Menz Gera werda Comunication office

Call Directions Website Contact the organization

Menz Gera werda Comunication  office Ensure smooth flow of information between the Menz Gera Government and the public and facilitate the

06/10/2026

የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና
ያለንን ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል ባለ ድርሻ አካላትን በማሳተፍ እንሰራለን
አቶ ማሩ ቸርነት
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

"በጥልቅ ሃሳብ መመራት እና ችግሮችን አስቀድሞ መለየት የኢትዮጵያ ብሩህ መንገድ አመላካቾች ናቸው።" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥ...
06/10/2026

"በጥልቅ ሃሳብ መመራት እና ችግሮችን አስቀድሞ መለየት የኢትዮጵያ ብሩህ መንገድ አመላካቾች ናቸው።" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ ተካሂዷል።

በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መንግሥት የኢትዮጵያን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ሁሉንም የጥንካሬ አቅሞች በማደራጀት የኢትዮጵያን ዕድገት እና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ላቅ ያሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ልምምድ ለማዘመን መንግሥት እየወሰዳቸው የሚገኙ እርምጃዎች፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጅ መቀረጹ፣ የሀገርን ጥቅም ለማስከበር አያሌ ወዳጆችን ማበራከት መቻሉ፤ የደኅንነት እና የጸጥታ ዘርፎች ይበልጥ እንዲዘምኑ መደረጉ፤ የትምህርት እና የጤና፣ የከተማ እና የገጠር ልማቶች ከኢትዮጵያ ሕዝብ መሠረታዊ ጥቅሞች ጋር እንዲተሳሰሩ ጉልህ የኾኑ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች የሚከበሩት በቀዳሚ ረድፍ ላይ የተቀመጡ ግቦችን በርትቶ በመተግበር ላይ ብቻ አይደለም፤ እልፍ ብሎ በማሰብ ላቅ ሲልም ጊዜን እና ዘመንን የሚቃኙ ደፈር ያሉ ስትራቴጂያዊ እሳቤዎችን ነድፎ ሀገርን ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ሃሳብ በመያዝም ጭምር ነው ብለዋል።

በቅርቡ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ማኅበራዊ እሴቶችን በማስተሳሰር፤ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በጽኑ የሃሳብ አምድ ላይ በማነጽ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሃሳብ ልእልና የሚያምን ለሕዝብ የተገዛ፣ ስክነት የጋራ ሃብቱ እንዲኾን ያስቻለ ክዋኔ ነው ብለውታል።

ኅብረተሰቡ የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲያገኝ የተወሰዱ የዲጂታላይዜሽን እርምጃዎች እና የሥራ ሂደትን የማሳለጥ በጎ ጅምሮችንም አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ተቀዳሚ ትኩረታቸው ሰላም እና ብልጽግና መኾኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ በተቃራኒ ከቆሙ አካላት ጋር ለመነጋገር እና ለመወያየት የታየውን ዝግጁነት እና ውጤታማ ሂደት በአብነት አንስተዋል።

በሌላም በኩል በጋራ ተጠቃሚነት እና በዲፕሎማሲያዊ አግባብ አስተማማኝ የባሕር በር ይኖረ ዘንድ ያደረግነው ጥረት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እና ይሁንታን እንዲያገኝ መሠረት ጥሏል ነው ያሉት። የኢትዮጵያን በጋራ የማደግ እና የመበልጸግ በጎ ሃሳቧን ያሳየ ነውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ አንድነት እና ሕልውና ላይ ያነጣጠሩ ውስጣዊ እና አካባቢያዊ የባላንጣነት ሃሳቦችን እና ፍላጎቶችን አስቀድሞ በመለየት በቂ ዝግጅት በማድረግ፤ የነገን እና የወደፊት ፈተናዎችን በመመልከት ሁለንተናዊ አቅምን ማዳበር እና የመፈጸም ክህሎትን ማላቅ ተገቢ እንደኾነም አስገንዝበዋል።

የመፈጸም አቅምን ማጠናከራችን ሳይታሰቡ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት ማበጀታችን እንደ ሀገር ፍቱን አካሄድ ነው ብለዋል። አሁን ካለው ተሞክሯችን ዐይተን በጋራ ለመመስከር ችለናል ነው ያሉት።

በጥልቅ ሃሳብ መመራት፤ ችግሮችን አስቀድሞ መለየት፤ ፍቱን እና ተሻጋሪ መፍትሔ ማዘጋጀት የኢትዮጵያን ብሩህ መንገድ የሚያመላክቱ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።



!

