Harari Management and Kaizen Institute

Call Directions Website Contact the organization

Harari Management and Kaizen Institute Training - Research - Consultancy

10/10/2026
 መስከረም 30 ቀን 2019 ዓም🧠 **በስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ላይ የተሰጠው ሥልጠና ተጠናቀቀ!**የሀረሪ ስራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት ከክልሉ ፖሊስ ኮ...
10/10/2026


መስከረም 30 ቀን 2019 ዓም
🧠 **በስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ላይ የተሰጠው ሥልጠና ተጠናቀቀ!**

የሀረሪ ስራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለትራፊክ ፖሊስ አመሪሮችና አባላት በስሜታዊ ብልህነት ላይ ከመስከረም 28/2019 ዓም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ::

ሥልጠናውን በይፋ የዘጉት የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ኃላፊ ኮማንደር ሙኽታር አብዶሽ ሲሆኑ፣ ሰልጣኞች በሥልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ሥራ ሲመለሱ በተግባር እንዲያውሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም ለሥልጠናው ስኬታማ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና አስተባባሪዎች ከራሳቸውና ከኮሚሽኑ ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

**ስሜታዊ ብልህነት ለሙያዊ ብቃት፣ ለተሻለ የሕዝብ አገልግሎትና ለጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር!**

#ስሜታዊብልህነት #ትራፊክፖሊስ #የሐረሪክልልፖሊስኮሚሽን #አቅምግንባታ #ሙያዊብቃት

ወቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:

በዌብሳይት: Blog
https://www.hmkimedia.blogspot.com/

በYoutube ቻነላችን
https://youtube.com/

በቴሌግራም:
https://t.me/c/1260317423/383

በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute

በፌስቡክ ገፃችን:
https://www.facebook.com/hararimki

በትዊተር፣
https://twitter.com/hararimki?t=j8vGvcUAHxwcw1Sjba3JMA&s=09

ተቀላቀሉን!!!

 መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ምለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ዙሪያ የ2ኛ ቀን ስልጠና ተካሄደ።የሥራ አመራርና ካይዘን ኢን...
09/10/2026



መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም

ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ዙሪያ የ2ኛ ቀን ስልጠና ተካሄደ።

የሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት እየሰጠ ባለው የ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ስልጠና ፕሮግራም የሁለተኛ ቀን ስልጠና ተካሂዷል።

ስልጠናው የትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በየዕለት የሥራ አጋጣሚዎች ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን የስሜት ጫናዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ፣ የራሳቸውንና የሌሎችን ስሜት እንዲረዱ እንዲሁም በአስቸጋሪ የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ በሙያዊ ሥነ-ምግባርና በተገቢ የመግባባት ክህሎት ምላሽ እንዲሰጡ አቅማቸውን ለማጎልበት ያለመ ነው።

በስልጠናው አፅንዖት የተሰጠው ስሜትን በተገቢው መንገድ መቆጣጠር፣ በጫና እና በአስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ በተረጋጋ መንፈስ ውሳኔ መስጠት፣ አለምግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እና ከሕዝብ ጋር በአክብሮት፣ በትዕግሥትና በሙያዊ ኃላፊነት መግባባት ላይ ነው።

በተለይም የትራፊክ ፖሊስ አባላት በየዕለቱ ከተለያዩ የሕዝብ ክፍሎች ጋር በቀጥታ በሚገናኙበት የሥራ ሁኔታ ውስጥ፣ ስሜታዊ ብልህነት የሕዝብ አመኔታን ለማጠናከር፣ የግጭት ሁኔታዎችን ለመቀነስና ውጤታማ፣ ሰው-ተኮር እና ሙያዊ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው ከመስከረም 28–30 ቀን 2019 ዓ.ም. በሦስት ሺፍት ለሦስት ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ ሲሆን፣ የሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) በተቋማት ውስጥ የሰው ኃይል አቅምን በማጎልበት የሥራ አፈፃፀምን፣ የአገልግሎት ጥራትንና ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማሻሻል ያለውን ተልዕኮ እያስቀጠለ ይገኛል።

HMKI — አቅምን መገንባት ለተሻለ አፈፃፀም!

#ስሜታዊብልህነት #የትራፊክፖሊስ #አቅምግንባታ

ወቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:

በዌብሳይት: Blog
https://www.hmkimedia.blogspot.com/

በYoutube ቻነላችን
https://youtube.com/

በቴሌግራም:
https://t.me/c/1260317423/383

በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute

በፌስቡክ ገፃችን:
https://www.facebook.com/hararimki

በትዊተር፣
https://twitter.com/hararimki?t=j8vGvcUAHxwcw1Sjba3JMA&s=09

ተቀላቀሉን!!!

