26th International Harar Day

26th International Harar Day

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from 26th International Harar Day, Government Organization, Harar.

Photos from 26th International Harar Day's post 12/07/2024

26ኛው አለም ዓቀፍ የሐረር ቀን በዓል በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማጎልበት አቅም የፈጠረ እንደነበር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አስታወቁ።

በክልሉ ሲከበር የቆየው 26ኛው ዓለም ዓቀፍ የሐረር ቀን በዓል ተጠናቋል።

በበዓሉ ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለጹት በዓሉ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲነቃቁ እድል ፈጥሯል።

በተለይ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ህዝቡና አመራሩ በመቀናጀት በክልሉ ከተማና ገጠር የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በጽዳትና ውበት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች አበረታች የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዓሉ የልዩነትና የመገፋፋት ሳይሆን የአብሮነትና የአንድነት፣ የመደጋገፍና አብሮ የመስራት ባህል የጎለበተበት መሆኑን በተግባር መታየቱንና ስኬታማ እንደነበርም ገልጸዋል።

ለበዓሉ ስኬታማነትም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችና አመራሩ ተናቦ እና ተቀናጅቶ በመስራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑንም ጠቁመዋል።

በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ የመጡ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገሪቱና በክልሉ የተከናወኑ የሰላም፣ የልማትና ሌሎች ስራዎችን ተመልክተው ምስክር የሰጡበት መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲሁም በክልሉ የተከናወኑ አጠቃላይ የልማት ስራዎች መመረቃቸውን እና የኢንቨስትመንት አማራጮችንም መመልከታቸውን ጠቅሰው ይህም አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ወደ ሀገር በመምጣት ተሳትፎ ላደረጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ምስጋና አቅርበዋል።

በቆይታቸውም ያጎለበቱትን መልካም ትስስር በቀጣይም በኢንቨስትመንት፣ በዲፕሎማሲ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በልማትና በሌሎች መስኮች ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ቅርስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በበኩላቸው በዓሉ "ሐረር የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት" በሚል መሪ ሃሳብ መከበሩን አስታውሰዋል።

በዓሉም የክልሉን የልማት ስራዎች እንዲጎለብቱ እና ገጽታ መገንባት ማስቻሉን ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ የመጡ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የልማትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እድል መፍጠሩን አክለዋል።

በበዓሉ ማጠናቀቂያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አፈ ጉባዔ አቶ ሙህየዲን አህመድ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ዳያስፖራዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በእለቱም ለበዓሉ መሳካት አስተዋፅኦና ተሳትፎ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀትና እውቅና ተሰጥቷል።

Photos from 26th International Harar Day's post 10/07/2024

የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ የሀረሪ ቋንቋ መተርጎሚያ አስመርቆ አገልግሎት ላይ አዋለ።

በሀረር ከተማ 26ኛው አለም አቀፉ የሀረር ቀንን በማስመልከት የባህል ቀን በዛሬው ዕለት የተከበረ ሲሆን በመርሃግብሩም ላይ የሀረሪ ቋንቋን ወደ አማሪኛ ኦሮሚኛና እንግሊዘኛ መተጎርግም የሚችል መተግበሪያ በይፋ አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል ።

መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ጉባኤ አፈጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ አለም አቀፉ የሀረር ቀን ክብረ በዓል በተለያዩ አገራት የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች እርስ በእርስ የሚገናኙበት ብሎም ከአገራቸው ጋር ያላቸወን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ የክልሉ ባህል እና ቋንቋ ሳይበረዝ ተጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ገልፀዋል።

የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በበኩላቸው በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገለግሎት የበቃው የትርጉም መተግበሪያ የሀረሪ ቋንቋን ለማሳደግ ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

የሀረሪ ቋንቋ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋርም ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዕለቱ የተለያዩ ባህላዊ ትርዒቶቸ የቀረቡ ሲሆን የሀረሪ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣ የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Photos from 26th International Harar Day's post 05/07/2024

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን ምክንያት በማድረግ የእግር ኳስ ውድድር መካሄድ ጀመረ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ በተገኙበት 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን ምክንያት በማድረግ የእግር ኳስ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።

በአባዲር ኢንተርናሽናል ስታድየም በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ የአውስትራሊያ ኮሙዩኒቲ ከሀረር እግር ኳስ ቡድን ጋር ባደረገው ጨዋታ ሀረር ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በተመሳሳይ የሀረሪ ክልል አመራሮችና የአዲስ አበባ ሀረሪ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ባደረጉት ጨዋታ ሀረሪ ክልል አመራሮች የአዲስ አበባ ኮሙዩኒቲን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ዛሬ በይፋ የተከፈተው የእግር ኳስ ውድድር ለተከታታይ አስራ አራት ቀን ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

በመክፈቻ ውድድሩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ፣ የፓርቲው ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመርን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች ፣ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ ዲያስፖራዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