#ኢትዮጵጵያ🇪🇹

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት - በምስልJoint Opening Ceremony of the House of Peoples’ Representatives and...
06/10/2026

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት - በምስል

Joint Opening Ceremony of the House of Peoples’ Representatives and the House of Federation - in pictures


#የመደመርመንግሥት

‎በታሪካዊ ጽርሐ አርያም ፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም የዓለም ቱሪዝም ቀን በተከበረበት በወረዳው የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በትኩረት በማስተዋወቅና በእጃችን የያዝነውን ስልክ የመዝናኛ ብቻ ሳይ...
06/10/2026

‎በታሪካዊ ጽርሐ አርያም ፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም የዓለም ቱሪዝም ቀን በተከበረበት በወረዳው የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በትኩረት በማስተዋወቅና በእጃችን የያዝነውን ስልክ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የቱሪስት መስተዋት በማድረግ በዘርፉ የሚገኙ ጥቅሞችን ማግኘት ይገባል አሉ - የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሩ ቸርነት
‎
‎መ/ሜዳ፦ መስከረም 26/2019 (መጌወመኮ)
‎
‎በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባሕል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በዓለም ለ47ኛ በሃገራችን ለ39ኛ በክልሌችን ለ32ኛ በወረዳችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ "ዲጅታል አጀንዳና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለቱሪዝም አድስ ቅኝት" በሚል መሪ ቃል ቱሪዝም ቀን በአልፋ ምድር ቀበሌ በታሪካዊቷ ጽርሐ አርያም ፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም የዓለም ቱሪዝም ቀን ተከብሯል።
‎
‎በዚህም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሩ ቸርነት፣ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ቤተ-ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን ነቃ-ጥበብ መንገሻ፣ የመ/ሜዳ ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ መልዓከ ሰላም ቆሞስ አባ ዘድንግል፣ የወረዳው ቤተ-ክህነት ዋና ፀኃፊ መጋቢ አእላፍ ግራጌታ መርሃ ፅድቅ፣ የጽርሐ አርያም ፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም አስተዳዳሪ መልዓከ አርያም ቀሲስ ናርዶስ በቀለ፣ የወረዳው ባሕል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ማህሌት ዓላማው፣ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች እና በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
‎
‎በመርሃ-ግብሩ የገዳሙ አስተዳዳሪ መልዓከ አርያም ቀሲስ ናርዶስ በቀለ ገዳሙ የተባረከ ቦታ ነው ሰላም ለመሆኑና አፄ ሚኒሊክ ለሃገር ሰላምና አንድነት ሱባዔ የያዙበት ነው ብለዋል።
‎
‎በርካታ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ መንግስት ለቱሪዝሙ መነቃቃት ትኩረት ከሠጠው ከወረዳው አልፎ ለሃገር በቱሪዝም ሃብቱ የሚጠቅም ስፍራ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
‎
‎የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሩ ቸርነት በበኩላቸው ለቱሪዝም ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ይህ ታሪካዊና የተባረከ ቦታ ስለመሆኑ አንስተዋል።
‎
‎ገዳሙ ከማህበረሰብ ጥብቅ ጓሳ ስፍራ ጋር በዙሪያው የተከበበ በመሆኑ ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንን አቅም ግን በተገቢው ልክ ለመስራት አልተቻለም ብለዋል።
‎
‎ለዚህም እንደ-ምክንያት ያነሱት የሰላም እጦት ሲሆን ለአካባቢያችን ሰላም በመቆም ከቱሪዝም ዘርፉ የሚገኙ ጥቅሞችን እስካሁን ባለመጠቀማችን በመቆጨት በድጅታል ሚዲያው ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የማስተዋቅና ከፍተኛ ጥቅም መጠቀም ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
‎
‎በተጨማሪም አቶ ማሩ ቸርነት "በእጃችን የያዝነውን ስልክ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የቱሪስት መስተዋት እናድርገው" በማለት ተናግረዋል።
‎
‎በተያያዘም አካባቢያዊ የእደ-ጥበብ ሥራዎችን ጨምሮ የማህበረሰቡን ባህልና ወግ የማስተዋወቅና በዘርፉ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት በቆራጥነት ሊሰራ ይገባል ተብሏል።
‎
‎የፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም በርካታ ነገስታትና አባቶች አሻራቸውን ያሳረፉበትና ታሪክ የተፈፀመበት የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ አፅም ያረፈበት ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻ ገዳም ነው።
‎
‎በመርሃ-ግብሩ የተለያዩ ቅርሶችና ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት እና ጥንታዊ የመንዝ ህዝብ የምግብ መገልገያና አልባሳት አውደርዕይ ቀርቦ በወረዳው ባሕል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ማህሌት ዓላማው የፓናል መወያያ ቀርቦና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ተጠናቋል።
‎
‎
‎

