26/05/2026
🌙✨ እንኳን ለ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✨🌙
=============//===============
የሀረሪ ክልል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የሰላም፣ የደስታ እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
ኢድ ሙባረክ! 🌙✨
14/05/2026
ኮሚሽኑ በመልካም አስተዳደር እና አዲሱ የሲቭል ሰርቪስ ፖሊሲ ላይ ስልጠና ሰጠ።
**
ግንቦት 06/2016 ዓ.ም
ሀረር
የሀረሪ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዲሱ ሰቭል ሰርቪስ የሰራተኞች ፖሊሲ ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናውም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አዳል ሙላቱ ተገኝተው በአዲሱ ፓሊሲ ስልጠና መዘጋጀቱ ሁሉም ሰራተኛ መብቱን እና ግዴታውን አውቆ በመስራት የሚሰራውን ስራ ተግባር ውጤት ተኮር አድርጎ እንዲሰራ ያነቃቃል ብሏል።
የግንዛቤ ስልጠናውን ሰነድ ወ/ሮ አይሻ አብደላ የኮሚሽኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የስልጠናውን ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም ስለጠናዉ መሰጠቱ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ተሳታፊዎች በስነምግባር አገልግሎትን በመስጠት ሚናቸዉን እነደሚወጡ ገልፀው ፖሊስው መውጣቱም ጥሩ መሆኑን ገልጿል።
13/05/2026
ኮሚሽኑ በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ያለው የተማሪዎች ስነ ምግባር ግንባታ ግንዛቤ መፍጠሪያ እንደ ቀጠለ ነው።
ግንቦት 05/2018
ሀረር
ዛሬም በአባድር ወረዳ በሚገኘው አውመጀዲን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኮሚሽኑ የአውተር ክፍል ባለሙያዎች በመገኘት ለተማሪዎች በስነ ምግባር ግንባታ; ሙስና ዙሪያ እና ኩረጃን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄዷል።
በግንዛቤውም ተማሪዎች ሊያጎለብቱ የሚገባው ስነ ምግባር እንዲሁም ኩረጃን እና ሙስናን ተፀይፎ በማደግ ለሀገርቷ ተረካቢ ተስፋ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑና በቀጣይም ወደ ሌላ ት/ቤቶች የሚቀጥል መሆኑ ነው።
12/05/2026
የታዳጊ እና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በስነ ምግባር መገንባት የሁሉም ግዴታ ነው ተባለ።
ግንቦት,04/2018
ሐረር
የሐረሪ ክልል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን በክልሉ በመንፈሳዊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሥነ ምግባር ግንባታ እና ኩረጃ መፀየፍ ዙሪያ ግንዛቤ እየሰጠ ።
በግንዛቤው መድረክም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አዳል ሙላቱ ተገኝተው የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በስነ ምግባር የመገንባት የሁሉም ሀላፊነት እንደሆነ በመግለፅ ይህንን በመገንዘብ ሁሉም የራሱን ሚና ልወጣ እንደሚገባ ተናግሯል።
ሀላፊነቱን የሚወጣ እና ኩረጃን የሚፀየፍ ትውልድ ለማፍራት ከመሰረቱ መሠራት እንዳለበትእንዲሁም በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ሂደት ላይ በየት/ቤቱ የሚገኙ ክበባት የፓርላማ አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገለፁ።
በተጨማሪም ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው ዛሬ ራሳቸውን በስነምግባር አንፀው ሀገራቸውን ብሎም አፍሪካን ያስጠራሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልፀዋል።
በመድረኩም የተገኙ ባለድርሻ አካላትም ከክልሉ ዐ'ህግ ቢሮ ባለሙያ:ከት/ርት ቢሮ ባለሙያ እና የትምህርት ዘርፋ ስሆን የኮሚሽኑ የህብረተስብ ተሳትፎ እና ግንዛቤ ማሳደግ ዳ/ሬት አቶ አባስ አብደላ የተዘጋጀውን ሰነድ ለተማሪዎች በማቅረብ ግንዛቤ ሰጥቷል ::
ተማሪዎች የአገሪቱን የወደፊት ትውልድ በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና ጠንካራ መሆኑንም በመግለፅ የግንዛቤ መድረኩን አጠናቋል ።
08/05/2026
ሙስናን የሚጠየፍ እና ሙያው በሚፈቅደው ስነ ምግባር ህዝቡን የሚያገለግል ጤና ባለሙያና ጤና ተቋማት ለፀረ ሙስና ትግሉ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
ሚያዚያ 30/2018
ሀረር
የሀረሪ ክልል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ለሚገኘው ጀጉላ ሆስፒታል አመራሮችና ሰራተኞችና በጤና ዘርፍ ሙስና መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የጤናው ዘርፍ በየደረጃው ያሉ ችግሮችን በማረምና ምላሽ በመስጠት ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን መታገልና መግታት እንደሚገባና ይህንንም ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች እና ጤና ተቋማት ሚና የጎላ እንደሆነ በስልጠናው ተገልጿል።
በመጨረሻም በጤናው ዘርፍ ለሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችና ሙስናን ለመከላከል እና ችግሮችን ለመፍታት ሚና እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ገልጿል።