Harari Government communication affairs Office

Harari Government communication affairs Office

Share

ይህንን ፔጅ ላይክ በማድረግ ስለ ክልላችን ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ያግኙ።

05/06/2026

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!

‎የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል። በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፥ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆኑን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይሄንን ምርጫ «የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ» ሲል ሰይሞታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ እውቅና ከተሰጣቸው 55 ድርጅቶች 65,299 የታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፥ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።

‎አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይሄንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከእውነታው ፈጽሞ የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሰረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረጋግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣ 65,299 የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎችን ወይም 1,100 ዕውቅና የተሰጣቸውን ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች መጋበዝ ባላስፈለገ ነበር።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ ዜጎች፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ላሠማራቸው ከ350,000 በላይ ኃላፊዎች፣ ሂደቱን ለጠበቁት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ግንባታ መጎልበት እና ለሂደቱ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት ላረጋገጡት የአፍሪካ እና ቀጣናዊ የታዛቢ ቡድኖች ምስጋናቸውን ያቀርባሉ!

‎ስለ ኢትዮጵያ ልማት

‎ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ውሳኔያቸውን ሲያስቀምጡ፣ ሀገራቸውን በፍጹም የዴሞክራሲ ባህል ውስጥ ለማንበር ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባላት ጸጋ ልክ የሚያስፈልጋትን ሁለንተናዊ ልማት በፍጥነት እውን የማድረግ ባህል እንዲቀጥል ሕዝባችን ተናግሯል።
‎ባለፉት ዓመታት የታየው እውነት እንደሚያሳየን የኢፌዴሪ መንግሥት የተስፋ ቃል መንግሥት አልነበረም። ይልቁንም በተጨባጭ የሚታዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ውጤት ተኮር መንግሥት ሲሆን፤ እነዚህም ውጤቶች በግልጽ የሚታዩ ናቸው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን፥ ይሄም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ይሄንን መነቃቃት መሠረት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዕድገቱ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ዘርፎችን በከፍተኛ ደረጃ ያካተተ ሰፊ መሠረት ያለው ቢሆንም፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ኢንዱስትሪው ለዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየመጣ ይገኛል። ይሄም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭማሪና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት ያሳያል።
‎እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ፥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ናቸው። አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ይህም ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ አሳይቷል። የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይሄም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው። ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ጨምሮ፣ ውጫዊ ጫናዎች በነበሩበት ወቅት ነው።

‎የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፥ ይሄም የሀገሪቱን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል። ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንግድ ተቋማትና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል። ይህ ግድብ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተደገፈ፣ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች የተገነባና ቀጣይነት የነበረውን ውጫዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ የተጠናቀቀ ነው። ከሃይድሮ ፓወር ጎን ለጎን፥ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኘውን የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና በአርሲ ዞን የሚገኘውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ በመሳሰሉ ሥራዎች የታዳሽ ኃይል አቅርቦቷን እያሰፋች ሲሆን፥ ይህም የቀጣናዊ ኢነርጂ ትብብርን እያሳደገ የብሔራዊ ኃይል አቅርቦት መረቡን የመቋቋም ዐቅም ያጠናክራል። በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት አንዱ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው ተጀምሯል። እነዚህ ምኞቶች አይደሉም፤ ተጨባጭ ሐቆች ናቸው።

‎ግብርና፣ አምራች ኢንደስትሪና ቴክኖሎጂ

‎በግብርናው ዘርፍ፣ የመንግሥት የምግብ ሉዓላዊነት አጀንዳ ወቅታዊ ለውጦችን ሳይሆን መዋቅራዊ ውጤቶችን እያስገኘ ቀጥሏል። በሶማሌ ክልል የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከአሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተፈረመው አጋርነት የዘመኑ ጉልህ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ማረጋገጫ ነው። ፋብሪካው በዓመት 3 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ሲሆን፥ ይሄም ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ ማዳበሪያ አምራች ሀገራት ተርታ ያሰልፋታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤ “ይህ ፕሮጀክት በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢንዱስትሪ ዕድገትና በኢኮኖሚ ራስን መቻል ላይ የተደረገ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል። አስተማማኝ ባልሆነና ውድ በሆነ የማዳበሪያ አቅርቦት ለረጅም ጊዜ ለተገደቡት ኢትዮጵያውያን አምራቾች የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ ፈጣንና ተጨባጭ ነው።

