09/04/2026
Harari Housing Development & Government Construction Agency
We build the future. Restoring the past.
09/04/2026
09/04/2026
06/04/2026
ኢትዮጵያ ከውድቀት ወደ ማንሰራራት፣ ከስጋት ወደ ተስፋ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከቁልቁለት ወደ ክፍታ፣ ከመፈረካከስ አደጋ ወደ ጠንካራ አገረ መንግስት ግንባታ መሸጋገሪያ መሰረት የጣለችበትን አገራዊ ለውጥ ለመደገፍ በሀረሪ ክልል በተካሄደ ትእይተ ህዝብ ላይ የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስራተኞች እና አመራሮች ተገኝተዋል።
የቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
መጋቢት 28/2018
26/03/2026
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት እንኳን ለሹዋሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የሀገራችን ሕዝቦች የአብሮነት ዕሴትን ከሚያጎለብቱ ባህላዊ በዓላት አንዱ በክልላችን በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የሹዋሊድ በዓል ይጠቀሳል።
የዘንድሮው የሹዋሊድ በዓል በክልሉ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን በሚያሳይ መልኩ እና የክልሉን ልማት እና ዕድገት የበለ ማጠናከር በሚያስችል መልኩ በደማቅ ዝግጅት ይከበራል።
ይህ ባህላዊ በዓል በክልሉ የመቻቻል፣ የአብሮነት እና የሰላም እሴትን በተለይም የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታው የጎላ ነው።
የዘንድሮውን የሸዋሊድ በዓል በተሳካ መልኩ ለማክበር የተለያዩ ኮሜቴዎች ተዋቅረው ሥራዎች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በዓሉ ባማረና በደመቀ መልኩ ለማክበር አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሁሉ ተጠናቀዋል።
በበዓሉ ላይም የሐረርን ታሪክ፣ እሴት እና ባህልን ሊያስተዋውቁ እና ሊገልጹ የሚችሉ ዝግጅቶችን በወንድማማችነት መንፈስ ለታዳሚው የሚቀርቡ ይሆናል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት በድጋሚ እንኳን ለሹዋሊድ በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆን ይመኛል።
19/03/2026
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም በተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር እንዲያከብር የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
ህዝበ ሙስሊሙ በተለይም በረመዳን ፆም ወቅት ያሳየውን የመደጋገፍንና መረዳዳት እሴቶችን በማጠናከር እንዲሁም ሰላምንና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ማክበር ያስፈልጋል።
ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ በክልሉ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነትን በማጠናከር በክልሉ እየተከናወኑ በሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ ድጋፉን እንዲያጠናክር የክልሉ መንግስት በዚህ አጋጣሚ ይጠይቃል።
የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ይመኛል።
ኢድ ሙባረክ!
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት
መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
ሐረር
18/03/2026
የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የዒድ አል-ፊጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለኤጀንሲው ሰራተኞች ድጋፍ አደረገ።
የቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
መጋቢት 09/2018
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Harar
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:30 |
| Tuesday | 08:00 - 17:30 |
| Wednesday | 08:00 - 17:30 |
| Thursday | 08:00 - 17:30 |
| Friday | 08:00 - 17:30 |
| Saturday | 08:00 - 12:00 |
