Humbo Woreda Government Communication Affairs

Call Directions Website Contact the organization

Humbo  Woreda Government Communication Affairs This is the official page of humbbo woreda gov. communication affairs page please like page and stay

አትሌት ጉዩ አዶላ በበርሊን ማራቶንን የግል ምርጥ ሰዓቱን በማሻሻል ጭምር አሸነፈ***********በ52ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ጉዩ አዶላ ለ2ኛ ጊዜ ያሸነፈበት ሆኗል።2 02 51 ርቀቱ...
27/09/2026

አትሌት ጉዩ አዶላ በበርሊን ማራቶንን የግል ምርጥ ሰዓቱን በማሻሻል ጭምር አሸነፈ
***********

በ52ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ጉዩ አዶላ ለ2ኛ ጊዜ ያሸነፈበት ሆኗል።

2 02 51 ርቀቱን ለማጠናቅቀ የወሰደበት ሰዓት ሆኗል።

ገመቹ ዲዳ 2ኛ ሲወጣ፣ ታንዛኒያዊው ጋብርኤል ጌይ 3ኛ ደርጃን ይዞ አጠንቋል።

ትግስት አሰፋ የበርሊን ማራቶንን አሸነፈች***************በ52ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ ሪከርዱን የምትሰብረብት እድል እጇ ላይ ቢሆንም ከ40 ኪ.ሜ በኋላ በገጠማት ...
27/09/2026

ትግስት አሰፋ የበርሊን ማራቶንን አሸነፈች
***************

በ52ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ ሪከርዱን የምትሰብረብት እድል እጇ ላይ ቢሆንም ከ40 ኪ.ሜ በኋላ በገጠማት ጉዳት ሳይሳካላት ቀርቷል።

ትግስት አሰፋ 2 11 04 በመግባት የግል ምርጥ ስዓቷን ጭምር በማሻሻል አሸንፋለች።

ጀግናዋ አትሌት ከባዱን ጉዳት ተቋቁማ በበላይነት ብታጠናቅቅ ሪከርዱን ግን ሳታሻሽል ቀርታለች።

በሁምቦ ወረዳ የ2019 ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል‎‎ሁምቦ፤ መስከረም 16/2019 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ላይኛ ሁምቦ ታዳጊ ማዘጋጃ...
26/09/2026

በሁምቦ ወረዳ የ2019 ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል
‎
‎ሁምቦ፤ መስከረም 16/2019 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ላይኛ ሁምቦ ታዳጊ ማዘጋጃ የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
‎
‎በዓሉ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፤ የሁምቦ ወረዳ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፤ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች ፤ ዳያቆኖች ፤ ዘማሪዎች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ ሀይማኖታዊ ሥራዓቱን ጠብቆ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ሁምቦ፦ መስከረም ፦16/2019 ዓ.ም የደመራ በዓል በወላይታ ሶዶ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክር...
26/09/2026

የመስቀል ደመራ በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ ሀይማኖታዊ ሥራዓቱን ጠብቆ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

ሁምቦ፦ መስከረም ፦16/2019 ዓ.ም የደመራ በዓል በወላይታ ሶዶ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሶዶ ደ/ፀ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።

በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባዋ ወ/ሮ ኢታገኝ ኃይለማርያም ጨምሮ የዞንና የወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፥ከሁሉም አድባራት የተሰባሰቡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፥የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በታደሙበት እየተከበረ ይገኛል ።

የሁምቦ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አማኑኤል ቦልጣና ለ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደራሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።‎‎በመልዕክታቸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ...
26/09/2026

