30/05/2026
የሐረሪ እና የምስራቅ ሐረርጌ ማረሚያ ተቋማት ከሕግ ታራሚዎች ጋር ልዩ የውይይት መድረክ አካሄዱ።
ሐረር፤ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና የምሥራቅ ሐረርጌ ማረሚያ ቤት ተልዕኮና አቅማቸውን በማቀናጀት፣ ከሕግ ታራሚዎች ጋር ያለውን የወንድማማችነትና የአብሮነት እሴት አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ የሚያጠነጥን ልዩ የውይይት መድረክ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በጋራ አካሂደዋል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ፤ ሐረር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር ታሪካዊ እሴት የምትታወቅ ከተማ መሆኗን አስታውሰው፣ ይህ በጎ መገለጫ በማረሚያ ቤቱም ውስጥ በተግባር እየታየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በከተማዋ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የሁለቱ ክልሎች ሕግ ታራሚዎች በወንድማማችነትና በሰላም በጋራ የሚኖሩበት በመሆኑ፣ ተቋሙን በሀገሪቱ ካሉ መሰል ተቋማት መካከል ብቸኛና ልዩ ተምሳሌት እንደሚያደርገው በልበ ሙሉነት አስገንዝበዋል። የምስራቅ ሐረርጌ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ከማል ገናም በበኩላቸው፣ ይህንን መልካም አንድነት ይበልጥ በማጠናከር በጋራና በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ኮሚሽነር አድናን አህመድ በማጠቃለያ ንግግራቸው የሁለቱን ተቋማት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ በተለይም የሁለቱን ተቋማት ተልዕኮ በማቀናጀት ታራሚዎችን የማረም፣ የማነፅና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ የመቀላቀል ሂደትን ውጤታማ ለማድረግ አቅሞችን በትብብርና በቅንጅት ማስተባበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉት የሕግ ታራሚዎች በበኩላቸው፣ የተጀመሩ የልማትና የማሻሻያ ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ ፍላጎታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በሁለቱ ክልሎች ታራሚዎች መካከል ያለውን የሰላምና የአብሮነት ልዩ እሴት ጠብቀው ለማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ በቁርጠኝነት እንደሚወጡ በሙሉ እምነት አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፦ኮማንደር ማህዲ
27/05/2026
በሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በድምቀት ተከበረ
የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን 1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን በኮሚሽኑ ግቢ ውስጥ በሚገኙ ታራሚዎች ዘንድ በድምቀት አክብሯል።
በማረሚያ ቤቱ ግቢ በተዘጋጀው ቦታ ታራሚዎች የኢድ አል-አድሃ የጋራ ሶላትን በሰላም የሰገዱ ሲሆን፣ በዓሉ የተስፋ፣ የመተሳሰብ እና የለውጥ መነሳሳት እንዲሆን ተመኝተዋል።
አንድን ኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ እና ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች በበዓሉ ወቅት ለታራሚዎች መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ታራሚዎች በሚገኙበት ማረሚያ ቤት በዓሉን በሰላም እና በመተሳሰብ እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክ ኮማንደር መህዲ መሀመድ እንደገለጸው፣ ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች የሃይማኖት በዓላትን በነጻነት እንዲያከብሩ ማመቻቸቱ፣ የታራሚዎችን ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ ለማሻሻል እና ለማረም ትልቅ ሚና ይጫወታል። በዓሉ በምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር ሳይታጀብ በሰላም መጠናቀቁንም ለማወቅ ተችሏል።
የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
26/05/2026
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት የማረሚያ ፖሊስ አባሎችን ያሳተፈ በጋራ ስልታዊ ዕቅድ ላይ ተወያዩ
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም | ሐረር
