10/10/2026
በወረዳችን የሚገኘው ግራናይት ማዕድን ለቀጣይ በማዕድን ሀብት ለኢንቬስትመንት ምቹ ማድረግና በማዕድን ሀብት የተሻለ ገቢ ለማምጣት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
መስከረም 30/2019 ዓ.ም
አርክሻ -ካይሳ
በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የሚገኘው ግራናይት ማዕድን ስፍራን የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መሠረት ቦጋለን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ጎብኝተዋል፤ በጉብኝቱም ወቅት የወረዳዉ ማዕድን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታድዮስ ብርሃኑ እንደገለፁት ለቀጣይ በማዕድን ሀብት ለኢንቬስትመንት ምቹ ማድረግና በማዕድን ሀብት የተሻለ ገቢ ለማምጣት ታቅዶ እየተሰራ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማምጣት የማዕድን ሀብቱን በዓይነትና በጥራት በመለየት እንዲለማ ማድረግና በተገኙ ግኝቶች ላይ የተደራጁ ወጣቶችንና አልሚ ባለሀብቶችን ወደ ሥራ ማስገባት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው ያሉት አቶ ታድዮስ፤
እንደ ወረዳ ይሄንን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት አውጥቶ ጥቅም ላይ ለማዋልና ለበርካቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያመች ዘንድ በቀጣይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የማዕድን ዘርፍ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካላቸው ዘርፎች አንዱ ነው። ዘርፉ ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ ካሉት ዋና ዋና ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
የውጭ ምንዛሬ ግኝት
የስራ ዕድል ፈጠራ፦
ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት፦ ናቸው
ግራናይት ለዘመናዊ የግንባታ ስራዎች፤ ቴራዞን፣ ክችን ካቢኔት፣ ለጌጠኛ የወለል ምንጣፎችና ደረጃዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች በጥሬ እቃ ግብዓትነት የሚውል፤ በዋጋም ውድ የሚባል ማዕድን መሆኑን በአለም ዙሪያ ይታወቃል።
ከዚህም በተጨማሪ ለዜጎች የሥራ ዕድል ፣ ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ ባለሃብቶች ይህን እድል እንዲጠቀሙበትም ጥሪ ቀርበዋል፡፡