የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ

የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ

Share

የሐረሪ ከልል ገቢዎች ባለሥልጣን

Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 24/01/2024

ሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2016 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ::

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2016 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ::
የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ያህያ አብዱረሂም እና የማናጅመንት አባልት በተገኙበት የቢሮውን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀሙን በመገምገም በቀጣይ የቱክረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እንዲሁም የስራ መመሪያዎችን በመስጠት ተጠናቋል።

16/5/2016

!! ገቢ ለልማት !!

የሐረሪ ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት

ቴሌግራ ቻናላችን :- https://t.me/HARARIREVENUE
በፌስቡክ ይህችን :- https://www.facebook.com/HarariRevenueOffice
በYoutube channel :- https://youtube.com/channel/UCbDC6MzW6pDkKH8g6F-SgLw
camkryst

04/01/2024
Photos from Harari Government communication affairs Office's post 26/12/2023
Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 14/12/2023

የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2016 በጀት አመት ለደረጃ እና ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በታክስ ህግ፤አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች ዙሪያ የሁለተኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በ2016 በጀት አመት ለደረጃ እና ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በታክስ ህግ፤አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች ዙሪያ ለሁለተኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናውን ሲመሩ የነበሩት የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ የትምህርት እና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ፍጹም ታሪኩ እንዳሉት ግብር ከፋዩን በማሰልጠን መብት እና ግዴታውን ጠንቅቆ አውቆ ግብር የሚከፍል ማህበረሰብ ማፍራት እደሚቻል ገልጸዋል።

4/04/2016

!! ገቢ ለልማት !!

የሐረሪ ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት

ቴሌግራ ቻናላችን :- https://t.me/HARARIREVENUE
በፌስቡክ ይህችን :- https://www.facebook.com/HarariRevenueOffice
በYoutube channel :- https://youtube.com/channel/UCbDC6MzW6pDkKH8g6F-SgLw
camkryst

Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 14/12/2023

በሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሲሰራ የነበረው ከዘጋ ኡጋ እስከ አባ ያዚዝ የጬር ኡጋ ለነዋሪ እና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ በዛሬው እለት ክቡር ፕሬዘዳንት ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተመረቀ።

Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 09/12/2023

የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለቀድሞ አመራሮች እንዲሁም ለአዲስ አመራሮች አቅባበል አደረገ።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የቀድሞ የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን እና ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ካሊድ አብዲ ሽኝት እና ለአዲስ የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር እና ም/ቢሮ ሃላፊ ያህያ አብዱረሂም የሥራ ርክክብ አድርጓል።

በፕሮግራሙ ላይ የሐረሪ ክልል ገቢዎች ሰራትኞች ለቀድሞ አመራሮች ሽኝት በማድረግ ለአዲሶቹም አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

በርክክቡ ወቅትም ቢሮ ሃላፊዋ እንደተናገሩት የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል አንዳንድ ያሉ ድክመቶችንም ለይቶ በማውጣት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ አስውቀዋል።

29/03/2016

!! ገቢ ለልማት !!

የሐረሪ ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት

ቴሌግራ ቻናላችን :- https://t.me/HARARIREVENUE
በፌስቡክ ይህችን :- https://www.facebook.com/HarariRevenueOffice
በYoutube channel :- https://youtube.com/channel/UCbDC6MzW6pDkKH8g6F-SgLw
camkryst

Photos from Harar Municipality የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት's post 08/12/2023
Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 03/12/2023

ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃዲር የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያህያ አብዱረሂም ም/ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃዲር የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያህያ አብዱረሂም ም/ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሾሙ።
የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ መልካም የስራ ዘመን አንዲሆንላቸው ይመኛል።

23/03/2016

!! ገቢ ለልማት !!

የሐረሪ ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት

ቴሌግራ ቻናላችን :- https://t.me/HARARIREVENUE
በፌስቡክ ይህችን :- https://www.facebook.com/HarariRevenueOffice
በYoutube channel :- https://youtube.com/channel/UCbDC6MzW6pDkKH8g6F-SgLw
camkryst

Photos from የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ's post 01/12/2023

የፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የፌደራል ድጎማ በጀት ቀመርን ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች የፌደራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን፤ እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመር የመወሰን፤ ከሀገራዊ ኃላፊነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱም የተጣሉበትን ኃላፊነቶችና የወጡ ሕጎችን ተከትሎ የሕገ መንግሥት የበላይነት፣ ሕገ መንግስታዊነት፣ ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሀገራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በክልሎች መካከል ውጤታማና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚረዳ የፌዴራል ድጎማና የጋራ ገቢዎች ቀመር እንዲዘጋጅ በማድረግ፤ የማከፋፈያ ቀመሮቹ በፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና በክልሎች የተመጣጠነ እድገት ላይ ያላቸዉን አንድምታ እንዲጠና በማድረግ ሰፊ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አሁን ያለው ቀመርና አፈጻጸሙ እንደገና መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከቋሚ ኮሚቴውና ከሚመለከታቸው የፌደራል ባለድርሻ አካለት ጋር ግብዓት ለመሰብሰብ የታለመ መድረክ ነው ብለዋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የፊስካል ፌዴራሊዝም ሪፎርም መደረጉንና በርካታ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎችን በተገቢው የሕግ አግባብ ለመመለስ ቁርጠኝነት እንደሚፈልግና ለዚህም ሁሉም ባለ ድርሻ አከላት በርብርብና በእኔነት ስሜት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

በቀጣይ ለሚደረገው የቀመር ማሻሻል ስራ ከሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ጋር ተያይዞ በጥናትና በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን መስራት ለቀመር ማሻሻል ሂደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

በመደረኩ የሚነሱ አስተያየቶችና ሀሳቦች ቋሚ ኮሚቴው ለሚያዘጋጀውና ለምክር ቤት ለሚቀርበው ሀገራዊ ሰነድ ትልቅ ግብዓት ሆኖ እንደሚወሰድም ነው የገለጹት፡፡
ለቀመር ዝግጅት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ወቅታዊና ተአማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ የጋራ ስምምነት መደረሱን ተጠቅሷል።

በመረጃ አቅርቦት ረገድ ሃላፊነት የተጣለባቸው የፌዴራልና የክልል ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንጭ :- ገቢዎች ሚኒስቴር

Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

4ኛ ሻሽ ጋራዥ
Harar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30
Saturday 08:30 - 12:30