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት፣ የማረሚያ ፖሊስ አባላትን ባሳተፈ መልኩ በተዘጋጀ የጋራ ስልታዊ ዕቅድ ዙሪያ ሰፊ የማኔጅመንት ውይይት አካሄዱ። መድረኩ በዋነኛነት ተቋማዊ ደህንነትን ይበልጥ በማጠናከር እና በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሂደት ዙሪያ የፖሊስ አባላቱን አቅምና ስምሪት በተቀናጀ መልኩ መጠቀም በሚያስችሉ ስልታዊ ስራዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ገለጻ፤ ሀገራዊ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁለቱም ተቋማት የማረሚያ ፖሊስ አባላትና አመራሩ በተቀናጀ ስምሪትና መረጃ የመለዋወጥ ቁርጠኝነት ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ተቋማዊ የጥበቃና ደህንነት ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማናቸውንም የጸጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እና የጋራ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መላው አባል የሚሳተፍበት ስልታዊ ዕቅድ መዘጋጀቱ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ ይህ የጋራ ስልታዊ ዕቅድ የሁለቱንም ተቋማት የደህንነት መዋቅር ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እና ለአባላቱ ግልጽ የሆነ የተልዕኮ አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ የውይይቱን አስፈላጊነት አስረድተዋል።
በዚህም መሰረት፤ በሁለቱም ተቋማት የሚገኙ የማረሚያ ፖሊስ አባላትን በአግባቡ በማሳተፍ እና ሙሉ ዝግጁነታቸውን በማረጋገጥ፣ በዕቅድ መሰረት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርግ የጋራ የደህንነት ግብረ-ሃይል በይፋ መቋቋሙ ተገልጿል።
በስብሰባው ላይ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ከማል ገናን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፤ የተቀናጀው ግብረ-ሃይል የአባላቱን ስምሪትና የቀጠና ድልድል በአግባቡ በመምራት፣ የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየዕለቱ የደህንነት ክትትልና የመረጃ ልውውጥ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እንደሚያከናውን በስብሰባው ላይ ተረጋግጧል።
ኮሚሽነር አድናን አህመድ ለመድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት መመሪያ፤ የተቋማቱ ዋነኛ ተልዕኮ የህዝብንና የሀገርን ሰላም በማረጋገጥ፣ ታራሚዎችን አርሞና አንጾ ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀል መሆኑን አስታውሰው፣ ለዚህ የጋራ ተልዕኮ ስኬት አመራሩና መላው የሁለቱ ተቋማት የፖሊስ አባላት በአብሮነትና በወንድማማችነት መንፈስ ሊቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ የጋራ ስልታዊ ዕቅድም እንደካሁን ቀደሙ ሁሉ በላቀ ትጋት፣ በጽኑ ቁርጠኝነት እና በታላቅ ፖሊሳዊ ስነ-ምግባር በተግባር ላይ እንዲውል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ኮሚሽነር አድናን አህመድ እና ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች "እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ" በማለት፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የተቋማዊ አንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ኮማንደር ማህዲ
24/05/2026
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የጋራ ስልታዊ ዕቅድ አጸደቁ
ሐረር — ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና የማናጅመንት አባላት የተሳተፉበት ስኬታማ የጋራ መድረክ በማረሚያ ኮሚሽኑ አዳራሽ ተካሄደ። በሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አድናን አህመድ ሰብሳቢነት በተመራው በዚህ ስብሰባ ላይ፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል የነበሩ የተናጠል አካሄዶችን በማስቀረትና 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስልታዊ ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ሁለቱ ተቋማት የሕግ ታራሚዎችን ሰላም ለመጠበቅና በማነፅ ረገድ የቆየውን የወንድማማችነት አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር፣ እጅግ ወሳኝ በሆነው የምርጫ ወቅት የተቀናጀ የጥበቃ ሥርዓት ለመዘርጋት ሙሉ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በዚህም መሠረት በኮማንደር ኃይሉ በቀለ የቀረበውና ከምርጫው በፊት፣ በዕለቱ እና ከምርጫው ማግስት ያለውን የተቋማት ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችለው የጋራ ፀጥታ ግብረ-ኃይል ዕቅድ ጠቃሚ ግብዓቶች ተካተውበት በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የተመረጡት አጀንዳዎች ወቅታዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቀ መሆኑን ገልጸው፣ የተጣለባቸውን ታሪካዊና ሙያዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም የውይይቱ ሰብሳቢ ኮሚሽነር አድናን አህመድ ባስተላለፉት የሥራ መመሪያ፤ የተያዘው የጋራ ስልታዊ ዕቅድ በወረቀት ላይ ብቻ ሳይወሰን መሬት ላይ ጠንካራ ውጤት እንዲያመጣ ቀጣይነት ያለው የሪፖርት፣ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት አሳስበዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም፣ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሰላም ለማጠናቀቅ የአመራሩና የፈጻሚው አካል ቅንጅት፣ ቁርጠኝነትና የጋራ ኃላፊነት መወጣት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን በማጉላት መድረኩን በስኬት አጠናቀዋል።
