Sidama Industrial Parks Development Corporation

Call Directions Website Contact the organization

Sidama Industrial Parks Development Corporation Agricultural Modernization, Agribusiness Development and Special Economic Zones

‎ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ‎‎ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ‎‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ...
22/10/2026

‎ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ
‎
‎ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር መሳይ ኃይሉ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሹመቶችን የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
‎
‎መልካም የስራ ዘመን!
‎

‎ኮርፖሬሽኑ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ‎‎ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ ‎‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2...
21/10/2026

‎ኮርፖሬሽኑ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
‎
‎ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከማኔጅመንት አባላትና ከመላው ሰራትኞቹ ጋር በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ገምግሟል።
‎
‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፓርኮች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) በበጀት ዓመቱ ዕቅድ ዝግጅት ወቅት ከሁሉም የሥራ ክፍሎች ጋር ውል በመፈራረም ወደ ተግባር እንደተገባ ጠቅስው፤ ስራዎችን በጥልቀት መገምገም በቀጣይ ኮርፖሬሽኑ ለሚያስመዘግበው የላቀ ውጤት ጥሩ መነሻ ይሆናል ብለዋል።
‎
‎2018 በጀት ዓመት በክልሉ ከሚገኙ የመንግስት ልማት ድርጅቶች መካከል ኮርፖሬሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ያስመዘገበበት ዓመት እንደነበር ጠቁመው፤ በዚህ ዓመትም በተሻለ ጥራት ስራዎችን በመተግበር ይህንኑ ውጤት በላቀ ሁኔታ መድገም እንደሚገባም ገልጸዋል።
‎
‎የአለታ ወንዶና የሞሮቾ የገጠር ለውጥ ማዕከላት የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ርክክብ የማድረግ ሂደት ላይ እንደሆነና ሌሎች አዳዲስ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በታቀደው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተተገበረ እንደሚገኝ በቀረበው ሪፖርት ተመልክቷል።
‎
‎በፓርኩ ውስጥ ጥሬ የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር ወደ ውጭ በመላክ ከሚገኘው የውጭ ምንዛሬ አንጻር በሩብ ዓመቱ አበረታች ውጤት ስለመመዝጉም በሪፓርቱ ተገልጿል።
‎
‎በአፈጻጸም ወቅቱ በፓርኩ ለማልማት ፍላጎት ካሳዩ ባለሀብቶች መካከል ከሁለቱ ጋር ውል መፈራረም የተቻለ ሲሆን፤ በቅንጅት በተሰራው ስራ በአብዛኛው አበረታች ውጤት መመዝገቡም ተጠቁሟል።
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc

‎የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አባላት የገጠር ለውጥ ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ አደረጉ‎‎ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ ‎‎የሲዳማ ኢንዱ...
17/10/2026

‎የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አባላት የገጠር ለውጥ ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ አደረጉ
‎
‎ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት አባላት የአለታ ወንዶ እና የሞሮቾ የገጠር ለውጥ ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ በዛሬው ዕለት አድርገዋል።
‎
‎በምልከታው የመጀመሪያ ዙር የገጠር ለውጥ ማዕከላት ሥራ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ርክብክብ ስለመፈፀሙ የተገለፀ ሲሆ፤ የሁለተኛ ዙር የውሃና ሌሎች አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ዝርጋታ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲንጠናቀቁ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
‎
‎መርሃግብሩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ም/ስራ አስፈጻሚ እና የፓርኮች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) የገጠር ለውጥ ማዕከላቱ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ካለው ጠቀሜታ እንዲሁም ለአርሶ አደሩና ለአካባቢው ህብረተሰብ ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎በምልከታው የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ የሚተገበሩ ቀሪ የመሠረተ ልማት ስራዎችን በተመለከተ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፤ በኮርፖሬሽኑ እየተገነባ የሚገኘው የሞሮቾ ነጋሻ ጤና ኬላ እና የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤትም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
‎
‎የገጠር ለውጥ ማዕከላት አርሶ አደሮችን የግብርና ምርት ከማምረት ጀምሮ እስከ ማቀነባበር፣ ማከማቸት፣ ማጓጓዝና ለገበያ እስከ ማቅረብ ያለውን ሂደት ለማሻሻል የሚያግዙ የግብርናና የንግድ አገልግሎቶች ማዕከላት ናቸው።
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc
‎

