24/04/2026
ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች። ይህ ጉዞ በተቀናጀ አሰራር ተመስርቶ፣ ከመቀነስ እስከ መቋቋም ድረስ የሚያካትት የልማት እርምጃዎችን በአስተማማኝ መንገድ አቀናጅቷል።
የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር፣ የደን ጭፍጨፋን በመከላከል እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። በተመሳሳይ ጊዜ የውሃ አስተዳደርን ማዘመን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተስማማ ግብርናን በመተግበር በምግብ ዋስትና ላይ የሚታይ ለውጥ አመጥቷል።
በከተማ ልማት ዘርፍ የወንዝ ዳር ልማቶችን ማስፋፋት፣ አረንጓዴና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እና ሞተር-አልባ ትራንስፖርትን ማስፋፋት ከተሞችን ከሥነ-ምህዳር ጋር የማስታረቅ አዲስ አቅጣጫ ፈጥሯል። በሀገር አቀፍ ደረጃም የከርሰ ምድር እና የገፀ ምድር ውሃን ለመስኖ ማዋል፣ ተስማሚ ዝርያዎችን መጠቀም እና የእንስሳት ሀብትን ማበረታታት፤ የሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን እያጠናከረ ይገኛል።
በኢነርጂ ዘርፍ የአረንጓዴ ኃይል ምንጮችን ማስፋፋት ልማትን የሚያነቃቃ ትልቅ ዐቅም ሆኖ ተገንብቷል፤ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ ትራንስፖርት መሠረት እየሆነም ነው።
እነዚህ ሁሉ ጥረቶች:-
LT-LEDS: (የረጅም ጊዜ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ልማት ስትራቴጂ)፣
TYDP: (የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ)፣
NDC: (በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተገበሩ ተሳትፎዎች)፣
NAP: (የሀገር አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ዕቅድ) ያሉ ማዕቀፎች እና የዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በተቀናጀ መልኩ በመተግበራቸው፣ ኢትዮጵያ ለትውልድ የምታሻግረው ዘላቂ እና አረንጓዴ ነገን መሠረት እየጣለች ነው።
ይህ ጉዞ ምላሽ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ብሩህ መፃዒ ጊዜ የሚገነባ አቅጣጫ ነው።
24/04/2026
በየዘርፉ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ
በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
የሐረሪ ክልል መንግሥት የአስፈጻሚ አካል የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።
ርዕሠ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ግምገማው በየዘርፉ የተቀመጡ ዕቅዶችን አፈጻጸም በመፈተሽ ለቀጣይ ተግባራት ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
አፈፃፀሙን ከዕቅዱ አንፃር መፈተሽና ውስንነቶችን ለይቶ በቀሪ ሦስት ወራት መፈጸም ይገባል ብለዋል።
በማኅበራዊና ኢኮኖሚው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ስኬቶችና ተግዳሮቶችን እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መፈተሽ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ቱሪዝም፣ኢንቨስትመንትና ሌሎች ዘርፎች ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱ የሚገኘውን አስተዋጽዖ መመልከት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማጎልበት ሥራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያም የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁ።
የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ከማስወገድ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት መመልከት ይገባልም ብለዋል።
ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
06/04/2026
28/7/2018
የሐረሪ ክልል ፕላንና ልማት ኮሚሽን ሠራተኞች የመጋቢት 24 የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተሳትፏል።
ኢትዮጵያ ከውድቀት ወደ ማንሰራራት፣ ከስጋት ወደ ተስፋ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከቁልቁለት ወደ ክፍታ፣ ከመፈረካከስ አደጋ ወደ ጠንካራ አገረ መንግስት ግንባታ መሸጋገሪያ መሰረት የጣለችበትን አገራዊ ለውጥ ለመደገፍ በሀረሪ ክልል የተካሄደ ትእይተ ህዝብ።
03/04/2026
በሐረሪ ክልል የፕላንና ልማት ኮሚሽን የብልፅግና ህብረት የ3ተኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ አካሄዷል.
በሐረሪ ክልል የፕላንና ልማት ኮሚሽን በቀን 25/07/2018 የብልፅግና ህብረት የ3ተኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ አካሄዷል.
========================
በኮንፈረንሱም በህብረቱ የተሰሩ የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም እና የተለያዩ አጀንዳዎች ለአባላቱ ቀርቦ በቀረበው በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ኮንፈረንስ ተጠናቋል::