30/05/2026
Customs commission Jijiga branch
ራዕይ፡- "በ2022 በአገራችን ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አሰተዳደር ተገንብቶ ማየት
30/05/2026
በጉምሩክ የቁጥጥር ሂደት የሚወሰዱ እርምጃዎች
☑️ኮሚሽኑ የጉምሩክ ፎርማሊቲ መከናወኑን ለማረጋገጥ በስራ ላይ ባሉት ድንጋጌዎች መሠረት አግባብነት ያላቸውን ማናቸውንም ዓይነት እርምጃዎች መውሰድ ይችላል፡፡
☑️በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር ኮሚሽኑ ዕቃዎች ከጉምሩክ ክልል መግቢያ በር ጀምሮ የጉምሩክ ፎርማሊቲ እስከሚከናወን ድረስ በዓይነት፣ በቅርፅ፣ በይዘትና በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ያልተለወጡ ሆነው መቆየታቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
በጉምሩክ የቁጥጥር ስርዓት መሠረት የሚወሰዱት እርምጃዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-
➙ዕቃዎችን በጉምሩክ ወደብ፣ በጉምሩክ ጣቢያ፣ በጉምሩክ መጋዘን፣ በመተላለፊያ መንገድ ወይም ኮሚሽኑ በሚወስነው ማናቸውም ሌላ ቦታ ላይ የመመርመር፣ የመከታተልና ጥበቃ የማድረግ፤
➙በመረጃና በስጋት ስራ አመራር ላይ ተመስርቶ ምርመራ የተከናወነበትን ወጪ ወይም ገቢ ዕቃ በድጋሚ እንዲመረመር የማድረግ፤
➙ወደ ውጭ ሀገር ለሚላክ ዕቃ ከሀገር ወጥቷል ብሎ ማረጋገጫ የመስጠት፤
➙የጉምሩክ ማህተሞችን ማድረግ፣ የጉምሩክ ሰነዶችን የመስጠትና የማረጋገጥ፤
➙የዕቃዎች ዓይነትና ሁኔታ አለመለወጡን ለማረጋገጥ ናሙናዎቸን፣ መግለጫዎችን፣ ፎቶዎችንና ሌሎች መረጃዎችን የመውሰድ፤
➙የመንገደኞችን ሻንጣዎችና ሌሎች ዕቃዎች የመመርመር።
☑️ከላይ በተገለጸው መሠረት ወደ ውጭ ሀገር ለሚላክ ዕቃ ከሀገር ወጥቷል ተብሎ ኮሚሽኑ ማረጋገጫ የሚሰጠው ከኢትዮጵያ መውጫ በሆነው የመጨረሻ ጣቢያ ከሚገኘው የጉምሩክ ሹም ዕቃው ከሀገር መውጣቱን የሚገልጽ ማረጋገጫ ወደ ኮሚሽኑ አውቶሜሽን ሲስተም ሲገባ ወይም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በጽሁፍ ሲደርስ ብቻ ነው፡፡
(ምንጭ)፡- የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006
በደንበኞች ትምህርት ቡድን የተዘጋጀ
ግንቦት 21/2018 ዓ.ም
ጅግጅጋ, ኢትዮጵያ
28/05/2026
26/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ አል-አድሐ (አረፋ) የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የአንድነት እሴቶች በጉልህ የሚገለጡበት ክቡር የሀይማኖት በዓል ነው። በመሆኑም ይህ ታላቅ በዓል በሕዝባችን መካከል ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አብሮነትንና መቻቻልን የሚያጠናክር እንዲሆን ቅ/ጽ/ቤቱ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
ቅ/ጽ/ቤቱ የተጣለበትን ሀገራዊ የህግ ማስከበርና የገቢ አሰባሰብ ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውን በየዘርፉ የላቀ አስተዋፅኦ እያደረጋችሁ ለምትገኙ ውድ ሰራተኞች፣ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ላኪዎች፣ አስመጪዎች፣ አምራቾች እንዲሁም የፀጥታ አካላት በሙሉ ከፍተኛ ክብርና ምስጋናውን ያቀርባል።
ይህ የአረፋ በዓል ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና፣ ለሕዝባችን አንድነትና መተሳሰብ፣ ለሁላችሁም ጤና፣ ደስታና ስኬት ያመጣ ዘንድ ቅ/ጽ/ቤቱ ከልብ ይመኛል።
ኢድ ሙባረክ!
