Raya Kobo Communication Office

Call Directions Contact the organization

Raya Kobo Communication Office ​"የራያ ቆቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን፤ የዘወልድ፣ መዛርድ፣ ክፍሎና ስንየ አባቶች የሰላም እና የአንድነት አሻራ ባለቤት። የወረዳችንን የልማት ስራዎች፣ ወቅታዊ መረጃዎች እና የአንድነት እሴቶች እዚህ ይከታተሉ!"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የቁቋማት አመራሮች ሾመዋል፦
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የቁቋማት አመራሮች ሾመዋል፦

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ። በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከ...
10/10/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ተገኝተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ የጎበኙት የአጼ ሠርጸ ድንግል ልዩ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእድሳት እና የጥገና ሥራ፣ የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ አልቤስት ትሬዲንግ የሆቴል ግንባታ ፕሮጄክት፣ ዓለማየሁ ካሳ ደረሰ የሆቴል ፕሮጄክት፣ የበላይነህ ክንዴ ሂልተን ሆቴል ፕሮጄክት እና የፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ባሕር ዳር ጣና ሆቴል ፕሮጄክትን ነው።

በጣና እያጌጠች፣ በዓባይ እየደመቀች የኖረችው ባሕር ዳር ከተማ አሁን ደግሞ በልማት ሥራዎች እየተዋበች ነው። ዛሬ የተጎበኙት የልማት ሥራዎች የባሕር ዳር ከተማን ዘመናዊነት የሚጨምሩ እና እድገቷን ከፍ የሚያደርጉ ናቸው።

ለወትሮው የቱሪዝም መዳረሻ የኾነችው ባሕር ዳር ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የሆቴል ግንባታዎች ሲጠናቀቁ የቱሪዝም እንቅስቃሴዋን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ። የከተማዋን ገጽታም ከፍ ያደርጋሉ። ተፈጥሮ እና የልማት ሥራዎች የተዋሃዱባት ከተማዋ አሁን ላይ በጥሩ የልማት ደረጃ ላይ ናት።

ባሕር ዳር ለቱሪዝም፣ ለአምራች እንዱስትሪ፣ ለትምህርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች የተመቸች ከተማ ናት።

አቶ ጌታቸው ረዳ  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) አቶ ጌታቸው ረዳን  የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ...
10/10/2026

አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) አቶ ጌታቸው ረዳን የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሜ ሾመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሜ መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

!

!🇪🇹

የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦1. ክቡር ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ...
09/10/2026

የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦

1. ክቡር ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ

2. ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የENFI ክትትል ዘርፍ ኃላፊ

3. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

4. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

5. ዶ/ር ደረጀ ድጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

6. አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

7. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

#መደመርመንግሥት

09/10/2026
ቀይ መስቀልን ለመደገፍ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀመስከረም 29/2019 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)የቀይ መስቀል ማኅበር ሰሜን ወሎ ቅርንጫፍ (...
09/10/2026

ቀይ መስቀልን ለመደገፍ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

መስከረም 29/2019 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)

የቀይ መስቀል ማኅበር ሰሜን ወሎ ቅርንጫፍ (Humane, dignified, sustainable migration and return programme) ሰብአዊ፣ ክብር ያለውና ዘላቂ የፍልሰትና ተመላሽነት ፕሮግራም፤ ተመላሾች የሕግ፣ የጥበቃ፣ የጤና፣ የትምህርት እና የመሠረታዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሪፈራል ሥርዓቶችን ማቋቋም እና አመጣጥ፣ አጀማመርና ተግባራት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮነን አጥናፉ እንደገለጹት፣ ቀይ መስቀል በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ የተቋቋመ ድርጅት በመሆኑ፣ ሁሉም አካላት ማኅበሩን ሊደግፉና ለሚያከናውናቸው ሰብአዊ ተግባራት አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይገባል።

አክለውም ማኅበሩ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ያለ አድልዎ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚያከናውነው ሥራ የማኅበረሰቡን የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ፣ የተቋማትን ትብብርና የሁሉንም አካላት ድጋፍ እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል።

በሥልጠናው የቀይ መስቀል ማኅበር ታሪካዊ አመጣጥ፣ የተመሠረተበት ዓላማና የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎቶች አጀማመር በስፋት የተዳሰሱ ሲሆን፣ ማኅበሩ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለሚጎዱ ወገኖች የሚያደርገው ድጋፍ ያለው ሰብአዊ ፋይዳም ተብራርቷል።

የቀይ መስቀል ማኅበር የሰብአዊነት እሴቶችን በማጠናከርና ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት በማስፋት ረገድ የሁሉም አካላት ድጋፍና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

