Munib Hay

Call Directions Contact the organization

Munib Hay Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Munib Hay, Harar.

23/10/2026

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ(ELMIS) Software በመጠቀም ህገወጥ የCOC ሰርተፍኬት የሰጡ ሃላፊዎች ከባድ የሙስና ጉድ

21/10/2026

እየተንሰራፈ ያለው የሙስና ጉድ

19/10/2026

ዜና አንባቢነኝ
ሰበር ዜና፡ በፈረንሳይ ፓሪስ ከፍተኛ ሁከት ተቀሰቀሰ!

በፓሪስ፤ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት፣ የደመወዝ፣ የጡረታ እና የህዝብ አገልግሎቶች ጉዳዮችን በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አደባባይ በመውጣታቸው ከፍተኛ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

በተለያዩ አካባቢዎች በተቃዋሚዎች እና በፖሊስ መካከል ግጭቶች መፈጠራቸው፣ የእንባ ጋዝ መተኮሱ፣ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው፣ ንብረት መውደሙ እንዲሁም ሰዎች መታሰራቸው ተዘግቧል።

ይህ አለመረጋጋት ስለ ህዝብ ደህንነት፣ ስለ ትራንስፖርት መስተጓጎል እና በአጠቃላይ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ስላለው ሁኔታ ስጋት ፈጥሯል።

🌍 እንደ ህዝባዊ ሰልፍ የጀመረው ይህ ክስተት፣ አሁን ለፈረንሳይ ባለስልጣናት ትልቅ ፈተና ሆኗል።

ሁኔታው እንዴት እንደሚያድግ በመከታተል ተጨማሪ መረጃዎችን እናቀርባለን።

#ፓሪስ #ፈረንሳይ #ሰበርዜና #ተቃውሞዎች #የአለምዜና

ወ/ሮ ባንቺአለም አሰፋ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል‎‎ሀረር ፣ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም— የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ‎የቢሮው የ...
19/10/2026

ወ/ሮ ባንቺአለም አሰፋ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል

‎‎ሀረር ፣ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም— የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ
‎የቢሮው የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ወ/ሮ ባንቺአለም አሰፋ በማድረግ ሹመዋል

🦅 intelligence
12/10/2026

🦅 intelligence

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሰንደቃችን የሚወክላቸውን እሴቶች በተግባር በማሳየት ሊሆን ይገባል - የሀረር ከተማ ነዋሪዎችሀረር፣ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም  የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ...
12/10/2026

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሰንደቃችን የሚወክላቸውን እሴቶች በተግባር በማሳየት ሊሆን ይገባል - የሀረር ከተማ ነዋሪዎች

ሀረር፣ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሰንደቃችን የሚወክላቸውን የነፃነት፣ የአንድነት፣ የሰላምና የሀገር ክብር እሴቶች በተግባር ማሳየት እንደሚገባ የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

በሀረሪ ክልል 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተከብሯል።

የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ዕለቱን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ቀደምት አባቶች በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኘውን ነፃነት ለመጠበቅና ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትን ለማጎልበት ያለንን ቁርጠኝነት የምናድስበት ዕለት ነው ብለዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ ሰንደቅ ዓላማ የቀለማት ውህደት ብቻ ሳይሆን የጋራ ታሪክ፣ የሕዝብ ክብር፣ የሀገር ማንነትና የነፃነት ምልክት ነው።

ዕለቱን ስናከብር ሰንደቃችንን በክብር ከፍ አድርጎ ከማውለብለብ ባለፈ የሚወክላቸውን እሴቶች በዕለት ተዕለት ተግባር ማሳየት ይጠይቃል።

በመሆኑም ለሀገር በመቆም፣ ለሕግ በመገዛት፣ የሌሎችን መብት በማክበር፣ ሰላምን በማጠናከርና ለልማት በጋራ በመስራት ሊሆን ይገባል።

ከእያንዳንዱ ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ በትጋትና በኃላፊነት በመስራት ለሀገር ልማት፣ሉዓላዊነትና ለጋራ ብልፅግና የድርሻውን መወጣት ይጠቅበታል።

