Harari environmental protection authority

Directions

Harari environmental protection authority ዘለቄታዊ የአካባቢ ጥበቃን ባማረጋገጥ አሉታዊ የአካባቢ ተፅ?

03/10/2026
ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ !Clean Ethiopia for Generation ! የፅዳት ዘመቻ 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ! የመስከረም ወር 4ኛ   ሳምንት የአካባቢ የፅዳት ዘ...
03/10/2026

ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ !Clean Ethiopia for Generation ! የፅዳት ዘመቻ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ! የመስከረም ወር 4ኛ ሳምንት የአካባቢ የፅዳት ዘመቻ በዛሬው እለት የባለስልጣኑ ሰራተኞች በማለዳ በመሰባሰብ የባለስልጣኑ ቅጥር ግቢ እና አካባቢው ላይ የፅዳት ዘመቻ አከናወኑ ::

በ3ኛው ዙር የተጀመረውን ፅዱ ኢትዮጵያ ለትልድ ! በሚል መሪ ቃል መስከረም ወር የሚደረገውን የድምፅ ብክለትን ቅነሳበማስመልከት የባለስልጣኑ ሰራተኞች በየሳምንቱ የሚያደርጉትን የአካባቢ የማፅዳት ዘመቻ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና ለህብረተሰቡ የድምፅ ብክለት የደረቅ ቆሻሻ አደገኛ ኬሚካሎችና የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ እያስከተለ ያለውን ከፍተና የጤና ችግር ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዋች ተጠናክሮ እንደሚቀጥ ገልፀዋል ::

መስከረም/23/2019

የሀረሪ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

# ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ
# ፅዱ ሐረር ለትውልድ
# ይቀላቀሉን
# ምድራችንን ከፕላስቲክ ብክለት እንከላከል!

👇
ሊንኩን በመጫን የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን::
🤳ለማንኛውም ጥቆማ አስተያየት እንዲሁም ቅሬታ

☎️7329 አጭር መስመር ይደውሉ !

https://www.facebook.com/HARARIEPA?mibextid=LQQJ4d
https://t.me/HarariEnvirometalProtactionAuthority

02/10/2026

የክልሉን ህዝብና መንግስት ዳግም በአመራርነት ለማገልገል ዕድል በማግኘቴ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ" አቶ ኦርዲን በድሪ

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉን ህዝብና መንግስት በርዕሰ መስተዳድርነት ለማገልገል ድጋሚ በክልሉ ምክር ቤት የተሰየሙ መሆኑን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው እንደገለፁት ይህን ታላቅ የህዝብ አደራ እና ሀላፊነት በሙሉ ፈቃደኝነት የተቀበልኩት፣ ለታሪካዊቷ እና ለሰላም፣ የፍቅርና የመቻቻል ምሳሌ ለሆነችው ክልላችን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል ካለኝ ቁርጠኝነት በመነሳት ነው ብለዋል።

በመጪዎቹ ጊዜያት የክልላችንን የሰላም፣ የልማት፣ እና የመልካም አስተዳደር እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፤ እንዲሁም የወጣቶቻችንን እና የሴቶቻችንን ተሳትፎ በማጎልበት የሁሉም ድምፅ የሚሰማበትን አሰራር ለመዘርጋት ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ሀረሪ ክልል የጋራ መኖሪያችን፣ የታሪካችን እና የማንነታችን መገለጫ ናት ሲሉ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ የጀመርነውን የእድገት ጉዞ ዳር ለማድረስ እና ክልላችንን የበለጠ ለማበልጸግ የሁሉም ትብብር እና ድጋፍ እንዲጠናከር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

✍️ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

02/10/2026

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከመስከረም 22/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ

በዚሁ መሠረት፦

1ኛ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ ቴክኒክና ሞያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ

2ኛ ወ/ሮ ፈቲያ ሳኒ የሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ

3ኛ ወ/ሮ ፈሪሃ መሀመድ የሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን

4ኛ አቶ ታመነ ፍቃድ የብቃት ማረጋገጫ ማዕከል ኃላፊ

5ኛ አቶ ረኢስ ዩሱፍ የሀረር ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ

6ኛ ኤልያስ ዩኒስ የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ኃላፊ

7ኛ ዶ/ር አብዱልሀኪም ኢምራን ጀጎል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ

8ኛ ወ/ሮ ሙና ኢስሀቅ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ባለስልጣን ኃላፊ

9ኛ አቶ ሰሚር አብዱላሂ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ

10ኛ አቶ አብዱልሀፊዝ አህመድ የሀረሪ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ኃላፊ

11ኛ አቶ ኤልያስ አብዱረህማን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ

12ኛ አቶ አብዱልሀኪም አብዱማሊክ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ አደረጃጀት ጉዳይ አማካሪ

13ኛ አቶ ኃይለጊዮርጊስ መገርሣ የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari environmental protection authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share