30/09/2022
የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ለሀኪም ወረዳ መስተዳድር አራተኛ ጤና ጣቢያ ከግማሽ ሚሊዬን በላይ የሚገመት የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።
የሀኪም ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በቦታው በመገኘት የተደረገውን ድጋፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ እጅ በተቀበሉበት ወቅት ለተደረገው ድጋፍ የክልሉን ጤና ቢሮ በራሳቸውና በወረዳው ስም አመስግነዋል።
19/09/2022
Congra Hakim Woreda Arategna Health center👌
02/09/2022
👉 ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን!!
"በሀኪም ወረዳ መስተዳድር ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም በወረዳ ደረጃ የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ስላለን ጧት ከ2:30 ጀምሮ ሀኪም ወረዳ መስተዳድር ቅጥር-ግቢ ፍቃደኞችን በማስተባበር ደማችንን እንለግሳለን።"
በጎ ፈቃደኞች ከወዲሁ ጥሪ ተደርጎላቿል!!
አቶ ቶፊቅ መሀመድ የሀኪም ወረዳ ዋና አስተዳደሪ
09/08/2022
በ2015 በጀት ዓመት በጤናዉ ዘርፍ የህብረተሰቡን እርካታ ይበልጥ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የጤናው ዘርፍ የ2014 ዓ.ም እቅድ አፋፃፀም ግምገማ በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በመድረኩ የጤናው ዘርፍ የ2014 ዓ.ም እቅድ አፋፃፀም ሪፖርት እና የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ቀርቦ መልካም አፈጻጸሞችን ማጠናከርና የአፈጻጸም ውስንነት የተገኘባቸው ስራዎች ላይ የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል።
በመጨረሻም የ2015 ዓ.ም የጤናው ዘርፍ ዕቅድን ከሁሉም ወረዳ አስተዳደሮች ጋር የስምምነት ውል በመፈራረም የግምገማ መድረክ ተጠናቋል።
በቀጣይም የሐኪም ወረዳ መስተዳድር ወደጤና ጣቢያው ብሎም እስከ ጤና ኬላ ድረስ በማውረድ በእቅዱ መሰረት መስራት እንዳለበትም ተጠቁሟል።
24/06/2022
በዛሬው ቀን 17/10/14/ በሐኪም ወረዳ አራተኛ ጤናጣቢያ የጽዳት ዘመቻ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ተከናወነ። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የወረዳ ጤና ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኦሪት አህመድ እና የቀበሌ አመራሮች አመራሮች በተገኙበት ከሴፍቲ ኔት ሰራተኞች እና የአራተኛ ጤና ጣቢያ ባለሞያዎች በጋራ በመሆን የጽዳት ዘመቻ አከናውነዋል። ዘመቻዉ በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።
23/06/2022
#የሐኪም ወረዳ ጤና_ሴክተር_የእውቅና_ሽልማት_አገኘ💻👏።
አረንጓዴ አሻራ ለጤናችን በሚል መሪ ቃል 4ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማብሰሪያ ስነ-ስርዕት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዉስጥ ተካሄደ።
በዝግጁቱ ላይ የሐኪም ወረዳ ጤና ሴክተር በ3ተኛው ዙር የኮቪድ ክትባት ዘመቻ 100% በላይ አፈፃፀም በማስመዝገቡ የእውቅና እና የማበረታቻ Laptop ሽልማት ተበረከተ።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ቶፊቅ መሀመድ የጤና ሴክተሩ በክትባት ዘመቻው ባስመዘገበው አመርቂ ውጤት መደሰታቸውን በመግለፅ፣መሰል የእቅድ አፈፃፀም ውጤት በሁሉም ዘርፎች ለመድገም የዘርፍ ሀላፊዎች ከሰራተኞች ጋር በመቀናጀት በትጋት መስራት ይገባል አሉ።
የወረዳው ጤና ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኦሪት አህመድ የተገኘው የእውቅና እና ሽልማት ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ውጤት የተሰጠ እውቅና መሆኑን በመጥቀስ በዘመቻው ለተሳተፉ በሙሉ ምስጋናቸውን አቀረቡ።
13/05/2022
ቀን 05/09/14
ከጤና ቢሮ ከወረዳና ከተለያዩ የጤና ተቋማት በተወጣጡ ባለሞያዎች በአራተኛ ጤና ጣቢያ የአፍላ ወጣቶች ክፍል ላይ ጉብኝትና ልምድ ልውውጥ በማድረግ እንዲሁም ከጤና ቢሮ በመጡ ባለሞያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተሰጥቷል
30/03/2022
በሐኪም ወረዳ አራተኛ ጤና ጣቢያ Water aid project ከ Heineken ጋር በመተባበር ለተቋሙ የእጅ መታጠብያ ቦታ ለተገልጋይ በተለይም ለዊልቸር ተጠቃሚዎች በሚመች እና ባማረ መልኩ በመስራት ዛሬ ቀን 21/07/14 በምክትል ጤና ቢሮ ሐላፊ የተመራ ቡድን ከ water aid project እና Heineken አባላቶች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቋል። ይህንን ያማረ የመታጠብያ ስፍራ ለሰሩ ባለድርሻ አካላት ምስጋና በማቅረብ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።