ከዚህ ምርጫ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ ሲገኙ የታየው ተምሳሌትነት ለቦረና ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ይህ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅበት ስም የሀገርን አንገት ያስደፋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፤ እርሱም ድርቅ ነው። ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዝናብ መጥፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን የገደለ፣ ቤተሰቦች ለውኃ ፍለጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን እንዲጓዙ ያስገደደ፣ እንዲሁም በእነዚህ የግጦሽ መሬቶች ላይ ለዘመናት ራሳቸውን ችለው የኖሩ ማኅበረሰቦችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እጅ እንዲዘረጉ አድርጎ ነበር። ዓለም የሚያውቃት ቦረና እርሷ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንቦት ወር ጉብኝት ግን የተለየ ታሪክ አሳይቷል። አሁን ላይ ለአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችና ለከብቶቻቸው ንጹሕ ውኃ እያቀረቡ ያሉትን የውኃና የመስኖ መሠረተ ልማቶችን የገመገሙ ሲሆን፥ ከጥቂት ዓመታት በፊት አቧራ ብቻ በነበረው መሬት ላይ የክላስተር እርሻዎችን ጎብኝተዋል፤ በያቤሎ የባህል ማዕከል መርቀዋል፤ እንዲሁም በአየር ንብረት ሁኔታዎች ምክንያት ቀድሞ ተገልሎ ለነበረው ቀጣና ዓመቱን ሙሉ ትስስር የሚፈጥር አውሮፕላን ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።

‎የአምራች ዘርፉም ተመሳሳይ የለውጥ ታሪክ አለው። በግንቦት 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ፤ መንግሥት ለአራት ዓመታት የተመዘገበውን ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ውጤቶች አቅርቧል። የአምራች ዘርፉ የግብአት አቅርቦት በዓመት 9 ሚልዮን ቶን ወደ 15 ሚልዮን ቶን አድጓል። የምርት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ማደጉን፣ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው ፋይናንስ ከ8.1 ቢልዮን ብር ወደ 50 ቢሊዮን ብር ማደጉን ያሳያል። እነዚህ ስኬቶች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ኤክስፖው በተጠናቀቀ በሃያ ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃውን ከሀገር ውስጥ የሚያገኘውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት «ግራንዲዩር የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ» ፋብሪካን በሞጆ ከተማ መርቀዋል። ቀደም ሲል በገቢ የሴራሚክ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሴራሚክ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ለማቆምና ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ትገኛለች።

‎በቴክኖሎጂው ዘርፍም፥ ዘመናዊ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዳታ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥርዓቶች የሚወሰን መሆኑን በመገንዘብ፥ መንግሥት ኢትዮጵያን ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ 5.0 ማሕቀፎችን ቀድመው ከተገበሩ ሀገራት ተርታ እያሰለፋት ይገኛል።

‎የጽንፈኝነትን ፖለቲካ ውድቅ ማድረግ

‎በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና የቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ።

እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትንና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረ የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው። መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረትና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር 'ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያድርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል። በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብትና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።

‎እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥሎ ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችንና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፣ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ ያካሄደው የሽብር እንቅስቃሴና ዝግጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጃቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም ይሄን የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።

‎በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል ፍላጎት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም። ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን አይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም ሁኔታውን በመቆጣጠር ፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል። በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል። ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል። መሰል ተግባሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃዎችን ይቀጥላል።

‎በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው። የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው።
‎ ‎
ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም!
//

05/06/2026

በክልሉ ከ38 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል-የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ

ሀረር ግንቦት 28/2018( ሀክመኮ):-በሐረሪ ክልል ከ38 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በአምስት ሚሊየን ኮደርስ መርሀ ግብር ስልጠና ከ 38 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።

የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 27 ሺህ 574 የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።

በመርሀ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል በሆኑ ስልጠናውን ያልወሰዱ በቀጣይ ግዜያት ተመዝግበው እንዲሰለጥኑ ሀላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል። https://ethiocoders.et/

Photos from Harari Government communication affairs Office's post 04/06/2026

በበጀት ዓመቱ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራትን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል

በ2018 በጀት ዓመት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራትን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ።

በሀረሪ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ቀሪ ጊዜያት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፥ የበጀት ዓመቱ ቀጣይ እቅዶችን በስኬት ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል።

በመሆኑም ተቋማት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደርና ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የጀመሯቸውን ተግባራት በቀሪ ጊዜያት ለማጠናቀቅ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተለይም በቱሪዝም ልማት፣የትምህርትና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትና በኮሪደር ልማት ላይ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልፀዋል።

የሌማት ትሩፋት እና የከተማ ግብርና ስራዎችን በማጠናከር የግብርና ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ስራም በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት በመስጠት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት ለማድረግ በቀጣይ ርብርብ እንደሚደረግም ገልፀዋል።

03/06/2026

በሐረሪ ክልል 11 ሺህ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው

በሐረሪ ክልል በበልግ እና መኸር እርሻ በድምሩ 11 ሺህ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ኡመር እንደገለፁት፦በክልሉ ያለውን አነስተኛ መሬት በአግባቡ ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

