Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Call Directions Website

Harari Regional State Innovation and Technology Agency This is official page of Harari Regional State Innovation and Technology Agency

24/09/2026
የ50 ዓመታት የፈጠራ ጉዞ በአንድ ታላቅ ሀገራዊ መድረክ!                                                                                    ...
24/09/2026

የ50 ዓመታት የፈጠራ ጉዞ በአንድ ታላቅ ሀገራዊ መድረክ!
የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የ50 ዓመታት ታሪክ፣ የላቀ የ5 ዓመታት ሀገራዊ ስኬቶች እና የነገው 50 ዓመታት ራዕይ በSTRIDE 2.0!
STRIDE 2.0 የተሰራውን የሚያከብርበት፣ የተቀየረውን የሚያቀርብበት እና የወደፊቱን የቴክኖሎጂ አቅጣጫ የሚያሳይ ታላቅ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ነው።
በመድረኩ የሚጠበቁ አበይት ሁነቶች፦ ✓ታሪካዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽኖች ✓የባለሙያዎች ውይይትና ፓናሎች ✓አዳዲስ የቴክኖሎጂ ጅምሮችና የፈጠራ ማሳያዎች

https://stride.systemelement.net/
ቀን፦ መስከረም 19 - 21 ቀን 2019 ዓ.ም. (Sept 29 – Oct 1, 2026) ቦታ፦ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም፣ አዲስ አበባ
አሁኑኑ ይመዝገቡ፤ የነገዋን ኢትዮጵያ በጋራ እንቅረፅ!

Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia

24/09/2026
24/09/2026
የሰው ሰራሽ አስተውሎት እያስመዘገበ ባለው አስደናቂ እምርታ የጤናው ዘርፍ ከምንጊዜውም በላይ በታካሚ ላይ ያተኮረ እና ይበልጥ ቀልጣፋ ለውጥ እያስተናገደ ይገኛል። 6 የጤና ፈጠራዎች፤ በሽታዎ...
23/09/2026

የሰው ሰራሽ አስተውሎት እያስመዘገበ ባለው አስደናቂ እምርታ የጤናው ዘርፍ ከምንጊዜውም በላይ በታካሚ ላይ ያተኮረ እና ይበልጥ ቀልጣፋ ለውጥ እያስተናገደ ይገኛል።

6 የጤና ፈጠራዎች፤ በሽታዎችን በቅድመ ማስጠንቀቂያ ለመለየት፣ ሕክምናዎችን ለግል የተስማሙ ለማድረግ እና የሕብረ ሕዋሳትን ጥገና በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን የሚያስችሉ የለውጥ ምዕራፎች ናቸው።

23/09/2026

አሊባባ የኤአይ ውድድሩን አፋፍሟል፤ እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር የሚደርስ ሞዴል እያበለጸገ ነው።

የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዕድገቱን ለማፋጠን አዲስ ቺፕ፣ ከፍተኛ አቅም ያለው የኤአይ ሞዴል እና ሰፊ የዳታ ማዕከል መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚረዳ እቅድ ይፋ አድርጓል።

ኩባንያው ከአሁኑ ዋና የኤአይ ሞዴሉ እስከ አራት እጥፍ የሚበልጥ አዲስ ሞዴል እያሰለጠነ ነው። የሞዴሉ መጠን ከ5 እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር ሊደርስ እንደሚችል አስታውቋል። ይህም የኤአይ ሞዴሎች የማሰብ፣ የመተንበይ እና ውስብስብ ሥራዎችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ካለው ዓለም አቀፍ ውድድር ጋር የሚገናኝ እርምጃ ነው።

አሊባባ የኤአይ መሠረተ ልማቱንም በስፋት ለማሳደግ እየሰራ ነው። የአሊባባ ክላውድ ዓለም አቀፍ የዳታ ማዕከላት አቅም ከ20 ጊጋዋት እንዲሻገር አቅዷል። ይህ ኤአይ ከሞዴል ልማት ባሻገር ቺፕ፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ዳታ ማዕከላትን ያካተተ ሙሉ የቴክኖሎጂ ሰንሰለት ለመገንባት የሚደረግ ኢንቨስትመንት መሆኑን ያሳያል።

የኤአይ ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለአሊባባ እንደ ኩባንያ የንግድ ዕድልን ከማስፋት ባሻገር፤ ለክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ለዳታ ማዕከላት፣ ለሴሚኮንዳክተር እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ የገበያ ፍላጎት እየፈጠረ ነው።

23/09/2026
ስትራይድ 2.0 (STRIDE 2.0)===================የኢትዮጵያን የ50 ዓመታት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ጉዞ እና የዲጂታላይዜሽን ስኬቶች የሚያከብር፣ ባለፉት ...
23/09/2026