09/10/2026

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመጪው ሰኞ ይከበራል

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመጪው ሰኞ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በድምቀት ይከበራል፡፡

ቀኑ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ሁነቱ ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበርና ክብር ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ነው፡፡

በመሆኑም የዘንድሮው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በምክር ቤቱ አስተባባሪነት በመላ ሀገሪቱ ወቅታዊ ሀገራዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

በዕለቱ ፕሬዚዳንቱ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድና ክብር ዘብ ታጅበው ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ያከናውናሉ፡፡

ይህ በዓል በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚከበር የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡



29/01/19

 መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ምለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረየሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲት...
08/10/2026


መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም

ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

የሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” በሚል ርዕስ ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናው የትራፊክ ፖሊስ አባላትና አመራሮችን በሶስት ሺፍት በመከፋፈል፣ ከመስከረም 28–30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ የትራፊክ ፖሊስ አባላትና አመራሮች የራሳቸውን ስሜት በመረዳትና በመቆጣጠር፣ የሌሎችን ስሜት በመረዳት እና በተገቢ ሙያዊ መንገድ ምላሽ በመስጠት ውጤታማ፣ ሰው-ተኮር እና ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ አቅም ማጎልበት ነው።

ስሜታዊ ብልህነት በተለይ አስጨናቂና በአስቸጋሪ የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ ራስን መቆጣጠር፣ ግጭትን በአግባቡ መፍታት፣ ከሕዝብ ጋር በአክብሮት መግባባት እና በሙያዊ ሥነ-ምግባር ሥራን ማከናወን ላይ ወሳኝ ሚና አለው።

HMKI — አቅምን መገንባት ለተሻለ አፈፃፀም!

#ስሜታዊብልህነት #የትራፊክፖሊስ #አቅምግንባታ

ወቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:

በዌብሳይት: Blog
https://www.hmkimedia.blogspot.com/

በYoutube ቻነላችን
https://youtube.com/

በቴሌግራም:
https://t.me/c/1260317423/383

በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute

በፌስቡክ ገፃችን:
https://www.facebook.com/hararimki

በትዊተር፣
https://twitter.com/hararimki?t=j8vGvcUAHxwcw1Sjba3JMA&s=09

ተቀላቀሉን!!!

 መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም“የመንግስት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ” ሥልጠና ተጠናቀቀ።የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክ...
01/10/2026


መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም
“የመንግስት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ” ሥልጠና ተጠናቀቀ።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር “የመንግስት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ” በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
ሥልጠናው ከመስከረም 19–21 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሦስት ተከታታይ ቀናት በመካሄድ፣ በሥራ ላይ የሚጠበቅ ሥነ-ምግባር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የተገልጋይ አያያዝ፣ የሙያ ኃላፊነት እና በተግባር ሊያጋጥሙ በሚችሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች ተካሂደዋል።
በሥልጠናው መዝጊያ ላይ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አሻ አሚኔ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሥልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት በከፍተኛ ተሳትፎና በትጋት መካሄዱን ገልጸው፣ በሥልጠናው ወቅት የተካሄዱ ውይይቶች፣ የተነሱ ተጨባጭ ተግዳሮቶች እና የቀረቡ አዳዲስ ሀሳቦች ፍርድ ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ በግልጽ ለመረዳት እንዳስቻሉ ጠቁመዋል።
እንዲሁም ሠልጣኞች በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር በየሥራ ክፍላቸው የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።
“በማንኛውም ሥልጠና ዋጋ የሚኖረው በክፍል ውስጥ ሲቀሰም ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለውጥ ማምጣት ሲችል ነው።” በማለት ያስገነዘቡት ክብርት ወ/ሮ አሻ፣ ሠራተኞቹ ወደ የሥራ ክፍሎቻቸው ሲመለሱ በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም ለተገልጋዮች የሚያሳዩት መልካም ሥነ-ምግባርና የሚሰጡት ቀልጣፋ አገልግሎት የሥልጠናው ፍሬ ማፍራቱን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ “ተገልጋዮቻችንን በአክብሮትና በቅንነት ማስተናገድ ግዴታችን ብቻ ሳይሆን፣ የሕዝብን አመኔታ የምናተርፍበት ዋነኛ መሣሪያችን ነው” በማለት አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም፣ ይህ ሥልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አሰልጣኞች፣ ለሥልጠናው አስተባባሪዎች እና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ከመስከረም 19–21 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው “የመንግስት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ” ሥልጠና በዚህ መልኩ በስኬት ፍጻሜ አግኝቷል።

  መስከረም 20 ቀን 2019 ዓም የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሥልጠና እየተሰጠ ነው::ስልጠናው እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ...
30/09/2026

መስከረም 20 ቀን 2019 ዓም
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሥልጠና እየተሰጠ ነው::

ስልጠናው እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።



ወቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:
በዌብሳይት: Blog
https://www.hmkimedia.blogspot.com/
በYoutube ቻነላችን
https://youtube.com/
በቴሌግራም:
https://t.me/c/1260317423/383
በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute
በፌስቡክ ገፃችን:
https://www.facebook.com/hararimki
በትዊተር፣
https://twitter.com/hararimki?t=j8vGvcUAHxwcw1Sjba3JMA&s=09
ተቀላቀሉን!!!

29/09/2026

Address

Total � EH Kombolch Road
Harar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30

Telephone

+251256665670

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Management and Kaizen Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Management and Kaizen Institute:

Shortcuts

Share