በክልሉ በ2018/19 በበልግ እና መኸር እርሻ በድምሩ 11 ሺህ 956 ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በበልግ ዝናብ እስካሁን 8 ሺህ 681 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ጠቁመው፥ ቀሪው 3 ሺህ 275 ሄክታር በክረምት መኽር ዝናብ ቶሎ ደራሽ ማሽላ እና ስንዴ ለመዝራት አሰፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ሶስት የገጠር ወረዳዎች በሚገኙ ማሳዎች ላይ እየለሙ የሚገኙት ሰብሎችም ማሽላ፣ በቆሎ እና ስንዴ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ለመኸር እርሻው ምርትና ምርታማነት ማደግ አስፈላጊው የማዳበሪያ፣ የዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓት አቅርቦት ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ያመለከቱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በምርት ዘመኑ እየለሙ ካሉ ሰብሎች 300 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰበሰብ መታቀዱንም አስረድተዋል።

በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎችም ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ሙያዊ እገዛና ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም አርሶ አደሩን ከዝናብ ጠባቂነት ከማላቀቅና ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አንፃር አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት።

በቀጣይም የተገኙ አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበትና ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የላቀ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

02/06/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ድምጹን በመስጠት ለዲሞክራሲዊ ግንባታ አስተዋጽዎ አድርጓል የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን

የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን በትላንትናው እለት የተካሄደውን 7ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በሀረሪ ክልል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የክልሉ ፌዴሬሽን አመራሮች ጨምሮ 250 የሚጠጉ ወጣቶች በምርጫ ታዛቢነት ተሳትፈዋል።

የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ረስተም ኡመር እንደገለጹት ፌዴሬሽኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የምልከታ ስራዎችን አከናውኗል።

በዚህም ምርጫው ፍፁም ሰላማዊና ነጻ ሆኖ መጠናቀቁን ተለያዩ አካላት የተሰበሰቡ መረጃዎች ያረጋገጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተገኘው መረጃ መሰረትም ዜጎች የወደዱትንና የፈለጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ያለ ምንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ሳይኖር በነጻነት መምረጥ መቻላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ፣ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ በሰለጠነ መልኩ በድምጹ በመምረጥ ለዲሞክራሲ ግንባታ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ወጣት ረስተም ኡመር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የምርጫው ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ፌዴሬሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

02/06/2026

ከሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ7ኛው ክልላዊና ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫውም በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫው ሂደት ወቅት የታዩ አዎንታዊ ጅምሮችን ይበልጥ በማጠናከር የምርጫውን ሰላማዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነት፣ ነፃና በሕዝብ ዘንድ ታማኒነቱን ማጠናከር ይገባል ብሏል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝቡን ውሳኔ እና ድምፅ እንዲያከብሩ፣ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ሰላም፣ መከባብር እና ሕጋዊ አሠራር እንዲመሩ እና ማንኛውንም ልዩነት በውይይት እና በሕግ ማዕቀፍ እንዲፈቱ ጥሪውን አቅርቧል።

የምርጫው ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መሠረት ተረጋግጦ እስከሚገለፅ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትዕግሥትና በኃላፊነት ስሜት እንዲቀሳቀሱ ጠይቋል።

ከምርጫ በኋላም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር እና የመግባባት ባህል እንዲጠናከር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በጋራ እንደሚሰራ ነው ያስታወቀው።

ማንኛውም ቅሬታ በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት እና በሰላምና በብሔራዊ ጥቅቅም ጉዳይ ትብብርን መሠረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተመላክቷል።

የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ሂደት የመፍታት ባሕላችንን ማጠናከር እና የትብብር እና የፉክክር ሚዛንን በማስጠበቅ የመደብለ ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕልን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የጋራ ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!
#ኢትዮጵያመርጣለች

02/06/2026

ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያውያን በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርገዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ጠቅላላ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁንም አመልክቷል።

አገልግሎቱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ሲል ገልጿል።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመላከተው፣ ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር መሆኗንና ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ እንደምትኮራ ገልጿል።

ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ ከመሻቷ በላይ እንደተሳካላትና ዛሬም የተደገመው ይኸው እንደሆነ አብራርቷል።

ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን ለመምረጥ እንዲሁም ሕገ-መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ለማስያዝ እንደምትሻ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም ማስፈለጉን አስታውቋል።

ለዚህ አገራዊ ጥሪ በምላሹ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው ቀኑን ሲጠባበቁ መቆየታቸውንና የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበልም በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ መዋላቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።

መራጮች ሌሊቱንም ጭምር አጋምሰው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫ ያደርገዋል ብሏል።

ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያልደረደሩት እንቅፋት እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር ባለመኖሩ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁንና ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ ማሸነፏን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ታቀርባለች ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።

01/06/2026

በሀረሪ ክልል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ምርጫውን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት

#ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ

01/06/2026

ዲሞክራሲያዊ መብቴን ተጠቅሜ ለሀገር ይበጃል ያልኩትን መርጫለሁ- ባለሃብቱ አንዋር ዩሱፍ

#ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Ethiopia, Harari Peoples Regional State, Harar City
Harar