“የባህር በር የማግኘት ጥያቄያችን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኝ መሠረት መጣሉ የኢትዮጵያን የመበልጸግ መሻት በጎ ሀሳብ ያሳየ ነው” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
06/10/2026

“የባህር በር የማግኘት ጥያቄያችን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኝ መሠረት መጣሉ የኢትዮጵያን የመበልጸግ መሻት በጎ ሀሳብ ያሳየ ነው” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

"የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባቸውን አካሂደዋል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥ...
06/10/2026

"የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባቸውን አካሂደዋል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ በማይናወጥ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንድትጸና፣ ዜጎቿም ለሀገር ብልጽግና ያላቸው ርዕይ፣ የጋለ መሻት እና የነገውን ትውልድ ባሰበ የአገልጋይነት መንፈስ የሚተጉ እንዲኾኑ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

የሀሳብ ጥልቀት፣ የዕውቀት ደርዝ፣ የሥነ ምግባር ከፍታ፣ የእሳቤ ባለቤት እና የመከወን ተነሳሽነት አንጡራ ሃብቶቻችን የኃይል ምንጮቻችን ይኾናሉ ብለዋል።

የሀገራችንን የተለምዶ የፖለቲካ ማጠንጠኛ ውርስ ከኾነው ከአምባጓሮ አመጽ እና የግጭት ጎዳና መላቀቅ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። "የጠመንጃ ባሕልን እና የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ብለዋል።

የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላም፣ በንግግር፣ በዕውቀት እና በመደማመጥ ላይ እንዲመሠረት መንግሥት ከፍ ያለ ትኩረት ይሰጣል ነው ያሉት። ለዚህም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በውይይት የዳበሩ ሀገራዊ ሀሳቦች ወደ መሬት እንዲወርዱ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ሙስናን እና ሌብነትን አምርሮ የሚታገል ማኅበረሰብ ለመፍጠር መንግሥት የጀመራቸው እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

ለኢትዮጵያን የሚመጥናት ሰላም፣ እድገት፣ ብልጽግና እና አንድነት በመኾኑ ሴራን እና ግጭትን የሚጠነስሱ የአዕምሮ እና የሀሳብ ውቅሮችን መንግሥት አምርሮ ይታገላል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያዊነት እሳቤ በእያንዳንዱ ጋሬጣ የሚደናቀፍ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንጊዜም ከእውነት እና ከታሪክ ጋር የሚሰለፍ አስተዋይ ሕዝብ ነው ብለዋል። መንግሥትም ይህንን ዕሴት አክብሮ እንደሚያስከብር አረጋግጠዋል።

!

!🇪🇹

#አሚኮ #ኢትዮጵያ🇪🇹



አሚኮ

‎"የመረጣችሁ ሕዝብ ከእምነት ጋር ታላቅ አደራ ጥሎባችኋል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ እየተካሄደ ነው። በሁለቱ ምክር ቤቶ...
06/10/2026

‎"የመረጣችሁ ሕዝብ ከእምነት ጋር ታላቅ አደራ ጥሎባችኋል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ እየተካሄደ ነው። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የሕዝብ ምክርቤት የመንግሥት ሥልጣን መሠረቱ ሰፊው ሕዝብ መኾኑ የሚረጋገጥበት ሕያው ማሕተም እና ምስክር ነው ብለዋል።