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
25/05/2026
NB፦ በቀን 22/09/2018 ዓ.ም በሚካሄደው የግልጽ ጨረታ ላይ የወጡ ተሽከርካሪዎች በምስል
የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች
የገቢ ፖስታ ጥቅል ዕቃዎች የጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈጻጸም፦
1) ለጉምሩክ ስነ ስርዓት አፈጻጸም ሲባል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች እንደሚከተለው ይመደባሉ፦
ሀ) ለቤተሰብ ወይም ለግል ፍጆታ ወይም መጠቀሚያ በፖስታ ጥቅል ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች፣
ለ) በድርጅቶች ለንግድ አገልግሎት ወይም ለእርዳታ ዓላማ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች፣
ሐ) ተላላፊ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች ናቸው።
2) በንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) የተመለከቱት ዕቃዎች፦
ሀ) በጉምሩክ አስተላላፊዎች በኩል ዲክላራሲዮን መሙላት ሳያስፈልግ በኤሌክትሮኒክስ የመፈተሻ መሳሪዎች እና በጉምሩክ አካላዊ ፍተሻ እየተደረገባቸው ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤
ለ) በፖስታ ጥቅል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ደብዳቤዎች፣ ሰነዶችና ዕቃዎች አካላዊ ወይም በኤሌክትሮኒክስ የመፈተሻ መሳሪያዎች እየተፈተሹ ቀረጥና ታክስ የሚከፈልበት ዕቃ አለመኖሩ እየተረጋገጠ ለፖስታ አገልግሎት ድርጀቶች በቀጥታ ይተላለፋሉ።
3) በንዑስ አንቀጽ 1 (ለ) የተመለከቱት ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ በወኪሉ አማካኝነት አሰፈላጊ ሰነዶች ተሟልተው የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ከቀረበ እና የጉምሩክ ስነ ስርዓት ከተፈጸመ በኃላ ዲክላራሲዮን አቅራቢው ለገቢ ዕቃዎቹ የሚከፈለውን ቀረጥና ታክስ በመክፈል ዕቃዎቹን ይረከባል።
4) ተላላፊ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ ለኮሚሽኑ በማሳወቅና በተፈቀደለት የተለየ መጋዘን በማቆየት በህግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ወደ መዳረሻው ሀገር ማስተላለፍ አለበት።
የወጪ ፖስታ ጥቅል ዕቃዎች የጉምሩክ ስነ ስርዓት አፈጻጸም፦
1) የወጪ ፖስታ ጥቅል ዕቃዎች እንደሚከተለው ይመደባሉ፦
ሀ) ለቤተሰብ ወይም ለግለሰብ ፍጆታ ወደ ውጭ የሚላኩ ዕቃዎች፤
ለ) ለንግድ ወይም ለሌላ ዓላማ ወደ ውጭ የሚላኩ ዕቃዎች።
ዋስትና ስለማስያዝና እና ቀረጥና ታክስ ስለሚከፈልበት ሁኔታ
1) ማንኛውም የፖሰታ አገልግሎት ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር በሚገባዉ የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች ላይ ለሚከፈለው ቀረጥና ታክስ ጠቅላላ የባንክ ጋራንቲ ወይም አስገዳጅ የኢንሹራንስ ቦንድ ማቅረብ አለበት፡፡
2) የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ በመግባቢያ ስምምነቱ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ የፖስታ ጥቅል ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ ይከፍላል፡፡
3) የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ ለፖስታ ጥቅል ዕቃዎች ቀድሞ የቀረጥና ታክስ የከፈለ እንደሆነ ወይም የባንክ ዋስትና እንደሆነ ከዕቃው ባለቤት ወይም ህጋዊ ተረካቢ የከፈለዉ ቀረጥና ታክስ ወይም የባንክ ዋስትና ልክ የመሰብሰብ መብት ይኖረዋል፡፡
4) የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ ከኮሚሽኑ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ያልፈረመ እና ዋስትና ያላቀረበ የፖስታ አገልግሎት ድርጅት የፖስታ ጥቅል ዕቃዎችን ከጉምሩክ መረከብ የሚችለው ቀረጥና ታክሱን ወዲያውኑ በመክፈል ብቻ ይሆናል፤
5) የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ በስምምነቱ መሰረት ቀረጥና ታክስ ያልከፈለ እንደሆነ ባልተከፈለዉ ቀረጥና ታክስ ልክ ካስያዘው ጠቅላላ ዋስትና ላይ ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
(ምንጭ)፡- በፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ ዕቃዎች ተፈጻሚ የሚሆን የጉምሩክ ስነ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 156/2011
በደንበኞች ትምህርት ቡድን የተዘጋጀ
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
ጅግጅጋ, ኢትዮጵያ
22/05/2026
NB፦ በቀን 18/09/2018 ዓ.ም በሚካሄደው የሀራጅ ጨረታ ላይ የወጡ ተሽከርካሪዎች በምስል
የመንግስት የጉምሩክ መጋዘን
ዕቃዎች ከመንግስት የጉምሩክ መጋዘን ስለሚወጡበት ሁኔታ፣
☑️ከመንግስት የጉምሩክ መጋዘን የሚወጣ ማንኛውም ዕቃ በጉምሩክ መጋዘን በቡድን አስተባባሪው ወይም በተወካዩ መረጋገጥ አለበት፣
☑️ከዚህ በታች በተገለፁት ምክንያቶች ዕቃዎች ከመንግስት የጉምሩክ መጋዘን እንዲወጡ ሊፈቀድ ይችላል፡-
➙እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸው ዕቃዎች፣
➙በፍትህ አካላት በእግዚቢትነት እንዲቀርቡ የተጠየቁ ዕቃዎች፣
➙በክርክር ላይ የነበሩና ለባለንብረቱ እንዲመለሱ ውሳኔ የተሰጠባቸው ዕቃዎች፣
➙ለመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ዕቃዎች፣
➙ለሰብአዊ እርዳታ እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ዕቃዎች ናቸው፡፡
ወደ ተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን የገቡ ዕቃዎችን የማቆያ የጊዜ ገዳብ
1) በኮሚሽኑ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ውሳኔ መሠረት ወደ ቦንድድ መጋዘን፣ ቦንድድ ኤክስፖርት ፋብሪካ፣ የቦንድድ ኤክስፖርት ማምረቻ መጋዘን እና የቦንድድ ግብአት አቅርቦት መጋዘን የገቡ ዕቃዎችን በሚከተሉት ምክንያቶች የጊዜ ገደቡን ለተጨማሪ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡-
ሀ) ኢንዱስትሪው የሚገለገልበት ማሽን በመሰበሩ ወይም በሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ እና ሌሎች አሳማኝ ምክንያት ድርጅቱ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ስራ ማቆሙን የሚያረጋግጥ መረጃ ሲቀርብ፣
ለ) ጥሬ ዕቃው በዓለም ገበያ ላይ እጥረት ያለበት በመሆኑ ወይም ከፍተኛ የግዢ ትዕዛዝ በመኖሩ ምክንያት የተያዘ ስቶክ ሲኖር፣
ሐ) ምርቱን የሚገዛው የውጭ ድርጅት ውሉን ማፍረሱ ሲረጋገጥ ወይም ሌላ ገበያ ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ፣
መ) በሌሎች ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች፣
ሠ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ (ሀ)፣ (ለ)፣ (ሐ) እና (መ) ከተመለከተው በተጨማሪ ስልጣን ከተሰጠው አካል የድጋፍ ደብዳቤ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
2) ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ አፈጻጸም ባለፈቃዱ በአንድ በጀት ዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ የማራዘሚያ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፡፡
3) የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ጥያቄ የሚቀርበው የጊዜ ገደቡ ከማለፉ በፊት መሆን አለበት፣
4) የማራዘሚያው ጥያቄ በኮሚሽነሩ ወይም ኮሚሽነሩ በሚወክለው አካል ሲፈቅድ ብቻ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
(ምንጭ):-የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 154/2011
በደንበኞች ትምህርት ቡድን የተዘጋጀ
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
ጅግጅጋ, ኢትዮጵያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Gumruk
Jijiga
12
