04/10/2026
የሐረሪ ፖሊስ የተተከሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞችን የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ ሥራ አከናወነ።
የአረንጓዴ ዐሻራ የተተከሉ ችግኞች በሕይወት እንዲቆዩና የታለመላቸውን የአካባቢ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ ከተከላ በኋላ ቀጣይነት ያለው የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ ተከናውኗል።
በዚህ መሠረት የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቀደም ሲል በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞችን የውሃ ማጠጣትና የእንክብካቤ ሥራ አከናውኗል።
በሐረሪ ክልል የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ለምግብ ዋስትናና ለኢኮኖሚ ጥቅም የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች ሲሆኑ 30 በመቶው ደግሞ የደን ዛፎችና ለእንስሳት መኖ የሚውሉ ዕፅዋት ናቸው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር የህብረተሰብ ተሳትፎን የሚያጎለብት አገራዊ ንቅናቄ መሆኑ ተገልጿል።
ለመጪው ትውልድ ጤናማና አረንጓዴ አካባቢ ማስረከብም የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑ ተጠቁሟል።
ችግኞች የደን ሽፋንን ለማሳደግ የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ የውሃ ሀብትን ለማጎልበትና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ዕድገት ለምግብ ዋስትናና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክት ዘላቂ የልማት ንቅናቄ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመሆኑም የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁና የተጠበቀውን ጥቅም እንዲያስገኙ የውሃ ማጠጣት የአረም ማስወገድና ሌሎች የእንክብካቤ ሥራዎች በቀጣይነት መከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል።
ሁሉም ዜጎችም በተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ ላይ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በሐረር ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞች መተከላቸው የሚታወቅ ሲሆን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ንቁ ተሳትፎ ሲያደርግ ቆይቷል።
በዚህ የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ መርሐ ግብር ላይ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ የወንጀል መከላከል ዘርፍ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ነገራ ዱፌራ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ያህያ አብደሰላም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የፖሊስ አባላት እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የፖሊስ ተመሪዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ ፦ ሳጅን ዮሐንስ መካ