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው
- አንድ ሊትር ቤንዚን ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ 0.90 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው

በአንጻሩ በአጎራባች ሀገራት የሁለቱም የነዳጅ ዓይነቶች አማካይ ዋጋ 1.50 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው።

ሀገራችን ሙሉ በሙሉ (100%) የነዳጅ ፍላጎቷን በገቢ ምርት የምታሟላ ሲሆን፣ በዋነኛነት የምታስገባበት ምንጮቿም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው።

*[ኢትዮጵያ ነዳጅ በዝቅተኛ ዋጋ የምታቀርበው ለምንድነው?]*

መልሱ የመንግስት ድጎማ ነው።

ኢትዮጵያ ወደ 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ሀገር ናት። ዜጎችን ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ለመጠበቅ መንግስት የነዳጅ ወጪን ከፍተኛውን ክፍል ይሸፍናል።

1. መንግስት በአሁኑ ወቅት መደበኛ ከሚደጉመው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር በየወሩ ለነዳጅ ድጎማ እያደረገ ይገኛል፤
2. ይህም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅትም በሀገር ውስጥ ያለው ዋጋ እንዳይንር ለማድረግ የተወሰነ ውሳኔ ነው።

*[በመካከለኛው ምስራቅ ምን እየተከናወነ ነው]?*

ወደ 20% የሚጠጋው የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የሆርሙዝ ሰርጥ ተብሎ በሚጠራው ወሳኝ የባህር መስመር በኩል ያልፋል። ይህ መስመር ለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ሀገሪቱ የምታስገባው ነዳጅ እና የናፍጣ ጭነት በዚህ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ነው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከማርች 2 ቀን 2026 ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ግጭት ምክንያት፦

- የሆርሙዝ ሰርጥ ለንግድ መርከቦች ዝግ ሆኖ ቆይቷል፤
- በዚህም ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ታዝዞ ሊመጣ የነበረ ከ180,000 ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ዘግይቷል፤
- አብዛኛዎቹ አቅራቢዎችም በቀውሱ ምክንያት ነዳጅ ማቅረብ አቁመዋል፤ የነዳጅ ማጣሪያዎችም ስለተጎዱ አቅርቦት ቀንሷል።

*[የኢትዮጵያ መንግሥት ምን አይነት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል?]*

1. የትራንስፖርት፣ የግብርና እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስራ ለማስቀጠል የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከተነሳበት ወቅት ጀምሮ በቀን 4.5 ሚሊዮን ሊትር ገደማ ናፍጣ ሲያቀርብ ቆይቷል።

2. የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም ዝግ ሆኖ ባለበት ወቅት፣ ዜጎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ እና ምርታማነት እንዳይጓደል፣ በዛሬው ዕለትም የናፍጣ አቅርቦት ከቅድመ ጦርነት ወደ ነበረው የአቅርቦት መጠን 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ ተወስኗል።

3. የሀገራችንን እና የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት ነዳጅን በከፍተኛ የዓለም ገበያ ዋጋ ከተለያዩ አማራጭ አቅራቢዎች እየገዛ ነው።

4. ነዳጅን አስቀድሞ ከተያዙ ጭነቶች ከመጠበቅ ይልቅ፣ ፈጣን አቅርቦት ለማግኘት በዕለቱ የገበያ ዋጋ ወዲያውኑ የመግዛት ስልትን (spot purchasing) እየተጠቀመ ነው።

5. ከመደበኛው ዋጋ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን በመሸፈን የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ቀጥሏል።

6. ምንም እንኳን መዘግየቶች እና ረጅም ሰልፎች ቢኖሩም፣ ሌሎች ሀገራት ማደያዎችን እየዘጉ እንዲሁም የነዳጅ ቁጠባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እያወጁ ባሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ነዳጅ አሁንም ባጠቃላይ ወደ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ማደያዎች እንዲቀርብ እያደረገ ይገኛል።

ናፍጣ በሀገሪቱ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል የነዳጅ ዓይነት በመሆኑ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምክንያት ለእጥረት የተጋለጠ ሲሆን፤ የቤንዚን አቅርቦት ግን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል።

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 15/04/2026

የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

መጋቢት 28/2018

የሀረሪ ክልል የመንግስት ንብረት አስተዳደርን በዲጂታል ዘዴ ሊያዘምን ነው።

የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ንብረቶችን በዘመናዊ የዲጂታል ስርዓት ለመምራት የሚያስችል የሶፍትዌር ትግበራ መጀመሩን አስታውቋል።