ዘጋቢ፦ ኮማንደር ማህዲ
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም
22/05/2026
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የ7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሂደት ለማስቀጠልና አሁን ያለውን ዝግጁነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ስልታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
(ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም)፦
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች፣ አስተባባሪዎችና መላው የፖሊስ አባላት በተገኙበት፣ የወቅቱን ቀጣይ የጸጥታ ሁኔታዎች ለመገምገም የሚያስችል ወሳኝ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በኮሚሽነር አድናን አህመድ መድረኩ በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2018 ዓ.ም የምታካሂደውን 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ፣ በማረሚያ ተቋማት አሁኑ ወቅት በአስተማማኝ ሁኔታ ይህንን አሁን ያለውን አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችል አገራዊ፣ ክልላዊና ተቋማዊ የጥንቃቄ ቅድመ-ዝግጅት ይበልጥ ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ተቋሙ የጣለበትን ህገ-መንግስታዊ አደራ በላቀ ዝግጁነት ለመወጣትና የህግ የበላይነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር አሁን ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል እጅግ ወሳኝ መሆኑም በመድረኩ መክፈቻ ላይ በስፋት ተነስቷል።
በዕለቱ በኮማንደር ዋሴ ካሳ የቀረበው ስልታዊ የመወያያ ሰነድ፥ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ታሪክ ያላቸውን የዓለማችን ያደጉና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመዳሰስ፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ በዝርዝር አሳይቷል።
በተለይም ሽንፈትን ለመቀበል በሚቸገሩ አስቀድሞ በዕቅድ ላይ በተመሰረተ አስቀድሞ መከላከልና ማክሸፍ የጸጥታ ተቋማት ዋነኛ ኃላፊነት መሆኑን የጠቆመው ይኸው ሰነድ፤ በአሁኑ ወቅት በክልላችን ያለው ይህንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ የጸጥታ ስልቶችን በተግባር በመተርጎም አሁን ያለውን ሰላም ሳያቋርጡ ለማስቀጠል የሚያስችል የጋራ ግንዛቤና የተደራጀ ተቋማዊ አቅም መገንባቱን አመልክቷል።
በቀረበው ስልታዊ ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ዙሪያ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዲላሂ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ አሁን በክልሉና በተቋሙ ያለውን የተረጋጋ ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠልና አነስተኛውን የስጋት ደረጃ ሙሉ በሙሉ ወደ ዜሮ ለማውረድ የአባላቱ ንቁ ተሳትፎና ሚስጥር የመጠበቅ ኃላፊነት የማይተካ ሚና እንዳለው አሳስበዋል።
በመጨረሻም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ ለተነሱ ጥያቄዎች አጠቃላይ ማብራሪያና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሰጡ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን ሰላማዊ ድባብ በቁርጠኝነት ለማስቀጠልና እያንዳንዱ የፖሊስ አባልና አመራር የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥና የተጣለበትን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በከፍተኛ ስነ-ምግባርና ዝግጁነት የመወጣት ግዴታ እንዳለበት ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል።
ይህ መመሪያም ኮሚሽኑ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ አሁን ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ለማስቀጠል ያለውን ዝግጁነት ያረጋገጠ ሆኗል።
በተያያዘም፣ የኮሚሽኑ ተቋማዊ አዲስ መዋቅር ማሻሻያ ረቂቅ ጥናት እንዲያዘጋጅ በሚቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ የፖሊስ አባላቱን ሚወክሉ ሁለት ተወካዮች ሙሉ ተሳትፎና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠዋል።