የሁምቦ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አማኑኤል ቦልጣና ለ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደራሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎
‎በመልዕክታቸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከነበረበት የተገኘበትን ዕለትን ለማስታወስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን ደመራ፤ መስቀል ደግሞ በማግስቱ መስከረም 17 በታላቅ መንፈሳዊ ኩኔት ይከበራል ብሏል።
‎
‎በመስቀል ደመራ በዓል ምንነት በማብራራት መልክታቸው የጀመሩት ኃላፊዉ ደመረ የሚለው ቃል መጨመርን ፣መሰብሰብን ፣መከመርን ይገልጻል ብለዋል።
‎
‎ከዚህ መንፍሳዊ ክዋኔ የምንማረው ብዙ ነው በማለት፤ በዚህም ዕድገትን እና ልማትን ለማምጣት የትኛውም ፈተና ቢገጥመን አብሮነት ፣መቻቻል፣ መረዳዳት፣ መተጋገዝ፣ አንድነት፣ አብሮነት እንደሆነ አስረድተዋል።
‎
‎መስቀል በዓልን ስናከብር ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሀጢያት ምክንያት የወደቁትን የሰውን ልጆች እኛን ለማንሳት ያደረገውን መርሳት አይቻልም ያሉት ኃላፊዉ ለበደላችን የተሰቀለበት መስቀሉ የተገኘበት ቀንን በማስታወስ በመሆኑ በመላው ሀገራችን በታላቅ ድምቀት የሚከበር መንፈሳዊ በዓል መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
‎
‎አክለው የመስቀል ደመራ በዓል በዓለም የሳይንስና የትምህርት ማዕከል/ዩኔስኮ/ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ የክርስትና እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን የመላው የሰው ልጆች አኩሪ በዓል በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል ብለዋል።
‎
‎በመጨረሻም የክርስትና እምነት ተከታዮች የመሰቀል ደመራ እና የመሰቀል በዓል የሠላም፣ የፍቅር ፣የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የብልጽግና እንዲሆን በመመኘት በዓሉን ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመጠያየቅ ባህላችን መሠረት የወደቁትን በማንሳት፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ የተራቡትን በማብላት ፣የተጠሙትን በማጠጣት አረጋዊያንንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ አካላት በመደገፍ በመጠየቅ ሊሆን እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።
‎
‎ለህዝበ ምዕመኑ የመስቀል ደመረ በዓልንና የመስቀል በ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መልዕክት በማስተላለፋቸው የተሰማቸውን ልባዊ ደሰታ ገልጸዋል፡፡
‎
‎ በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን!!
‎ መልካም በዓል!
‎
‎ አቶ አማኑኤል ቦልጣና
‎የሁምቦ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽቤት ኃላፊ
‎ መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ጌቦ የደመራ እና የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!‎‎እንኳን ለደመራ እና ለብርሃነ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ...
26/09/2026

የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ጌቦ የደመራ እና የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
‎
‎እንኳን ለደመራ እና ለብርሃነ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ ! አደረሰን !
‎
‎በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወድሃለሁ።
‎
‎መስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በእጅጉ የሚከበር ታላቅ ክብረበዓል ነውና በድጋሜ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
‎
‎በወረዳችን በልዩ ድምቀት ከሚከበሩ ኃይማኖታዊ ክብር በዓላት መካከል አንዱ መስቀል(ደመራ) በዓል ነው።
‎
‎መስቀል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ሁሉ ያለ ልዩነት መውደዱን ህይወቱን አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅር የገለፀበትና ፍቅርንና ይቅርታን ያስተማረበት ነው።
‎
‎ደመራ ደመረ የሚል ትርጉም በውስጡ ያለበት በመሆኑ በዓሉ አብሮነታችንና መተሳሰብን የሚያጎላ ነው።
‎
‎መስቀል ፍቅር ነውና ከጥላቻ ፍቅርን፣ ከመገፋፋት መቀራረብን፣ ከራስ በላይ ለሌሎች ማሰብን ከመስቀሉ ስራ እየተማርን መለወጥ ያስፈልጋል።
‎
‎በዓሉ በአካባቢያችን ቢሎም በአገራችን በድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል በመሆኑ ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ ነው።
‎
‎የመስቀል በዓል በአለም በማይዳሰሱ ቅርሶች "UNESCO" የተመዘገበ ነውና ባህላዊ ዕሴት ጠብቆ እንዲቆይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
‎
‎ደመራ እና መስቀል በዓል ኃይማኖታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በዓሉ በውስጡ የያዛቸው እሴቶችን ጠብቆ የሚከበር በመሆኑ ፋይዳው እጅግ ከፍተኛ ነው።
‎
‎በዓሉ በርካታ ቱሪስቶች ከውጭ ሀገር በመምጣት የሚታደሙበት እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ድምቀት የሚከበር ኃይማኖታዊ ክብረ በዓል ነው።
‎
‎ክብረ በዓሉ በአለም በማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግቦ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እያስገኘ ያለ ነውና በዓሉን በድምቀት ሊናከብረው ይገባል።
‎
‎በዓሉን ሲናከብር የተለመደውን የመልካም እሴቶችን በማጎልበት፥ የተራቡትን በማብላት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ አቅመ ደካሞችን በመርዳት በፍጹም ፍቅርና ደስታ መሆን እንደሚገባ ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
‎
‎በአንድነት፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ የተሞላ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቴን በድጋሜ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።
‎
‎በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የተደራጀው የፀጥታ መዋቅር ከህዝብ ጋር በመሆን ተቀናጅተው መስራት ይኖርበታል።
‎
‎በድጋሚ መልካም የደመራ እና የመስቀል በዓል!!
‎
‎ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
‎ የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
‎ ክብር አቶ ጌታቸው ጌቦ
‎
‎ መስከረም 16፤2019 ዓ.ም

‎የወላይታ ዞን አስተዳደር ከካዎ ኮይሻ ወረዳ ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ለሰፈሩት ወገኖች ማዕድ አጋራ‎‎ሁምቦ፤መስከረም 16/2019 የወላይታ ዞን አስተዳደር ከካዎ ኮይሻ ወረዳ ተፈናቅለ...
26/09/2026

‎የወላይታ ዞን አስተዳደር ከካዎ ኮይሻ ወረዳ ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ለሰፈሩት ወገኖች ማዕድ አጋራ
‎
‎ሁምቦ፤መስከረም 16/2019 የወላይታ ዞን አስተዳደር ከካዎ ኮይሻ ወረዳ ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ለሰፈሩት ወገኖች የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ በማጋራት የበዓል መዋያ ስጦታ አበርክቷል።
‎
‎በማዕድ ማጋራቱ የተገኙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እንኳን የደመራና መስቀልና በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎
‎የዞኑ አስተዳደር በየበዓላቱ ከካዎ ኮይሻ ወረዳ ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ለሰፈሩት ወገኖች እንዳይቸገሩ አብሮ ሲከበር መቆየቱንም አስታውሰዋል።
‎
‎በስፍራው የሚገኙ ተሳፋሪዎች ራሳቸው እስከሚችሉ ድረስ ጠንክረው መሰራት እንዳለባቸውም መክረዋል።
‎
‎ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመለወጥ መትጋት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪው፥ የዞኑ አስተዳደር በዘላቂነት እንዲያቋቁሙ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
‎
‎በቅርቡ የመጡ ተፈናቃዮች እርስበርስ ተጋግዘውና ተደጋግፈው መሰራት እንዳለባቸውም በማሳሰብ፥ የአከባቢው ሰላምን ከፀጥታው አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
‎
‎አያይዘውም አንድነታቸውን በማጠናከር አከባቢውን ለማልማትና ለመለወጥ መትጋት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪው፥ መላው የወላይታ ህዝብ አብሮ እንዳላቸውና እያደረገ ያለውን ድጋፍም አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።
‎
‎በስፍራው ለሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች የዞኑ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
‎
‎አያይዘውም የዞኑ አስተዳደር አከባቢውን በልዩ ሁኔታ እየደገፈ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ መሠረተ ልማቶች ለማሟላት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
‎
‎በሁሉም አካባቢ ለተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረግ በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
‎
‎የአበላ አባያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ዋኬ በበኩላቸው የወላይታ ዞን አስተዳደር ተፈናቃዮች እንዳይቸገሩ በየበዓላቱ እያደረገ ያለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
‎
‎የመደጋገፍና የመተጋገዝ ባህላችን ማጠናከር እንደሚገባ በማሳሰብ፥ በስፍራው የሚገኙ ተሳፋሪዎች ራሳቸው እስከሚችሉ የወረዳው አስተዳደር እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
‎
‎በማዕድ ማጋራት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች አቶ መስፍን ቶማስና ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤልን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች ተገኝተዋል።

በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ ወረዳዊ ንቅናቄ መድረክ በ...
26/09/2026

በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ ወረዳዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሁምቦ፣ መስከረም 16/2019 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ ወረዳዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ጌቦ እንዳሉት የበጎ አገልግሎት ሥራ ስራዎች በራሳቸው ፍላጎት በመነሳት ያለምንም ክፍያ የሚያከናውኑት መልካም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

በበጎ ተግባር የሚሳተፉ ወጣቶችን ጨምሮ አጠቃላይ አካላት የወደቁትን የማንሳት ትልቅ ኃላፊነት አለብን ያሉት አቶ ጌታቸው የተጀመሩ ቤቶች ተጀምሮ እስኪጠናቀቁ በኃላፊነት መንፈስ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አብራርተዋል።

የሁምቦ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ኃላፍ አቶ አማኑኤል ቦልጣና በበኩላቸው በክረምት ወቅት የነበረውን ጥንካሬ በማጎልበት የበጋ በጎ ተግባር ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወረዳው ወጣቶች እና በጎ አግልግሎት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ መሪሁን ጤና የክረምት ወራት ማጠቃለያ ሪፖርት እና የበጋ ወራት ዕቅድ እያቀረቡ ነው።

በመድረኩ የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ጌቦ፣የሁምቦ ወረዳ ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ አማኑኤል ቦልጣናን ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት፣ የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች፣ የወጣቶች እና የሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶች፣ ፌደሬሽን እና ማህበር እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

የጣምራ ስራ ውይይት ሁምቦ ወረዳ ፣ ሶዶ ዙሪያ ወረዳና ኦፋ ወረዳ ጋር  በወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ ጣምራ ዉይይት ተካሄደ ።‎‎ሁምቦ ፦ቀን 15/01/2019 ዓ.ም ሁምቦ  ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ፣ ...
25/09/2026