ይህንን አዲስ አሰራር በክልል ደረጃ በይፋ ለማስጀመር እንዲቻልም ለከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ለማኔጅመንት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ይህ ንቅናቄ የመንግስትን የሀብት አያያዝ ከባህላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር የታለመ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህንን የዲጂታል የንብረት አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ቢሮው ከአፍሮኔክስ ቴክ ሀብ (Afronex Tech Hub) ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።

እንደ እቅዱ ከሆነ በመጀመሪያው ምዕራፍ 15 ተመረጡ የመንግስት ተቋማት የሶፍትዌሩ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመት ደግሞ ሶፍትዌሩን ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማስማማት (Customization) ስራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ያህያ አብዱረሂም ገልጸዋል።

የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የዲጂታል አሰራሩ የክልሉን የንብረት አያያዝ ወደ ላቀ ዘመናዊነት የሚያሸጋግርና ግልጽነትን የሚፈጥር ነው።

ኃላፊው አክለውም በበጀት ዓመቱ የተቀመጡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው፣ በተመረጡት ተቋማት ውስጥ ስርዓቱ ሳይዘገይ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ስርዓት ተግባራዊ መሆኑ በመንግስት ንብረት ላይ የሚታዩ የአያያዝ ጉድለቶችንና አላስፈላጊ ብክነቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ይረዳልም ተብለዋል።

በተጨማሪም በንብረት አስተዳደር ዙሪያ ተጠያቂነትን በማስፈን የክልሉን ውስን ሀብት በአግባቡ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 07/04/2026

የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

መጋቢት 29/2018

* * * * *

የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ከጅኔላ ወረዳ አሰተዳደር ጋራ ውይይት ተካሄደ!

በኢትዮጲያ መንግስትና በዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር የተደረገው ስምምነትና የገንዘብ ድጋፍ መሠረት የማህበራዊ ተጠያቂነት (SA) ፕሮግራም በስፋት እየተተገበረ ሲሆን ዓላማው የመንግስት አገልግሎቶችን ግልፅነትና ተጠያቂነት በህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር ነው።


በመሆኑም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራም የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት በሚካሄደው ስራ በዛሬው እለት በመደረኩ በመጀመሪያ ላይ ስለ ማህበራዊ ተጠያቂነት ምንነት፣ አላማ፣ አመጣጥ እና በፕሮግራሙ ላይ ምን፣ መቼና እንዴት እንደሚሰራ በቻናል አንድ አስተባባሪ አቶ ኑረዲን መሐመድ በአጭርና በግልፅ ቀርቧል።


በዚህ መሠረት በጅኔላ ወረዳ ቀበሌ 14 ውስጥ የውሃ ፍሳሽ መውረጃ (drainage) ቱቦ በተገቢ አቀራረብ አልተገነባም በመሆኑ ውሃ ወደ ነዋሪዎች ቤቶች እየገባ የጤና አደጋና የንብረት ጉዳት እያመጣ መሆኑ ተገልጿል።


ችግሩን ለመፍታት በመጋቢት 29/2018 ዓ.ም ከህብረተሰቡና ከተያያዥ አካላት ጋር የጋራ ውይይት ተካሂዶ ችግሩ በግልፅ ቀርቦ ማህበረተሰቡና የሚመለከታቸው የአገልግሎት ሰጪ አከላት አስተያየታቸውን ሰጥተው ችግሩን በባለቤትነት መውሰድ ያለበት የጅኔላ ወረዳ ሲሆን ይንንም ለማሰፈፀም ሰምምነት ላይ በመድረስና የሚሰሩትን ስራዎች በቀጣይ የጋራ እቅድ እንደሚዘጋጅ ተወስነዋል።


👉 ማህበራዊ ተጠያቂነት የህብረተሰብ ድምፅን የሚያጠናክር እና የተግባር ለውጥ የሚያመጣ ቁልፍ መንገድ ነው።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 06/04/2026

የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድጋፍ አድርገውል።

መጋቢት 28/2018

* * * * * *

የሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድጋፍ አድርገውል።

በሀረሪ ክልል ከመጋቢት 2010 ጀምሮ በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በለውጡ የተገኙ ድሎችና ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ እውቅና የሚሰጥ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ::

በክልላችን ደረጃ ያለፉት የለውጥ ዓመታት ጠንካራ የአመራር ውህደት የፈጠርንባቸው፣ ከፍተኛ መነሳሳትና ቁርጠኝነት የታየባቸው፣ የመላው ህዝባችን ንቁ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያረጋገጥንባቸው፣ የመንግስትና የህዝብ ግንኙነት ያጠናከርንባቸው ናቸው።