05/07/2024

በሀረሪ ክልል በነገው እለት የዲያስፖራ አባላት 500 ሺህ ችግኞችን ይተክላሉ

በሀረሪ ክልል በነገው እለት የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲያስፖራ አባላትና የክልሉ ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ይጀመራል።

ከተለያዩ አለማት የመጡ የክልሉ የዲያስፖራ አባላትም በነገው እለት በሚጀመረው ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ማስጀመሪያ ላይ 500 ሺህ ችግኞችን ይተክላሉ።

የዲያስፖራ አባላቱ እንደየመጡበት አካባቢ የመትከያ ስፍራ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል እና በ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ በርካታ ሀረሪዎችና የሀረር ተወላጆች ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን የሚያስፖራ አባላቱ በሚኖራቸው ቆይታም በአረንጓዴ አሻራ በተጨማሪ በበጎ ፍቃድ አገልግሎትና በሌሎች መርሃግብሮች ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።

በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት መጠናቀቁ ይታወሳል።

Photos from Ordin Bedri's post 04/07/2024
Photos from 26th International Harar Day's post 03/07/2024

በሀረሪ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ ይደርጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ሰኔ 26/2016(ሀክመኮ) :-በሀረሪ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ

በሀረር ከተማ 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀ የንግድ ትርኢትና ባዘር ተከፍቷል።

የንግድ ትርኢትና ባዛሩን የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የማህበራዊ መስተጋብርን እና ኢኮኖሚውን በማጠናከር ረገድ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በክልሉ በቱሪዝም በተለይ በሆቴል ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት የመስሪያ ቦታ ከማመቻቸት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ሀረር ከ1 ሺ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ጥንት በአለም አቀፍ ንግድ የምትታወቅ የራሷ የመገበያያ ሳንቲም የነበራት በተለይ በዘይላ እና በርበራ ንግድ እውቅናን ያተረፈች እንደነበረች ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

በመሆኑም በክልሉ ያለውን የዕርስ በዕርስ መስተጋብሩ ይበልጥ በማጎልበት 26ኛውን አለም አቀፍ የሀረር ቀን ኢኮኖሚውን በሚያነቃቁ መርሀግብሮች ለማክበር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በክልሉ ለኢንቨስትመንት ትኩረት ሰቶ በመስራት በከልሉ ምርት እና ምርታማነትን ከማጎልበት ባሻገር ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርም ልዩ ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰራ አክለዋል።

በክልሉ በርካታ የልማት ስራዎች ፍጥነትና ፈጠራን ባካተተ መልኩ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ርዐሰ መስታዳድሩ ጠቁመዋል።

በቀጣይም በከተማና በገጠር የተጀመሩ የልማት
ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች የአንድ ሰሞን ስራ ሳይሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

በግንድ ትርኢትና ባዛሩ ከተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

03/07/2024
Photos from 26th International Harar Day's post 02/07/2024

ለ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሀረር ከተማ አቀባበል ተደረገ

ለ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ ከተለያዩ አለማት ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሀረር ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ያደረጉት ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል እንዲሁም በ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዲያስፖራዎች ሀረር ከተማ ሲደርሱ በክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ይጀምራል።

02/07/2024

26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በሀገራዊ ለውጡ የዳያስፖራውን ሚና በሚያጎሉ ሁነቶች ይከበራል:- የበዓሉ አከባበር ዐቢይ ኮሚቴ

26ኛውን ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን የዳያስፖራውን ሚና በሚያጎሉ የተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የበዓሉ አከባበር ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ።

የበዓሉን ዝግጅት በተመለከተ የበዓሉ አከባበር አብይ ኮሚቴ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

የኮሚቴው ሰብሳቢና የሐረሪ ጉባዔ አፈ ጉባዔ አቶ ሙህየዲን አህመድ እንደተናገሩት 26ኛው ዓለም ዓቀፍ የሐረር ቀን በዓል በክልሉ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል።

ለበዓሉም በውጭ ሀገር የሚኖሩ የሐረር ተወላጆችና ወዳጆች፣ ዳያስፖራዎች እንዲሁም ከሀገሪቱ የተለያዩ ክፍል የሚገኙ እንግዶች ወደ ክልሉ በመግባት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

በዓሉ ታሪክን፣ ባህልንና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማሳደግና ለመጪው ትውልድ አኩሪ ባህልና ታሪክን በማስተላለፍ ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘንድሮም የታለመለትን ዓላማ ይዞ እንደሚከበር አመልክተዋል።

በዓሉ “ሐረር የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከበር የተናገሩት አቶ ሙህየዲን፤ መሪ ቃሉን የሚመጥን የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩም ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒትና ባዛር እንዲሁም የሀገሪቱና የክልሉ ገጽታ የሚገነባበት የዳያስፖራው ሚናና የሰላም እሴቶች ላይ ያተኮሩ ጽሁፎች የሚቀርቡበት ሲምፖዝየም እንደሚካሄድም ተናግረዋል።

እንዲሁም አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ ግብር የዝግጅቱ አካል መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙህየዲን፤ ለመርሃ ግብሩም የችግኝ ዝግጅትና የጉድጓድ ቁፋሮ መከናወኑን ገልጸዋል።

በክልሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ለውጥ የሚያመጡ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች በበዓሉ ሰሞን እንደሚመረቁም ጠቅሰዋል።

የስፖርት፣ ባህልና ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች እንዲሁም የአብሮነት ቀን የበዓሉ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የበዓሉን ቀን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

Photos from 26th International Harar Day's post 01/07/2024

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን በተሳካ መልኩ ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል- አቶ ኦርዲን በድሪ

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን በተሳካ መልኩ ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።

ርዕሰ መሰተዳድሩ ከሰኔ 26 ጀምሮ በሀረር ከተማ ስለሚከበረው በዓል አስመልክተው እንደተናገሩት የዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ከወትሮው በተለየ መልኩ በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

ለበዓሉ ስኬታማነት ሲደረጉ የቆዩ ስራዎች ውጤታና በተለይም የሀረር ከተማን ከፍታ ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሰረት የተጣለበት ስለመሆኑ አንስተዋል።

በዓሉ በተለያየ አለማት የሚገኙ ሀረሪዎችና የሀረር ተወላጆች ተሰባስበው የሚያከብሩት በዓል መሆኑን ጠቁመው ይህም እርስ በእርስ መደጋገፍንና አንድነትን ከማጠናከር አንፃር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው 26ኛ አለም አቀፍ የሀረር ቀን ሀረር ከተማ መከበሩም ዲያስፖራው በከተማው በተፈጠረው ምቹ ሁኔታን በመጠቀም መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስና ስለሀገሩ ነባራዊ ሁኔታ እንዲገነዘብ ያግዛል ብለዋል።

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያደረጉትን ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል እና በዓሉን ለማክበር በርካታ ሀረሪዎችና የሀረር ተወላጆች ወደ ሀገር ቤት እየገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከተለያዩ አለማት እየመጡ የሚገኙ ዲያስፖራዎች ወደ ናፈቋት ሀረር ከተማ ሲደርሱም በተለመደው የእንግዳ ተቀባይነት እሴት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

በዓሉም ወንድማማችነትን በሚያጠናክና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ በድምቀትና በተሳካ መልኩ ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት መጠናቀቁን አብራርተዋል።

የበዓሉ አከባበር ስኬታማነት የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ህዝቡ እያደረገው የሚገኘው ርብርብ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

Photos from 26th International Harar Day's post 01/07/2024

ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንትና በበጎ ፈቃድ ስራዎች አሻራቸውን እንዲያኖሩ ዝግጅት ተደርጓል-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንት፣ በተለያዩ የልማት ስራዎችና የበጎ ፈቃድ ተግባራት አሻራቸውን እንዲያኖሩ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተለያዩ ዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትወልድ ኢትዮጵያውያን ክረምቱን ወደ ሀገራቸው በመግባት አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ከአውስትራሊያና አሜሪካ በ26ኛው የሐረር ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአቀባበል ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከሐረሪ ክልል አመራሮች ጋር በመሆን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች አሻራቸውን እንዲያኖሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሶስተኛ ዙር ጥሪ መቅረቡን አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አስታውሰዋል።

ወቅቱ ትምህርት የሚዘጋበት በመሆኑ በርካታ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን እንዲያውቁ ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ መሰረት በሐረር ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዜጎችን ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ተሳትፏቸው እንዲጠናከር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም የልማት ሥራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን አሻራቸውን እንዲያኖሩ ምቹ ሁኔታዎች የመፍጠሩ ሥራ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል።

የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ዑመር በበኩላቸው የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራ አባላት የሐረር ቀን በዓልን ከማክበር ጎን ለጎን በተለያዩ በጎ አድራጎት መርሃ ግብሮች እንዲሳተፉ በክልሉ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ነጻ የህክምና አገልግሎት፣ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውኑም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ለውጥ ማስመዝገቧን ያነሱት አቶ አብዱልሀኪም፥ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፍ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አቅናው እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ በሁለት ዙር ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን መጥተዋል።

አሻራዎን ያኑሩ በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 20/2016 ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን እንዲያውቁ ለሦስተኛ ዙር ጥሪ መቅረቡንም ጠቁመዋል።

አገራዊ ጥሪው ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ በአካል ቀርቦ ለማየት እድል እንደሚሰጥም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ያነሱት።

ዛሬ አዲስ አበባ ከገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን መካከል በአውስትራሊያ ጠቅላላ ሀኪም የሆኑት ጀማል መሀመድ(ዶ/ር) ፤ በሙያቸው ሀገራቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

የኩላሊት እጥበት ክሊኒክ ለማቋቋም ፕሮጀክት መቅረጻቸውንም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ ከአውስትራሊያ የመጡት ዱሴት አብዶሽ እና ፈቲሃ አብዱላሂ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ የረጅም ጊዜ እቅድ እንደነበራቸው አንስተዋል።

ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ተከትሎም በተለያየ የልማትና ኢንቨስትመንት ስራ ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Harar