23/05/2026
በአሚር ኑር ወረዳ ታላቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሄደ
በአሚር ኑር ወረዳ ቀበሌ 02 የብልፅግና ፓርቲን የምረጡኝ ቅስቀሳ አስመልክቶ ደማቅ የ“ቡና ጠጡ” መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የጀጎል ኮሪደር ልማትን ጨምሮ በክልሉ የተከናወኑ ግዙፍ የልማት ስራዎች የወጣቶችና የሴቶችን ሁለንተናዊና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸው ተገልጿል።
በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ፤ ፓርቲው ሴቶችንና ወጣቶችን ያካተተ፣ በተግባር የሚታይ የልማትና የብልፅግና ጉዞ እያረጋገጠ መሆኑን አብራርተዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በመፍጠር እና በመፍጠን ስራ መርህ እየተገነባ የሚገኘው አዲስ የስራ ባህል፣ ወጣቶች ሌትና ቀን በመታተር ለሀገራቸውና ለክልላቸው ዕድገት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ማስቻሉንም ገልፀዋል።
የህዝባችን የዘመናት ቁጭት ወደ ድል በተለወጠበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የወጣቶች አሻራ የጎላ እንደሆነ ሁሉ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የጀጎል ኮሪደር ልማት የዚሁ ስኬት ትልቅ ማሳያ መሆኑ በመድረኩ አንስተዋል።
በተለይም የጀጎልን ታሪካዊና ባህላዊ እሴት በጠበቀ መልኩ የኮሪደር ልማቱ መከናወኑ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለቱሪስቶች ደግሞ ይበልጥ ሳቢና ማራኪ አድርጓታል ብለዋል።
በኮሪደር ልማቱ የመንገድ መብራቶች በፅዳትና ውበት እንዲሁም በተያያዙ የልማት ስራዎች ላይ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸውና በገንዘባቸው ታሪካዊ አሻራቸውን ያሳረፉ ሲሆን፣ ሰፊ የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ፈጣን ዕድገት በሺዎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውንና ብዙዎችም የኑሮ ደረጃቸውን በእጅጉ ማሻሻላቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል።
የሐረር ከተማም ሆነ የአጠቃላይ ሀገሪቱ ተምሳሌታዊ ዕድገት እውን ሊሆን የቻለው የወጣቶችን እና የሌላውንም የህብረተሰብ ክፍል እምቅ አቅም በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ያስቻለው አካታቹ የ“መደመር ፍልስፍና” ተግባራዊ መሆን መጀመሩ እንደሆነ ተመላክቷል።
በመጨረሻም ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ የጀጎል ኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የፓርቲው በተግባር የተረጋገጠ ጉዞ ውጤቶች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ማህበረሰቡ ለፓርቲው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልና ነገን ዛሬ እየገነባ፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ የሚገኘውን ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።
የመደመር፣ የትብብር እና የአንድነት መገለጫ የሆነው የስንዴ ነዶ እንድመርጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ምርጫ2018
23/05/2026
በአሚር ኑር ወረዳ ቀበሌ 01 ገንደ ፌሮ የብልጽግና ህብረት በ"ቡና ጠጡ" መርሃ-ግብር ደማቅ የምረጡኝ ቅስቀሳና የዕጩዎች ማስተዋወቂያ አካሄደ
በአሚር ኑር ወረዳ የቀበሌ 01 ገንደ ፌሮ ብልጽግና ህብረት ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የሚሆኑ ዕጩዎችን የማስተዋወቅና የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በባህላዊ የ"ቡና ጠጡ" ሥነ-ሥርዓት በድምቀት አካሂዷል።
በገንደ ፌሮ በተካሄደው በዚህ የምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ መድረክ ላይ ከሁሉም የአካባቢው መንደሮች የተወጣጡ የፓርቲው ደጋፊዎች፣ አባላት፣ እናቶችና ወጣቶች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች በነቂስ ተገኝተዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሙስጠፋ ኢሊያስ ብልጽግና ሰው-ተኮር ለውጥ ለማምጣት በትጋት የሚሠራ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡ መንግሥትና ፓርቲ የጀመሯቸውን የልማት፣ የሰላም፣ የአንድነት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታትና ሁለንተናዊ ልማትን የማረጋገጥ ሥራዎች ለማስቀጠል ከምንም ነገር በላይ ለአንድነታችንና ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል።
ብልፅግና ቃልን በተግባር የፈተነ የሀገር ፓርቲ መሆኑን ገልጸው፤ አካታች ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለማስቀጠል ኅብረተሰቡ ከተሳሳቱ ትርክቶች በመራቅ የለውጡን ቀጣይነት በተስፋ ሊጠብቅና ሊደግፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአሚር ኑር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሚር ሙኽታር በበኩላቸው ባለፉት አምስት ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የተመዘገቡ የለውጥ ድሎች የዚህ ሕያው ምስክር ናቸው ብለዋል።
በተለይም በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ ለረጅም ጊዜ ሲነሱ የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በለውጡ መንግሥት ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
ለአብነትም በወረዳው የተከናወኑ የመሠረተ-ልማት ግንባታ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውንና በጅምር ላይ ያሉ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ጠቁመዋል።
የሸንኮር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱላሂ ለጋራ ልማትና አብሮነት እንደ "ቡና ጠጡ" ያሉ የባህል እሴቶችን በማሳደግ የሕዝቡን የብልፅግና ጉዞ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በዚህ ደማቅ የ"ቡና ጠጡ" የምረጡኝ ቅስቀሳ መድረክ ላይ የክልል ፣ የወረዳና የቀበሌ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
13/05/2026
በአሚር ኑር ወረዳ ት/ት ቤቶች የጤና አገልግሎት ዘመቻ ተካሄደ
በአሚር ኑር ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ለመምህራንና ለተማሪዎች የተለያዩ የጤና አገልግሎቶች በስፋት እየተሰጡ መሆኑ ተገለጸ።
በዚህ የጤና ዘመቻ ውስጥ የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሀኒት እደላ፣ የደም ግፊት ምርመራ፣ የስነ ምግብ ልየታ (Nutritional Screening)፣ የHPV vaccine ክትባት እና ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች ለተጠቃሚዎች እየተሰጡ ነው።
መርሃ ግብሩ የተማሪዎችንና የመምህራንን ጤና ለማሻሻል፣ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከል እና ጤናማ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር ታላቅ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።
04/05/2026
በአካባቢ ጽዳትና በወባ መከላከል ላይ ያተኮረ የተቀናጀ ዘመቻ ተካሄደ።
በአሚር ኑር ወረዳ የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ፣ የወርዳ ጤና ፅ/ ቤት፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና የሴፍቲኔት ፕሮግራም አባላት በጋራ በመሆን ሰፊ የአካባቢ ጽዳትና የወባ መከላከል ስራ አከናወኑ።
በተለይም በቀበሌ 01 ግንደ ፌሮ አከባቢ ለወባ በሽታ መራቢያነት ተጋላጭ የሆኑ ስፍራዎችን በመቃኘት፣ በሽታው አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰራ ይገኛል ።