ሐረሪ ደንብ ማስከበር Harari Code Enforcement

ሐረሪ ደንብ ማስከበር Harari Code Enforcement

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሐረሪ ደንብ ማስከበር Harari Code Enforcement, Government Organization, Harar.

23/07/2024

የሀረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ምክንያት በዜጎች በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል ።

ፅ/ቤታችን በጉዳቱ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ የሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ይመኛል ።

23/06/2024
15/05/2024

ለግንዛቤ ያህል
// // // // // // // // //
በህገ መንግስቱ አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ እንደተቀመጠው “ሁሉም ሰዎች ንፁህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው” ይላል።

ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ መርዐ ግብሮች የተተገበሩ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን አለመንከባከብ ወይም ጉዳት ማድረስ ለዘርፉ የወጣውን ህግ አለማክበር በህግ ተጠያቂ እንደሚደርግ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ያመለክታል።

አንዳንድ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ጥረቶች ልማቱን የሚቀለብስ ጎጂ አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ በመሆናቸው፣ በአጠቃላይ አካባቢን መጠበቅ፣ በተለይም የሰውን ጤንነትና በጎ ሁኔታ እንደዚሁም የሕያዋንን ደሕንነትና የተፈጥሮን ሥነ-ውበት ማቆየት የሁሉም ተግባርና ኃላፊነት በመሆኑም ነው፡፡ የመከላከያ ወይም የማስወገጃ እርምጃዎችን በመውሰድ በማሕበራዊና በኢኮኖሚያዊ ልማት ጥረቶች ሂደት የሚከሰተውንና የማይፈለገውን ብክለት ማስወገድ ሳይቻል መከላከል ተገቢ በመሆኑ አዋጁ ሊወጣ ችሏል።

የኢፌዲሪ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ 300/1995 የብክለት ቁጥጥርን በተመለከተ በአንቀጽ 3 ን/አንቀጽ - ከ1-5 ያሰፈራቸው ድንጋጌዎች

1.ማንም ሰው ተገቢን የአካባቢ ደረጃ በመተላለፍ አካባቢን ሊበከል ወይም በሌላ ሰው በኩል እንዲበከል ሊያደርግ አይፈቀድለትም።

2. ሕግ በመተላለፍ ማንኛውንም በካይ ወደ አካባቢ በሚለቅ ሰው ላይ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት አስተዳደራዊ ወይም ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ ይችላል።

3.ብክለትን ወይም ሌላ አካባቢያዊ ጉዳትን ሊያስከትል በሚችል የተግባር መስክ የተሰማራ ማንም ሰው፣ የቆሻሻ መመንጨትን ለማስወገድ ወይም ወደ ተፈላጊው መጠን ለመቀነስ በባለሥልጣኑ ወይም በሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ትዕዛዝ መሠረት በተገቢ ቴክኖሎጂና ሲቻልም ቆሻሻን መልሶ በጥቅም ላይ ለማዋል በሚያስችሉ ዘዴዎች መጠቀም አለበት።

4.ብክለትን ያደረሰ ማንኛውም ሰው፣ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በሚወሰነው ሁኔታና የጊዜ ገደብ መሠረት አካባቢውን ማፅዳት፣ ወይም ለማፅጃ የወጣውን ወጪ መሸፈን አለበት።

5. በጤና ወይም በአካባቢ ላይ አደጋ እንዳያስከትል ከሚያሰጋ የሥራ እንቅስቃሴ ሊመጣ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ድርጅትን እስከ መዝጋት ወይም ወደ ሌላ ቦታ እስከ ማዛወር የሚደርስ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይችላል።

ብክለትን በሚመለከት ስለሚፈፀም ጥፋት በአዋጁ እንደተደነገገው አንድ የተፈጥሮ ሰው የዚህን አዋጅ ወይም በሥሩ የሚወጡትን ደንቦች በመተላለፍ በካይን ወደ አካባቢ በመልቀቅ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ፣ ከአንድ ሺህ ብር በማያንስና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከአንድ ዓመት በማያንስና ከአሥር ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።

ጥፋቱን የፈፀመው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ከሆነ ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከሃያ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፤ የሥራ ኃላፊውም ከአምስት ዓመት በማያንስና ከአስር ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ።

ሐረር ከተማን ፅዱ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በጋራ እንስራ !

Photos from Harar Municipality የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት's post 15/05/2024
በሐረር ከተማ እርሻቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ሲያነሱት የነበረው የመብት ጥያቄ ምላሽ አገኘ Etv | Ethiopia | News zena 14/05/2024

በሐረር ከተማ እርሻቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ሲያነሱት የነበረው የመብት ጥያቄ ምላሽ አገኘ Etv | Ethiopia | News zena በሐረር ከተማ ዲያስፖራ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ16 ዓመት በፊት ለቤቶች ልማት እርሻቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ሲያነሱት የነበረው የመብት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ተናገሩ፡...

Photos from Harari Government communication affairs Office's post 13/05/2024
Photos from Harari Mass Media Agency's post 10/05/2024
Want your business to be the top-listed Government Service in Harar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Harar