የጣምራ ስራ ውይይት ሁምቦ ወረዳ ፣ ሶዶ ዙሪያ ወረዳና ኦፋ ወረዳ ጋር በወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ ጣምራ ዉይይት ተካሄደ ።
‎
‎ሁምቦ ፦ቀን 15/01/2019 ዓ.ም ሁምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ፣ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት እና ኦፋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር ወቅታዊ ፀጥታ ዙሪያ ጣምራ ዉይይት በዋጭጋ ቡሻ ታዳጊ ማዘጋጃ 01 ቀበሌ ተካሄደ ።
‎
የዉይይቱ አጀንደዎች:-
‎1. በድንበር ዘለል ወንጀል በአከባብ የሚከሰቱትን መከላከል ዙሪያ
2. ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር
‎3. ቅንጅታዊ ስራ በተመለከተ ፣
‎4. መረጃ ልውውጥ በተመለከተ ስሆን
አካባቢያችን ወንጀል ስጋት ነፃ ለማድረግ የፖሊስና ፀጥታ አካላት ከህ/ሰብ ቅንጅቱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መጠናከር እንደሚገባ ተብራርቷል።
‎
‎አስተማማኝ ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ዘንድሮ ከአገራዊ ምርጫ ፣ የወላይታ ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ በርካታ የተሠሩ ተግባራትን በመገምገም ለቀጣዩ መንግስት ምስረታ ጋር ከአገር ደረጃ እየቃጣ ያለ ፀጥታ ችግርን በማሳበብ በአከባብ ፀጉረ ለውጦች ችግር እንዳይፈጽሙ ተግተን በመጠበቅ የመረጃ ስረዓትን ውጤታማ በማድረግ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥተው የሚገቡበት አከባብ ለመፍጠር የሚያስችል ጠንካራ የጣምራ ሥራ መሰራት አለበት ተብሏል ።
‎
‎በተለይም ወንጀል ከመፈጸሙ በፍት አስቀድሞ የመከላከል ስራ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ህ/ሰብን ያሳተፈ ወንጀል በመከላከል የፖሊስ አባላት ለዜጎች ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተገቢው መወጣት እንዳለባቸው ገልጿል ።
‎
በመድረኩ፦ የሦስቱ ወረዳ ፖሊስ አዛዦች ፣ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ማ/አ/ወ/መ/ማ/ያ ኃላፊዎች የ3ቱም ወረዳ አጎራባች ቀበለ አስተዳደሮች የቀበሌ ሚሊሻዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
‎
‎በጀግነንት መጠበቅ በሰባዊነት ማገልገል!!
‎ ሁምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት !!

በሁምቦ ወረዳ የ‘ጊፋታ’ በዓል አካል የሆነው እና አዲስ ዘመን የሚበሰርበት የ‘ጉሊያ’ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ‎‎ሁምቦ፤መስከረም 11/2019 የጊፋታ በዓል ዕለት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ የሆ...
21/09/2026

በሁምቦ ወረዳ የ‘ጊፋታ’ በዓል አካል የሆነው እና አዲስ ዘመን የሚበሰርበት የ‘ጉሊያ’ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ
‎
‎ሁምቦ፤መስከረም 11/2019 የጊፋታ በዓል ዕለት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ የሆነው የጉሊያ ስነስርዓት በድምቀት ተከብሯል።
‎
‎‘ጊፋታ’ ተከብሮ፣ ሰንጋ ታርዶ ከተበላ በኋላ ወጣቶች ችቦ በመያዝ አባቶች ደግሞ ደመራውን እየዞሩ ሀገርና ምድርን በመመረቅ ደመራውን ይለኩሱታል፤ ይህ ሥርዓት በወላይታ ብሔር ዘንድ ‘ጉሊያ’ በመባል ይታወቃል።
‎
‎ወንዶች ሥጋ ከበሉ በኋላ ጉሊያ ወደ ሚቀጣጠልበት ቦታ በመሄድ በእሳት የተያያዘ እንጨት (ችቦ) ይዘው ከመጡ በኋላ ጉሊያውን አንድ የዕድሜ ባለፀጋ አዛዉንት መጀመሪያ እንዲሎክሱ ይደረጋል በመቀጠልም ሁሉም ይዘዉ የመጡትን ችቦ ጉሊያዉን ያይዛሉ፡፡
‎
‎ታዲያ ደመራው ሲደመር ሁሉም በህብረት እና በአንድነት በመተቃቀፍ ‘ሃያሌኬ’ የተሰኘ ባህላዊ ዘፈን እየዘፈኑና እየጨፈሩ የ‘ጉሊያ’ውን ምሶሶ እስኪወድቅ ድረስ ይዞሩታል።
‎
‎በዚህ መካከል የ‘ጉሊያ’ው ምሶሶ ወደቀኝ ከወደቀ "አዲሱ ዓመት የጥጋብ ዓመት ነው" ብለው፣ ተመራርቀው ይሸኛኛሉ።

Address

Wolaita Zone Humbo Woreda
Humbo Tebela
DREAMBOAT

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Humbo Woreda Government Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Humbo Woreda Government Communication Affairs:

Shortcuts

Share