04/06/2026
የሐረሪ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በ“ሰቆጣ ቃልኪዳን ማስፋፊያ ፕሮጀክት” አማካኝነት በአሚር ኑር ወረዳ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና በፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን (GBV) ለመከላከል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ተማሪዎች ከማንኛውም ዓይነት ጥቃትና ስጋት ነፃ በሆነ አካባቢ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲገነባ ቢሮው ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
ስልጠናው የፆታ ተኮር ጥቃት ምንነት፣ ዓይነቶች፣ መንስኤዎችና የመከላከል ስልቶችን በስፋት የዳሰሰ ሲሆን፣ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ የወሲብ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ በዝርዝር ተብራርቷል።
በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ለማስወገድ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመገንባት ያለመ ነው።
በስልጠናው በተለይም የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚያስከትለው ከፍተኛ የጤና፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ጉዳት በስፋት ተብራርቷል።
በአሚር ኑር ወረዳ ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች በሴቶችና ህፃናት ላይ የጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ በስልጠናው ተሳትፈው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና የፆታ ተኮር ጥቃቶችን ለማስወገድ በትብብር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
“በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ የሴቶችና የህፃናት መብት ሲከበር ጤናማና የተረጋጋ ማህበረሰብ ይገነባል።”
04/06/2026
የሐረሪ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በ“ሰቆጣ ቃልኪዳን ማስፋፊያ ፕሮጀክት” አማካኝነት በአባድር ወረዳ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና በፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን (GBV) ለመከላከል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ መፍቱሃ አልዪ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት ሴት ልጅ ግርዛት በሴቶች ላይ ከፍተኛ የጤና፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ጉዳት የሚያስከትል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት መሆኑን ገልፀው፣ በህግ የተከለከለና የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑን በማስገንዘብ ህብረተሰቡ ከእነዚህ ጎጂ ልማዶች እንዲርቅ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም ወ/ሮ መፍቱሃ አልዪ ተማሪዎች ከማንኛውም ዓይነት ጥቃትና ስጋት ነፃ በሆነ አካባቢ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲገነባ ቢሮው ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ስልጠናው የፆታ ተኮር ጥቃት ምንነት፣ ዓይነቶች፣ መንስኤዎችና የመከላከል ስልቶችን በስፋት የዳሰሰ ሲሆን፣ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ የወሲብ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ በዝርዝር ተብራርቷል።
በአባድር ወረዳ ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች የተወጣጡ የሴቶችና ህፃናት ጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ አባላት፣ በስልጠናው ተሳትፈው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና የፆታ ተኮር ጥቃቶችን ለማስወገድ በትብብር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
“በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ የሴቶችና የህፃናት መብት ሲከበር ጤናማና የተረጋጋ ማህበረሰብ ይገነባል።”
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያውያን በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርገዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
ጠቅላላ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁንም አመልክቷል።
አገልግሎቱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ሲል ገልጿል።
አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመላከተው፣ ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር መሆኗንና ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ እንደምትኮራ ገልጿል።
ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ ከመሻቷ በላይ እንደተሳካላትና ዛሬም የተደገመው ይኸው እንደሆነ አብራርቷል።
ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን ለመምረጥ እንዲሁም ሕገ-መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ለማስያዝ እንደምትሻ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም ማስፈለጉን አስታውቋል።
ለዚህ አገራዊ ጥሪ በምላሹ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው ቀኑን ሲጠባበቁ መቆየታቸውንና የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበልም በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ መዋላቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።
መራጮች ሌሊቱንም ጭምር አጋምሰው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫ ያደርገዋል ብሏል።
ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያልደረደሩት እንቅፋት እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር ባለመኖሩ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁንና ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ ማሸነፏን አረጋግጧል።
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ታቀርባለች ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።
02/06/2026
ኢትዮጵያ መርጣለች፣ ጸንታለች፣ አሸንፋለች