በመሆኑም እንደዜጋ በተሰማራበንት መስክ ለለውጥና ለስኬት ጠንክረን በመስራት የሀገራችንን ክብርና ታላቅነት ለማስጠበቅ እንሰራለን ብለዋል።

አቦከር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎችና ወላጆች ጋር በውጤት ማሻሻልና በስነ-ምግባር ዙሪያ  ውይይት አካሄዷል።‎‎ሀረር ፣ መስከረም 30/2019 ዓ.ም በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የአቦ...
10/10/2026

አቦከር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎችና ወላጆች ጋር በውጤት ማሻሻልና በስነ-ምግባር ዙሪያ ውይይት አካሄዷል።
‎
‎ሀረር ፣ መስከረም 30/2019 ዓ.ም በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የአቦከር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎችና ወላጆች ጋር በውጤት ማሻሻልና በስነ-ምግባር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
‎
‎የአቦከር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች፣ ከወላጆችና ከመምህራን ጋር በትምህርት ቤት ደንቦች መከበርና የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ዙሪያ ሰፊና ውጤታማ ውይይት አካሄዷል።
‎
‎በመድረኩ ላይ የወላጆች የቅርብ ክትትልና የትምህርት ቤቱ ደንቦች መከበር ለተማሪዎች ሁለንተናዊ ስኬትና ውጤታማነት ያለውን ወሳኝ ሚና በስፋት ተመላክቷል።
‎
‎ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን የሥነ ምግባር መመሪያ በአግባቡ በማክበር፣ በትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎችን በጥብቅ እንድከታታሉ ጥሪ ቀርቧል።
‎
‎በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤቱ አመራሮች በሙሉ ተገኝተው የነቃ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፥ ለተማሪዎች ስኬት በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል።
‎

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰራተኞቻቸው ጋር ውይይት ስነ ስርዓት ባደረጉበት ወቅት ካነሷቸው ሃሳቦች ውስጥ:-የትምህርት ዘርፉን ለመለወጥ ያሉብንን ችግሮች ጥልቀት በሚገባ መረ...
09/10/2026

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰራተኞቻቸው ጋር ውይይት ስነ ስርዓት ባደረጉበት ወቅት ካነሷቸው ሃሳቦች ውስጥ:-

የትምህርት ዘርፉን ለመለወጥ ያሉብንን ችግሮች ጥልቀት በሚገባ መረዳት ይኖርብናል፤

በቅድሚያ ሁላችንም ይህ ተቋም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገልገል የተቋቋመ ተቋም ነው ብለን እናስብ፤

ከአሁን በኋላ በተቋሙ የሚያስፈልገው ቅንነት ብቻ ነው፤

ሁላችንም እዚህ መስሪያ ቤት ስንመጣ ፖለቲካችንን ትተን ተቋሙ የተቋቋመበትን አላማ ውጤትን ለማሻሻል ለማሣካት የሚያስችል ምንም አይነት የፖለቲካ አቋም ቢኖርህ ለዚህ መስሪያ ቤት የሚፈይደው ነገር የለም

ብሄርና ዘር የሚለውን ጉዳይ ቤታችሁ ትታችሁ ኑ

ከሁላችንም የሚጠበቀው ሀላፊነት ነው

በብሄሬ፣ በጎሳየ ወይንም በፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊነቴ ተጠግቼ ይህንን ላገኝ እችላለሁ ማለት በፍፁም አይሰራም

የትምህርት ሴክተሩ የፖለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፖሊቲካ አመለካከታችንን ትተን እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ካቢኔ አባላትን ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቋልክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ...
08/10/2026

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩዎች
ካቢኔ አባላትን ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቋል

ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ‎የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በድጋሚ ተሹመዋል
‎እንኳን ደስ አሎት

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እንዲያገለግሉ በድጋሚ ተሹመዋልክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተ...
08/10/2026

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እንዲያገለግሉ በድጋሚ ተሹመዋል

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል

በዚሁ መሰረት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ አቅርበዋል

ምክር ቤቱ በክቡር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረበውን የሹመት ጥያቄ መሠረት በማድረግ፣ ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እንዲያገለግሉ ሹመት አጽድቋል

Address

Harar

Telephone

+251915736636

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Munib Hay posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Munib Hay:

Shortcuts

Share