በአጠቃላይ መድረኩ በአሁኑ ወቅት የአባላትን የጋራ ዝግጁነት ይበልጥ በማጠናከር፣ የተቋማዊ መረጃዎችን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅና አሁን ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተግባራዊና ስልታዊ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቋል።
18/05/2026
በሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለሲቪል ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ
ዛሬ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም በሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የለውጥ እና መልካም አስተዳደር ተጠሪ አማካኝነት ለሲቪል ሠራተኞች የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በኮሚሽኑ አዳራሽ ተሰጥቷል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሲቪል ሠራተኛውን አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ሰልጣኞቹ ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ለኮሚሽኑ አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በኮማንደር መሐመድ አሚር እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ሥልጠና፣ ሰልጣኞቹ ያገኙትን የለውጥ መሣሪያዎች አተገባበር ዕውቀት በኮሚሽኑ መልሰው ለሌሎች ሠራተኞች ማካፈልና ማሰልጠን በሚችሉበት የክህሎት ደረጃ ላይ ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ኮሚሽነር አድናን አህመድ አክለውም ሥልጠናው በዋናነት በቢሮክራሲያዊ ሰንሰለት የሚባክን ጊዜን በመቀነስ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት ለተገልጋዮች ተደራሽ ለማድረግ የተወለመ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አዲሱ የሪፎርም አሠራር በሠራተኛው ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ላይ ያተኮረ የብቃት ሥራ አመራርን (Competency Management) የሚያሰፍን ሲሆን፣ የክህሎት ክፍተቶች በሥልጠና እንዲሞሉና ሥራ በተጨባጭ የውጤታማነት ልኬት እንዲመዘን ያደርጋል።
በተጨማሪም የሠራተኞች ስምሪትና ዕድገት ከማንኛውም የፖለቲካና የዘመድ አዝማድ ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መልኩ፣ በችሎታ ላይ ብቻ (Merit-based) እና የሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ባረጋገጠ በአካታችነት መርህ እንደሚመራ ገልጸዋል።
በማጠቃለያውም፣ የሲቪል ሠራተኛው የሥራ ውጤት ምዘና ከድሮው አሠራር ወጥቶ እያንዳንዱ ሠራተኛ ከኮሚሽኑ ዓመታዊ ዕቅድ የተቀዳ የራሱ የሥራ ዕቅድ እንዲኖረው ተደርጓል።
ምዘናው ቀጣይነት ባለው መልኩ በየወቅቱ ግብረ-መልስ የሚሰጥበት ሲሆን፣ ከፍተኛ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ሠራተኞች ደግሞ የዕውቅናና የማበረታቻ የሽልማት ሥርዓት ይዘረጋል።
ኮሚሽነር አድናን አህመድ ይህ የሪፎርም ጉዞ ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ሠራተኛ አዲሱን አሠራር በሙሉ ልብ ተቀብሎ ለተቋሙ ዕድገት የራሱን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሥልጠናው "በእውቀትና በክህሎት የታነጸ ሲቪል ሰርቫንት ለተቋማዊ ስኬት መሠረት ነው!" በሚል መሪ ቃል ተጠናቋል።
ዘጋቢ፦ ኮማንደር ማህዲ
ግንቦት 10/2018 ዓ.ም
18/05/2026
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ ሪፎርምን የሚያፋጥኑ ወሳኝ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የጋራ የውይይት መድረኩን አጠናቀቀ
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ያሉትን ችግሮች በአዎንታዊ አስተሳሰብ ወደ መልካም አጋጣሚዎች ለመቀየር ያለመ ታሪካዊና ስልታዊ የጋራ የውይይት መድረክ አካሄደ።
በኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ በዚህ ስብሰባ ላይ፤ የኮሚሽኑ ማናጅመንት አባላት፣ አስተባባሪዎችና መመሪያ አርቃቂ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ኮሚሽነሩ ባስተላለፉት መሪ ቃል፣ አመራሩ ችግሮችን ወደ ውጭ ከማላከክ ወጥቶ ውስጣዊ አቅምን በመፈተሽ ለላቀ ተቋማዊ ስኬት በአዲስ መንፈስ መነሳት እንዳለበት በጥብቅ አሳስበዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎቹ በቀረቡት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ሙሉ በሙሉ በመግባባት የጋራ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።
በዚህም መሠረት እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚጠናቀቁ አንገብጋቢ የድርጊት መርሃ-ግብርና የዘገዩ የ9 ወራት ቀሪ ሥራዎች በልዩ ትኩረት እንዲፈጸሙ፣ የጥበቃ አባላትን ለማጠናከር የተረቀቁ የማበረታቻ መመሪያዎች በአስቸኳይ ጽድቀው ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲላኩ እንዲሁም ተቋማዊ ጥበቃን በቴክኖሎጂ ለማገዝ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የሚደረገው የሬዲዮ መገናኛ ፍላጎት መጠን ተወስኖ ይፋዊ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ በጋራ ተወስኗል።