የምክር ቤት አባላት የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የሚደነግጓቸው ሕጎች በዘመናዊዋ ኢትዮጵያ የሥልጣን ፍኖት የተጣለባቸው ኀላፊነት ከፍ ያለ መኾኑን አስገንዝበዋል።

የምክር ቤት አባላት "የመረጣችሁ ሕዝብ ከእምነት ጋር ታላቅ አደራ ጥሎባችኋል" ነው ያሉት። ይህንንም በጥበብ እና በማስተዋል መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የምክርቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አሥተዳደርን የሚያዘምን፣ ኢኮኖሚን ከፍ የሚያደርግ፣ ትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ይበልጥ የሚያስፋፋ፣ ምርት እና ምርታማነትን የሚያሳድግ፣ የኑሮ ውድነትን የሚገራ፣ የመሠረተ ልማቶችን የሚዘረጋ፣ የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚያጸና ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።

!
!🇪🇹

#አሚኮ #ኢትዮጵጵያ🇪🇹



አሚኮ

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ***************የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አ...
06/10/2026

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
***************

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡ እና ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያራምዱ ሕጎችን እንዲያወጡ አሳሰቡ።

ፕሬዚዳንቱ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴረሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ይህ ታላቅ ምክር ቤት ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ ብቻ የሚገኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ አባላቱ ይህንን ተገንዝበው የተጣለባቸውን አደራ በታማኝነት ሊፈጽሙ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ላይ ሊሆን እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ በተለይም ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን መግታት የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ የላቀ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የጤና እና የትምህርት ዘርፎችን ከፍ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ከፍታ የሚያሸጋግሩ ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጂ እና በመሳሰሉት መስኮች የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ላቀ ውጤታማነት ማደግ እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በመልዕክታቸው አስምረውበታል።
EBC
*****
👇👇👇

ለወቅታዊና ትክክለኛ እና አዳዲስ መረጃዎች የማህበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ : ለወዳጆቾም ይጋብዙ:-
የፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/mmgovinformation?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
የቴሌግራም :- https://t.me/+NNXg48iHTZRjYWQ0
ቲክ ቶክ :-
https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8v54bFrAIIp&_r=1
ኢሜል :- [email protected]
ስልክ ቁጥር :- +251116850701

የመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙንኬሽን

 #አንኳር   "በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳብ መሰረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይኖረናል " ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
06/10/2026

#አንኳር
"በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳብ መሰረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይኖረናል "
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

የምክር ቤት አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ኃ...
06/10/2026

የምክር ቤት አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት የተጣለባችሁ ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የሁለቱ ምክር ቤት ተመራጭ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ስብሰባውን በይፋ ያስጀመሩት ፕሬዚዳንት ታዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል፡፡

ተመራጮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብን ይሁንታ አግኝተው የምክር ቤቶቹ አባል በመሆናቸውም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ ታላቅ ምክር ቤት የመንግሥት ስልጣን መሰረቱ እና ምንጩ የሰፊው ሕዝብ ይሁንታ እና ድምጽ እንደሆነ የሚረጋገጥበት ሕያው ማህተምና ምስክር መሆኑን አውስተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች የምታከናውኗቸው ሥራዎች እና የምትደነግጓቸው ሕጎች ለዘመዊዋ ኢትዮጵያ የሥልጣን መንገድ በሕዝብ የይሁንታ ድምጽና ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የተጣለበችሁ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህ የመረጣችሁ ሕዝብ ከአመኔታ ጋር ታላቅ አደራ የሰጣችሁ በመሆኑ ይህንን ኃላፊነተ በታላቅ አስተዋይነት፣ ጥበብ፣ ብልሃት እና ታታሪነት እንደምትወጡ የኢትዮጰያ ሕዝብ ያምናል ነው ያሉት፡፡

ሁለንተናዊ ዝግጅታችሁም ይህንን አደራ የሚመጥን ብቻ ሳይሆን ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ የሚያሸጋገር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
FBC

Address

Mehal Meda
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menz Gera werda Comunication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Menz Gera werda Comunication office:

Shortcuts

Share