የአረብ ሀገር ተመላሾች ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞረዳይ ደምሴ በስልጠናው እንደተናገሩት የቀይ መስቀል ማኅበር ዋነኛ ተልዕኮ የሰውን ሕይወት ማዳን፣ ስቃይን ማቃለል፣ ጤናንና የሰውን ክብር መጠበቅ እንዲሁም በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች ያለ አድልዎ ድጋፍ ማድረግ መሆኑ ጠቁመው ይህንን ተልዕኮ ለማሳካትም የማኅበረሰቡ ተሳትፎና የበጎ ፈቃደኞች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ሥልጠናው ስለ ቀይ መስቀል ማኅበር ታሪካዊ አመጣጥ፣ አጀማመርና ተግባራት ያለውን ግንዛቤ ከማሳደጉም በላይ፣ የሰብአዊነት መርሆዎችን በተግባር ለማስፈጸምና ማኅበሩ የሚያከናውናቸውን የሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎች ለማጠናከር የሁሉም አካላት ድጋፍና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል።

09/10/2026
‎ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ይከበራል።‎‎የቀኑን አከባበር በማስመልከት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል፦‎‎19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ...
09/10/2026

‎ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ይከበራል።
‎
‎የቀኑን አከባበር በማስመልከት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል፦
‎
‎19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የኢፌዴሪ መንግሥት ፕሬዘዳንት በተገኙበት በድምቀት ይከበራል፡፡
‎
‎19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
‎
‎የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይደነግጋል፡፡
‎
‎ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡
‎
‎ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና አርማ ነው፡፡ ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበትና በሀገራዊ አንድነትና ህብረ ብሔራዊነት መግባባትን የሚፈጥሩበት ሀገራዊ በዓል በመሆኑ ነው፡፡
‎
‎ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ከጀመረ እነሆ አስራ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዘንድሮ ለአስራ ዘጠነኛ ጊዜ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነትና አስተባባሪነት በመላ ሀገሪቱ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከበራል፡፡
‎
‎በዚህም መሠረት ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዕለቱን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት በማስተላለፍ በንግግር ከከፈቱ በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት በመላው ሀገሪቱ ዜጎች በሠንደቅ ዓላማው ፊት ቃለ መሃላ የሚፈጸምበት ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡
‎
‎ከዚያም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ እና ክብር ዘብ ታጅበው በክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት አማካኝነት ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።
‎
‎በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
‎
‎ይህ በዓል በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች በተመሳሳይ ሰዓትና ድምቀት ይከበራል።
‎
‎የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት!

በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ተጽኖ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ለመቀነስ የተሠራው ሥራ ውጤታማ ነው።በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ክስተት እና የዝናብ እጥረት ትንበያን ተከትሎ በተወሰዱ ቅድመ-ዝግጅቶች ...
09/10/2026

በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ተጽኖ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ለመቀነስ የተሠራው ሥራ ውጤታማ ነው።

በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ክስተት እና የዝናብ እጥረት ትንበያን ተከትሎ በተወሰዱ ቅድመ-ዝግጅቶች ምክንያት የሰብል አዝመራው በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የቆቦ ከተማ ከንቲባ ኃይለአብ ወንድሙ እና የከተማዋ ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት እንዳስረዱት ከአርሶ አደሮች ጋር በተደረገ ቅድመ-ተግባቦት ድርቅን የሚቋቋሙ እና በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት ውጤታማ ነው።

በዚህም 200 ሄክታር የቦሰት ጤፍ እና 200 ሄክታር የመልካም ማሽላ በኩታ ገጠም የለማ ሲኾን ከዚህ ውስጥ 100 ሄክታሩ (50 ሄክታር ጤፍ እና 50 ሄክታር ማሽላ) ለቀጣይ መኸር የዘር ምንጭ የሚኾን የዘር ብዜት ታሳቢ ተደርጎ የተዘራ ነው ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኝ አባተ በበኩላቸው የዝናብ እጥረቱን ለመቋቋም ሦሥት ቁልፍ ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህም የመስኖ አማራጮችን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ዝግጁ ማድረግ፤ የዝናብ ውኃን በማቀብ የአፈር እርጥበትን ማቆየት እና ፈጥነው የሚደርሱ እና ድርቅን የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መዝራት ከተወሰዱ እርምጃዎች ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።

ኀላፊው አክለውም፤ በዞኑ ከሚገኘው ከ231 ሺህ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት ውስጥ ከአፋር ክልል ጋር በሚዋሰኑ ቆላማ አካባቢዎች ዝናብ ባለመጣሉ 40 ሺህ ሄክታሩ በድርቅ ተጎድቷል። ሆኖም ቀሪው መሬት በጥሩ የሰብል ቁመና ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለማግኘት የታቀደውን 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማሳካት ይቻላል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።

Address

+251914802280
K'obo
NONE

Telephone

+251333340269

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Raya Kobo Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Raya Kobo Communication Office:

Shortcuts

Share