በተጨማሪም በግንባታ ላይ የተሳተፉ አባላትና ታራሚዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ሥልጠናና ፈተና እንዲያገኙ፣ የ2019 ዓ.ም የይቅርታ ዝግጅት ሥራዎች አሁኑኑ በኮሚቴ ተዋቅረው እንዲጀመሩና የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ ዕቅድ ውጤት ተኮር በሆነ መልኩ እንዲደለደል ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 7 የተደረገውን አጠቃላይ ግምገማ መሠረት በማድረግም፣ የላቀ አፈጻጸም ላላቸው እውቅና ለመስጠት፣ የስነ-ምግባር ጉድለት ባለባቸው ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈንና ዕቅድ ለሌላቸው አባላት ልዩ ሥልጠና ለመስጠት በጋራ ተወሳኝ አቅጣጫ ተቀምጧል። መድረኩ "አንድነታችንና ቁርጠኝነታችን ለስኬታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ቃል በጥብቅ የኃላፊነት ስሜት ተጠናቋል።
16/05/2026
የሐረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አገልግሎቱን ወረቀት አልባ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተስማማ
የሐረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመደገፍ፣ አሠራሩን ለማዘመንና ሙሉ በሙሉ ወደ ወረቀት አልባ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚያስችለውን ፍሬያማ የሥራ ውይይት ከኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር አካሂዷል።
ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገው በዚህ የጋራ መድረክ ላይ፣ የተቋማዊ ትስስርንና የሥራ ቅልጥፍናን ለማሳደግ በሚያስችሉ ዘመናዊ የዲጂታል መፍትሔዎች (Digital Solutions) ላይ በዝርዝር መክክር ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የኮሚሽኑን የውስጥ ደህንነት፣ የኮሙኒኬሽንና የሀብት አስተዳደር ሥርዓት ለማዘመን ቃል የተገባላቸው በርካታ የቴክኖሎጂ አማራጮች ቀርበዋል።
ከእነዚህም መካከል የደንበኞች አገልግሎት ፍሰትን የሚያቀላጥፈው Tele Contact Center፣ የውስጥ ስብሰባዎችንና ውይይቶችን በዲጂታል አማራጭ በማድረግ የሥራ ፍጥነትን የሚጨምረው Tele Meet እና የተቋሙን የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር በቴክኖሎጂ ለማዕከላዊነት ለመምራት የሚያስችለው Tele ERP በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።
በተጨማሪም የኮሚሽኑን የጸጥታና ደህንነት ክትትል ይበልጥ ለማጠናከር Digital PTT/PTV የተሰኙ የድምፅና ምስል የታገዙ የሬዲዮ ኮሙኒኬሽኖች፣ ዘመናዊ የቪዲዮ ክትትል ሥርዓት (Video Management System) እና የተሽከርካሪዎችን ስምሪት ለመቆጣጠር የሚያስችል Fleet Management System በጋራ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። እነዚህ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች የተቋሙን የዕለት ተዕለት ኦፕሬሽንና የደህንነት ቁጥጥር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩታል ተብሏል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገሪቱ ትኩረት የሰጠችበትን «የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025» መርሃ-ግብር በተጨባጭ እውን ለማድረግ በእያንዳንዱ ተቋም ውስጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማረጋገጥ የግድ መሆኑን አሳስበዋል።
ኮሚሽኑ በቅርቡ ካካሄደው አጠቃላይ የአፈጻጸም ግምገማ የለየውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት ለመሙላትና አሠራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ከሐረሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። አክለውም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተጀመሩትን የቴክኖሎጂ ትግበራዎች በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂዎች ከሁለቱም ተቋማት ጋር በቅርብ ቅንጅት በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ዘገቢ፦ኮማንደር ማህዲ
ግንቦት 8 / 2018 ዓ.ም
16/05/2026
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጥልቅ የግምገማ መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ
የሐረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ ሪፎርምን ለማፋጠንና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ከሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለት ምዕራፎች ከፍሎ ሲያካሂድ የቆየው ጥልቅ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ በተቀመጠለት ዕቅድ መሠረት በዛሬው ዕለት ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም. በስኬት ተጠናቋል።
ይህ መድረክ ከመጀመሪያው ዙር የመላው አባላት ተሳትፎ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ዙር የአመራርና የፖሊስ አባላት ግምገማ ድረስ፣ እያንዳንዱ አካል "በሠራው ልክ" የሚመዘንበት ጥብቅ የተጠያቂነት ሥርዓት የሰፈነበት ነበር።
ይህም የተቋሙን የማረምና የማነፅ ተልዕኮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።
የግምገማው ዋና አስፈላጊነትና ዓላማ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት፣ ተደጋጋሚ ወንጀል ፈጻሚዎችን ቁጥር ለመቀነስና የታራሚዎችን ስብዕና ግንባታ ለማሳለጥ ታላቅ አቅም መፍጠር ሲሆን፤ ሂደቱም ይህንኑ ግብ በትክክል ማሳካቱ ተረጋግጧል።
በውይይቱ ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን በአዲስ የአሠራር ስልት ለመተካት የተደረሰው የጋራ መግባባት፣ ተቋሙን ለቀጣይ ብሔራዊና ክልላዊ ተልዕኮዎች ይበልጥ ዝግጁ ያደረገ ከመሆኑም በላይ ተቋማዊ ለውጡን የማፋጠን ያለው ፋይዳው የጎላ መሆኑ እሙን ነው።
ይህ የውይይት መድረክ ለአመራሩም ሆነ ለመላው አባላት አዲስ ሞራል የሰጠ፣ ለላቀ ተልዕኮ የሚያነሳሳ እና ለወደፊት ሥራዎች ትልቅ ተቋማዊ አቅም የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
ለዚህ ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ መላው የኮሚሽኑ የሚሊተሪና የሲቪል ሠራተኞች ላሳዩት ከፍተኛ ቁርጠኝነት ኮሚሽኑ የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል።
በመጨረሻም ይህንን መሠረት በማድረግ፣ በቀጣይ ሰፊ የሪፎርም ማሻሻያ ሥራዎች የሚከናወኑ ይሆናል።
በዚህም በአሠራርና አደረጃጀት፣ በአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ እንዲሁም ግልጽ በሆነ የተጠያቂነትና የማበረታቻ ሥርዓት ላይ ያተኮሩ አዳዲስ የመዋቅር ማሻሻያዎችን በማድረግ ተቋሙን ይበልጥ ለማዘመን ታቅዷል።
መላው አባላትም በታየው የጋራ መነሳሳትና 'በጊዜ የለኝም' መንፈስ በመታገዝ፣ የተቋሙን ታላቅ ራዕይ በአዲስ ስብዕና እና በተሟላ ዝግጁነት ወደ ተግባር እንዲቀይሩት ጥሪ ቀርቧል።
ዘጋቢ፦ኮማንደር ማህዲ
13/05/2026
የሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሁለተኛ ዙር ጥልቅ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት ግንቦት 5/2018 ዓ.ም በይፋ ጀመረ
የሀረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማረጋገጥና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ያለመ የሁለተኛ ዙር ጥልቅ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ጀምሯል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ የውይይቱ ዋነኛ ትኩረትም ባለፉት የሥራ ወቅቶች የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ላይ ያተኮረ ነው።
የግምገማ መርሃ ግብሩ ከመጀመሩ አስቀድሞ ትላንት ዕለት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ እና ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ የግምገማውን አስፈላጊነትና ስነ-ስርዓት በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ (ኦረንቴሽን) ሰጥተዋል።
በወቅቱም ኮሚሽነሮቹ በመጀመሪያው ዙር ግምገማ ወቅት የተለዩ የአፈፃፀም ክፍተቶችና የፈፃሚዎች ድክመቶች በዝርዝር መታየታቸውን ገልጸው፤ አመራሩ ለቀጣዩ ምዕራፍ ራሱን በሚገባ ማዘጋጀት እንደሚገባው አሳስበዋል።
በዚህ በሁለተኛው ዙር ግምገማ እያንዳንዱ የሥራ ክፍልና አመራር "በሠራው ልክ" የሚመዘንበትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር መዘርጋቱ ተመልክቷል።
ይህም ታታሪነት የሚበረታታበት፣ የአሠራር ግድፈቶች የሚታረሙበትና የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት የአመራሩ ቁርጠኝነት የሚፈተሽበት መድረክ እንደሚሆን በኮሚሽነሮቹ አማካኝነት በሰፊው ተብራርቷል።
በአጠቃላይ ይህ ጥልቅ ግምገማ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማቀላጠፍና በየደረጃው የሚታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ተጨባጭ የሥራ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ታምኖበታል።
በዛሬው ዕለት ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ግምገማ በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚውል ከወጣው መርሃ-ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ:- ኮማንደር መህዲ