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከክልሉ ከተማና ገጠር የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 24/03/2026

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

መጋቢት 15/2018

* * * * *

የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ስልጠና ተካሄደ::


በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በቻናል አንድ ፕሮግራም ስር የሚከናወነው የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት በሶፊ ወረዳ አው-ዑመር ቀበሌ ለተመረጡ የትኩረት ቡድኖች ስልጠና ተሰጥቷል።


ስልጠናው “የማህበረሰብ አገልግሎት መመዘኛ ካርድ” (Community Score Card) ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ በሚያገኙት አገልግሎቶች ላይ በስምምነት ነጥብ በመስጠት የሚገምግም አሰራር መሆኑ ተገልጿል።


ይህ መሳሪያ ዜጎችን፦
✔️ የአገልግሎቶችን ጥራት
✔️ ተደራሽነት
✔️ አጥጋቢነት
✔️ ውጤታማነት


በተግባር እንዲገምግሙና እንዲፈትሹ የሚያስችል ሲሆን፣ በመንግስትና በማህበረሰብ መካከል ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትን እና ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል።


በመጨረሻም ተሳታፊዎች በወሰዱት ስልጠና መሰረት የጤናና የትምህርት ዘርፎችን የሚገመግሙ ቡድኖችን በመለየት፣ በተዘጋጀው የግምገማ ፎርማት መሰረት በቡድን ውይይት በማካሄድ የተቀናጀ ውጤት እንዲያቀርቡ በተግባር ልምምድ አድርገዋል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 21/03/2026

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

መጋቢት 12/2018

* * * * *

የ2018 በጀት አመት በቻናል አንድ ፕሮግራም ስር የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት በጅኔላ ወረዳ ቀበሌ 16 የትኩረት ቡድን የማህበረተሰብ ውይይትና የጋራ ግምገማ የማህበራዊ ተጠያቂነት የአተገባበር ኡደት የሆነውን የማህበረተሰብ መመዘኛ ካርድ አማካኝነት ግምገማው ተካሄደዋል።


በዚህ ግምገማ የጤና፣ የትምህርት፣ የውሃና ፍሳሽ እንዲሁም የመንገድ ዘርፎች የግምገማው ዘርፍ ሲሆኑ የወጣቶች፣ የሴቶችና የተጋላጭ ቡድኖች የተቀናጅ ውጤት በመቅረብ የህብረተሰቡ አስተያየትና ችግሮች በተግባር ተዳምጠዋል።

በተመሳሳይ ቀን የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የራስ በራስ ግምገማ (self-assessment) አካሂደዋል።


በመድረኩ የክልሉ ም/ቤት የማህበራዊና የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢዎች፣ በገንዘብና ኢኮኖሚና ትብብር ቢሮ የቻናል አንድ አሰተባባሪና የማህበራዊ ተጠያቂነት ተጠሪ፥ የጄኔላ ወረዳና የቀበሌ 16 የማህበራዊ ተጠያቂነት መድረክ አባላቶች በቦታው በመገኘት ሂደቱን ተከታትለው የህብረተሰብ ጉዳዮችን በቅርብ ያዳመጡ ሲሆን በማንኛውም ጊዜ በተነሱት ችግሮች ሂደቱን በመከትል ድጋፍ እንደሚያደረጉ ግልፀዋል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Photos from Harari Finance & Economic Cooperation Bureau's post 19/03/2026

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

መጋቢት 10/2018 ዓ.ም

* * * *

የሀረሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለወረዳዎች የፕሪንተር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

አሰራርን ለማዘመን ለወረዳዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ::

የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በክልሉ ለሚገኙ አራት ወረዳዎች የፕሪንተር ድጋፍ አደረገ።

ቢሮው የCALM ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑት ለሸንኮር፣ ሐኪም፣ ኤረር እና ሶፊ ወረዳዎች ነው ይህንን ድጋፍ ያበረከተው።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ያህያ አብዱረሂም ተገኝተው ቁሳቁሱን ለወረዳዎቹ የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

የፕሮግራሙ አስተባባሪ እንደገለጹት ቢሮው የወረዳዎችን የአሰራር አቅም ለማሳደግና አገልግሎትን ለማዘመን በ2017 ዓ.ም በተመሳሳይ የኮምፒውተር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

የዛሬው የፕሪንተር ርክክብም የዚሁ ተከታታይ የድጋፍ መርሃ-ግብር አካል መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ በፕሮግራሙ ወረዳዎች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ይበልጥ ቀልጣፋ እና ውጤታማ እንደሚያደርገው ታምኖበታል።

Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Jinella
Harar