The Harari People Regional State Culture, Heritage and Tourism Bureau

Share

The official page of Harari Region Culture, Heritage and Tourism

Photos from Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን's post 21/04/2026
21/04/2026

ባለፍት ዘጠኝ ወራት ከ151 ሺህ 404 በላይ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ሀረሪ ክልልን ጎብኝተዋል

ባለፍት ዘጠኝ ወራት ከ151 ሺህ 404 በላይ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ሀረሪ ክልልን ጎብኝተዋል ክልሉን መጎብኘታቸውን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ቅርስ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ባለፉት 9 ወራት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በክልሉ የቱሪስት ፍሰቱን የሚያጎለብቱ ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው።

በተለይም የዓለም አቀፍ ህያው ቅርስ የሆነውን የጁገል ቅርስን ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ እንዲሁም የተለያዩ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ሐረር ከተማን በቱሪስቶች ምቹና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በተለይም በ4ኛው ዙር በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የመልሶ ልማት ያለ መንግስት ተጨማሪ በጀት ተቋማትና ህብረተሰቡን በማስተባበር 9 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መልሶ ማልማት ተግባራት መከናወኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አክለዋል ።

በከተማው እየተሰሩ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ልማት ስራዎች ለከተማው ተጨማሪ አቅም ከመፍጠር ባሻገር የቱሪስት ፍሰቱ እና ቆይታ እንዲጨምር ማስቻሉን አክለዋል።

የሀገር ውስጥ ቱሪሰት ፍሰቱ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 13.14% እንዲሁም የውጪ አገራት ቱሪስቶች ፍሰት 45.1% ብልጫ ማሳየቱንም በማሳያነት አቅርበዋል።

በዘርፉ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩንም በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል።

የክልሉን ባህል ፣ ቅርስና ቱሪዝም ከማስተዋወቅ አንጻርም ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን አክለዋል፡፡

ባህላዊ ክብረ በዓላት ማለትም የሹዋሊድ፤ኸቲመት፤ የዊርሻቶ በዓል ፣ የሰፈር ፋታሕ በዓል እና ኢሬቻ በዓልን ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ተደርጓል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ባለፈት ዘጠኝ ወራት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ጎብኝዎች ከ368 ሚሊየን ብር በላይ በክልሉ ወጪ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የህዝብ አብሮነትና አንድነትን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ሕብረ ብሄራዊ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ የዋሻና ድንጋይ ስዕሎች መገኝታቸውን የገለጹት ኃላፊው ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ ቀሪ ወራትም በክልሉ በባህል፣ በቅርስ እንዲሁም በቱሪዝም ልማት ሥራ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚከናወን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

21/04/2026

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ151 ሺህ 404 በላይ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ሀረሪ ክልልን ጎብኝተዋል
**********************************

13/08/18

Photos from Ethiopian News Agency's post 07/04/2026
06/04/2026

ሐረር ከተማ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የአርኪኦሎጂ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ መጋቢት 28/2018

በሩሲያ በሴንት ፒተርስበርግ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የአርኪኦሎጂ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይም የሐረርን ልዩ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ለማጥናትና ለመጠበቅ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ምክክር ተደርጓል።

የሀረሪ ክልል የቱሪዝም ኃላፊ አቶ ሳሚ አብዱልዋሲ በጉባኤው ላይ እንዳሉት ሀረር የንግድ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ትስስር ማዕከል ሆና በትውልድ ቅብብሎሽ ከአንድ ሺህ አመታት በላይ የተሻገረች እድሜ ጠገብ ከተማ ነች።

በ16ኛው ክፍለ ዘመን በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል እንደነበረች አስታውሰዋል።

ከተማዋ በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ እንዲሁም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ቅርሶችን በጉያዋ አቅፋ የያዘችና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ነች ብለዋል።

ኃላፊው በገለጻቸው ሀረር ከተማ ከቱሪዝም ልማት አንፃር ያላትን ሰፊ እድል፤ ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት እና እየተከናወኑ ያሉትን የቅርስ ጥብቃና እንክብካቤ የቱሪዝም የመዳረሻ ልማት ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

ከተማዋ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እና ለቱሪስቶች ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በሀረር ከተማ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ሩሲያዊው ገጣሚ እና ተጓዥ ኒኮላይ ጉሚሌቭ በሀረር ከተማ ለረጅም ግዜ መቆየቱን ጠቁመው የገጣሚው ጉዞም ለኢትዮጵያ የባህል ጥናት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው ገልጸዋል።

ሀረር ከተማ በጉባኤው ላይ መሳተፏ ልምድ ለመለዋወጥና ተሞክሮ ለመቅሰም ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ከጉባኤው የሚቀሰመው ልምድና ተሞክሮም በቀጣይ በሀረር ከተማ የጀመረችውን ዘርፈ በዙ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

Photos from Ordin Bedri's post 06/04/2026
Photos from Harari Mass Media Agency's post 03/04/2026
Photos from Harari Government communication affairs Office's post 31/03/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Amir Uga
Harar