ስትራይድ 2.0 (STRIDE 2.0)
===================
የኢትዮጵያን የ50 ዓመታት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ጉዞ እና የዲጂታላይዜሽን ስኬቶች የሚያከብር፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ዋና ዋና ብሔራዊ ስኬቶችን የሚቃኝ እንዲሁም ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ አገር አቀፍ ሁነት ነው።

ሁነቱ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. (እንደ ፈረንጀቹ አቆጣጠር ከሴፕቴምበር 29 እስከ ኦክቶበር 1 ቀን 2026) በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ይከናወናል።

ይህ ሁነት የሃሳቦች፣ የእድገት፣ የቴክኖሎጂ እና የመፃኢ እድሎች ማመላከቻና የባለራዕዮች መገናኛ ቦታ ይሆናል።

የ50 ዓመታት ጉዞ እና እድገት፤ የአምስት ዓመት ስኬት፣ ከዛሬ ውጥን የቀጣይ 50 ዓመታት ጉዞ ይጀምራል።
ይምጡ ይጎብኙን።

​መግቢያ በነፃ!

ሁነቱ ለህዝብ ክፍት በሚሆንባቸው ሁለት ቀናት (በመስከረም 20 እና መስከረም 21) በጠቅላላው 750 ነፃ የጎብኚዎች መግቢያ ፈቃዶች (Passes) የተዘጋጁ ሲሆን፣ በየቀኑ 375 ነፃ ፈቃዶች የሚሰጡ ይሆናል።

​ቦታ፦ አዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም
ቀን፦ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 21(ከሴፕቴምበር 29 እስከ ኦክቶበር 1)

አዘጋጅ፦ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
​

Introducing STRIDE 2.0 ==================Ethiopia’s national summit celebrating 50 years of Science, Technology and Inno...
23/09/2026

Introducing STRIDE 2.0
==================
Ethiopia’s national summit celebrating 50 years of Science, Technology and Innovation (STI) and the country’s digitalization journey, while reflecting on five years of major national achievements and looking ahead to the next 50 years. From 29 September to 1 October 2026, the Science Museum in Addis Ababa will become a national meeting point for ideas, progress, technology and the future. 50 Years of Progress. The Next 50 Start Here.

FREE ENTRY!
A total of 750 free visitor passes have been prepared for the two days when the event will be open to the public, with 375 free passes available each day on September 30 and October 1.

Location: Addis Ababa Science Museum
Date: September 29 - October 1
Organizer: Ministry of Innovation and Technology

በሐረሪ ክልል  በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት ገጽታን የቀየሩና ተሞክሮ የሚወሰድበት ተግባራት ተከናውነዋል በሐረሪ ክልል  በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ...
22/09/2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት ገጽታን የቀየሩና ተሞክሮ የሚወሰድበት ተግባራት ተከናውነዋል

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት ገጽታን የቀየሩና ተሞክሮ የሚወሰድበት ተግባራት መከናወኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካላት ተናገሩ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና የኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል የተመራ ልኡክ በሐረሪ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ፣ኢንደስትሪ ልማት እና ሌሎች ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና የኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል እንዳሉት በክልሉ በተለይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን የማስቀረት ስራ በስፋት ስለመከናወኑ ተናግረዋል።

በዚህም ኢንዱስትሪው የሚያመርተው የፖል ምርት ለኮሪደር ልማት ስራ በማዋል ከተማዋን ውብና ማራኪ ማድረጉን በምልከታ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በአንድ ቦታ የተለያዩ አገልግሎት በማግኘት ወጪና ጊዜን ባግባቡ እንዲጠቀሙ እያደረገ ስለመሆኑም መመልከት መቻላቸውን አስረድተዋል።

በአካባቢው የሚገኙ ሃብትንና ጥበብን በመጠቀም የሚገነቡት የገጠር ሞዴል መንደሮች የሚበረታቱና ልምድ ያካፈለ ተግባር ስለመሆኑም ገልጸዋል።

እንደ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል ገለጻ በክልሉ በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት ገጽታን የቀየሩና ተሞክሮ የሚወሰድበት ተግባራት መከናወኑን አክለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናትናኤል ሚሊዮን በበኩላቸው በክልሉ ጥንታዊ እና ታሪካዊ እሴቶች በያዘ መልኩ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ሳቢና ማራኪ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በመሰረተ ልማት ግንበታ፣ በኢንዳስትሪ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚከናወኑት ተግባራት ዓርዓያ ያላቸውና ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

በጉብኝቱ መርሃ ግብር የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እና ሌሎች የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Regional State Innovation and Technology Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share