‎ኮርፖሬሽኑ ከአዲስ የአቮካዶ ዘይት ማቀነባበሪያ ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ ‎‎ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ‎‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን...
13/10/2026

‎ኮርፖሬሽኑ ከአዲስ የአቮካዶ ዘይት ማቀነባበሪያ ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ
‎
‎ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፓርኮች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) Basilea Trading One Member PLC ከተሰኘ የአቮካዶ ማቀነባበሪያ ኩባንያ ጋር በዛሬው ዕለት የውል ስምምነት ፈርመዋል።
‎
‎ፕሮጀክቱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት አቶ በቃሉ ጌታሁን የተጀመረ ሲሆን፤ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሂደቶችን በማጠናቀቅ ነው በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስተ ለማድረግ ወደ ተግባር ምዕራፍ የተሸጋገረው።
‎
‎ፋብሪካው ከአቮካዶ አምራች አርሶ አደሮች ጋር ዘላቂ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን በማጠናከርና ሰፊ ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር ለአካባቢውና ለሀገር ኢኮኖሚ የጎላ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይሆናል።
‎
‎ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን እስከ 150 ቶን ጥሬ አቮካዶ በመቀበል ለማቀነባበር ዕቅድ እንዳለውና በየወሩ እስከ 6 ኮንቴይነር ምርት ወደ ውጭ ገበያ የመላክ ውጥን መያዙ ተገልጿል።
‎
‎በተጨማሪም ወደፊት ፕሮጀክቱን በማስፋፋት የተጣራ የአቮካዶ ዘይት በማምረት፤ እንዲሁም በአቮካዶ ተረፈ ምርት ኮስሞቲክስ እና የእንስሳት መኖን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የማቅረብ ዕቅድ እንዳለውም ተጠቁሟል።
‎
‎በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ! አስተማማኝ ሀብት ያፍሩ!
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc
‎

‎Sidama Region is rich in diverse agro-commodities, offering immense potential for agro-processing investment and value ...
09/10/2026

‎Sidama Region is rich in diverse agro-commodities, offering immense potential for agro-processing investment and value addition.
‎
‎Unlock this agricultural potential, add value, create job opportunities and expand access to domestic and international markets.
‎
‎Sidama IPDC warmly invites domestic and international investors to invest in the processing of coffee, fruits, vegetables, cereals, oilseeds, spices and dairy products at Yirgalem Integrated Agro-Industrial Park.
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc

06/10/2026

🇪🇹 እንኳን ለመደመር መንግስት ምስረታ በሰላም አደረሳችሁ!
‎
‎ኮርፖሬሽኑ ግብርናን ከኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር፣ ጥሬ የግብርና ምርት ወደ እሴት በመቀየር እና አግሮ-ኢንዱስትሪ ልማትን በማፋጠን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ለውጥ የበኩሉን ሚና ይወጣል።
‎
‎ግብርናን ከኢንዱስትሪ እናገናኛለን፤ ምርትን ወደ እሴት እንለውጣለን፤ በመደመር የጋራ ብልፅግናን እንገነባለን።
‎
‎የሲዳማ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን!

‎የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ‎‎መስከረም 21/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ‎የሲዳ...
01/10/2026

‎የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
‎
‎መስከረም 21/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ

‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ኃይሉ የተራ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
‎
‎መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ!
‎

25/09/2026

‎Cassava Processing: Untapped Investment Opportunity
‎
‎Meet the growing demand for cassava-based food products with modern technology and advanced food processing solutions.
‎
‎Invest in cassava processing at Yirgalem Integrated Agro-Industrial Park and turn opportunity into value!

‎ኮርፖሬሽኑ ከአካባቢው ማህበረሰብ ለተወጣጡ በፓርኩ ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ‎‎መስከረም 12/01/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ‎‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ...
22/09/2026

‎ኮርፖሬሽኑ ከአካባቢው ማህበረሰብ ለተወጣጡ በፓርኩ ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
‎
‎መስከረም 12/01/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከአካባቢው ማህበረሰብ ለተወጣጡ በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
‎
‎የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፓርኮች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) ድጋፉ ኮርፖሬሽኑ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ከሚያሳይባቸው ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ፓርኩ ከአካባቢ ማህበረሰብ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በትምህርትና ተያያዥ ልማት ዘርፍ የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
‎
‎ድጋፉ የተማሪዎቹን የትምህርት እድል ለማጠናከር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑና የነገን ትውልድ ለማፍራት ኮርፖሬሽኑ ለዘርፉ እያበረከተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያሳያልም ተብሏል።
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc

‎ለሜኢ ሜኢ ፋብሪካ ጥራት ያለው የቡና ምርት አቅርቦት ትስስርን ለማጠናከርና በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ ‎‎መስከረም 09/2019 ዓ....
19/09/2026

‎ለሜኢ ሜኢ ፋብሪካ ጥራት ያለው የቡና ምርት አቅርቦት ትስስርን ለማጠናከርና በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ
‎
‎መስከረም 09/2019 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ቡናን በማቀነባበር ለውጭ ገበያ ለሚያቀርበው ሜኢ ሜኢ ፋብሪካ ጥራት ያለው የቡና ምርት አቅርቦት ትስስርን ለማጠናከርና በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የምክክር መድረክ አካሂዷል።
‎
‎የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ ፓርኩ በተለያዩ የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ያለውን አቅም በመጠቀም የዕሴት ጭማሪን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በተለይም በቡናና አቮካዶ ላይ ሰፋፊ ኢንቨስትመንቶችን እያስተናገደ እንደሆነ ተናግረዋል።
‎
‎ያሉ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማስገንዘብ የገቡ ኢንቨስትመንቶችን በአግባቡ በመያዝ የግብርናውን እንዱስትሪ ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
‎
‎የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የፓርኮች ኦፕሬሽን ዋና ዳይሬክተር ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በፓርኩ ቡናን በማቀነባበር ላይ የሚገኘው የሜኢ ሜኢ ኩባንያ ከሲዳማ ክልል ከአሮሬሣ፣ ጫቤ ጋምቤልቶ፣ ሆኮና ደራራ ወረዳዎች ከተደራጁ 14 የቡና አቅራቢ ማህበራት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር ላይ ይገኛል ብለዋል።
‎
‎ይህ ትስስር የቡና አምራቾችን፣ አቅራቢ ማህበራትንና አቀነባባሪ ኩባንያውን በማገናኘት የተሻለ የገበያ ትስስር፣ የተረጋጋ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና ተጨማሪ የእሴት ጭማሪ ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑም ነው የተጠቆመው።
‎
‎በመድረኩ የኩባንያው ባለቤት ሚስተር ዜንግ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፤ የኩባንያው ቀጣይ ዕቅድ፣ እንሁም ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
‎
‎በመድረኩ የሲዳማ ክልል ቡና፣ አትክልትና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን፣ የህብረት ስራ ኤጀንሲ፤ የአራቱ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የህብረት ስራ ማህበራት ሊቀመንበሮች፣ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት፣ የህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት እንዲሁም ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።
‎
‎For more information:- Visit us on
‎Website: www.sidaamaipdc.com
‎Telegram: https://t.me/SIDAAMA_IPDC
‎YouTube: youtube.com/
‎Tiktok:
‎https://www.tiktok.com/.ipdc
‎

Address

Piassa
Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Industrial Parks Development Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidama Industrial Parks Development Corporation:

Shortcuts

Share