Habru Woreda Government Communication Affairs Office

Call Directions Website Contact the organization

Habru Woreda Government Communication Affairs Office Habru Woreda Government Communication Affairs
የሀብሩ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬ

የ2018/19 የመኸር ምርት ግምገማ እና የድርቅ ጉዳት መጠንን ለመለየት የስምሪት ውይይት ተካሄደወልድያ :- ጥቅምት 25/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ወሎ ዞን በ201...
04/11/2026

የ2018/19 የመኸር ምርት ግምገማ እና የድርቅ ጉዳት መጠንን ለመለየት የስምሪት ውይይት ተካሄደ

ወልድያ :- ጥቅምት 25/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ወሎ ዞን በ2018/19 የምርት ዘመን በተከሰተው የእርጥበት እጥረት በሰብል ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም እና በቀጣይ መከናወን ያለባቸውን የመፍትሔ ተግባራት ለመለየት የታለመ የስምሪት ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱ የተዘጋጀው በሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባባሪያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ሲሆን፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በቅንጅት የሚሳተፉበት የመኸር ሰብል ዳሰሳ ጥናት (Assessment) ለማካሄድ የሚያስችል የስምሪት አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት ቡድኖቹ በተመረጡ የዞኑ ወረዳዎች ተሰማርተው ዝርዝር ጥናት የሚያካሂዱ ሲሆን፣ በስምሪቱ የሚሸፈኑት ወረዳዎች ላስታ፣ ቡግና፣ መቄት፣ ጋዞ፣ ሀብሩ፣ ራያ ቆቦ እና ጉባላፍቶ ናቸው።

በዚህ የዳሰሳ ጥናት በሚገኘው መረጃ መሠረት በእርጥበት እጥረት ምክንያት በምርት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን ተለይቶ፣ ለቀጣይ አስቸኳይና የዘላቂ ድጋፍ ሥራዎች አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

ሀብሩ ወረዳ | ለዓመታት በጎርፍ ምክንያት ለሰው ሕይወትና ለንብረት ጉዳት ሲዳርግ የቆየውን ችግር የፈታው የተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ!             ጥቅ...
04/11/2026

ሀብሩ ወረዳ | ለዓመታት በጎርፍ ምክንያት ለሰው ሕይወትና ለንብረት ጉዳት ሲዳርግ የቆየውን ችግር የፈታው የተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ!

ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም(ሀብሩ)

በሀብሩ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ለዓመታት የማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ሲያስተጓጉልና ለሰው ሕይወትና ለንብረት ጉዳት ሲዳርግ የቆየውን ችግር ለመፍታት የተገነባው አዲሱ የተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።

በ7,352,915.47 ብር ወጪ የተገነባው ይህ ድልድይ በሀብሩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎችና በአጎራባች አምባሰል ወረዳ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ወሳኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በድምሩ 10,574 ነዋሪዎች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ከእነዚህም መካከል 8,543 ነዋሪዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ፣ 4,608 ወንዶችና 3,935 ሴቶች ናቸው። ቀጥተኛ ያልሆኑ ተጠቃሚዎች ደግሞ 2,031 ሲሆኑ፣ 908 ወንዶችና 1,123 ሴቶች እንደሆኑ በተገኘው መረጃ ተመላክቷል።

ድልድዩ ከመገንባቱ በፊት የ08 እና የ035 ቀበሌ ነዋሪዎች እንዲሁም የአምባሰል ወረዳ የቋሆ ቀበሌ ማህበረሰብ በወንዙ ሙላት ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት ይዳረጉ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም በጎርፍ ወቅት የመሻገሪያ መንገዱ መዘጋት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያቋርጥ ነበር።

በአሁኑ ወቅት ድልድዩ መገንባቱ የነዋሪዎችን የእንቅስቃሴ ምቹነት ከማሳደጉም በላይ በጎርፍ ወቅት ይከሰት የነበረውን የመንገድ መቋረጥ በመቅረፍ የገበያ፣ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ያግዛል።

በተጨማሪም ከጎርፍ ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ የሰው ሕይወትና የንብረት አደጋዎች መከላከያ መፍትሔ ይሆናል።

የሀብሩ ወረዳ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሱሌማን መሀመድ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ ችግር የፈታ፣ የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ያቀለለና ደህንነታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ የሚያግዝ ወሳኝ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት ነው።

የድልድዩን ግንባታ «መሃመድ ግርማቸው እና ጓደኞቹ ሥራ ተቋራጭ» ያከናወነ ሲሆን፣ የማማከር አገልግሎቱን ደግሞ «አማካሪ ጥላሁን እና ጓደኞቹ አማካሪ ድርጅት» ሰጥቷል።

በአጠቃላይ የተንጠልጣይ ድልድዩ ግንባታ መጠናቀቅ የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ ችግር ከመፍታት ባለፈ የሰው ሕይወትን ለመጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከርና የልማት ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው።

"ትኩረትና እንክብካቤ ለሁሉም ህፃናት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የአለም አቀፍ  የህፃናት ቀን ሁሉም ማህበረሰብ ሊያከብረው የሚገባ ቀን መሆኑ ተገለፀ።ጥቅምት 25 /2019/ዓ/ም ሀብሩ ኮሙ...
04/11/2026

"ትኩረትና እንክብካቤ ለሁሉም ህፃናት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የአለም አቀፍ የህፃናት ቀን ሁሉም ማህበረሰብ ሊያከብረው የሚገባ ቀን መሆኑ ተገለፀ።

ጥቅምት 25 /2019/ዓ/ም ሀብሩ ኮሙኒኬሽን

በሰ/ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉ/ጽ/ቤት "ትኩረትና እንክብካቤ ለሁሉም ህፃናት" በሚል መሪ ቃል ህዳር 11 የሚከበረውን የአለም አቀፍ የህፃናት ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከአብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ማካሄዱን የሀብሩ ወረዳ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ዘቢባ ደጉ ገለፁ ።

እንደ ሀላፊዋ ገለፃ በአገራቀፍ ደረጃ ለ 21ኛ ጊዜ በአለማቀፍ ደረጃ ለ 37ኛ ጊዜ ህዳር 11 /2019 ዓ/ም የሚከበረው አለማቀፍ የህፃናት ቀን በወረዳው ውስጥ በሚገኙ 20 ት/ቤቶች በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ሲሆን በወረዳ ደረጃ በድምቀት ለማክበር ከአብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ጋር የበዓሉን የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም ግምገማ ማድረጋቸውንም አክለው ገልፀዋል ።
ንዑሳን ኮሚቴዎችም በበኩላቸው የተሰጣቸውን የስራ ክፍፍል በውጤታማነት እስከ በአሉ ፍፃሜ በመስራት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል ።

በመጨረሻም ወ/ሮ ዘቢባ እየተሰሩ ያሉ ተግባራቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የዝግጅት ምዕራፉ እየተጠቃለለ መሆኑን ገልፀው በአሉ በተለያዩ ሁነቶች የሚደምቅ ሲሆን ሁሉም ማህበረሰብ ሊያከብረው የሚገባ ቀን መሆኑንም ገልፀዋል ።


•~•~•
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የተቋማችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ዩቲዩብ:https://www.youtube.com/
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/share/19dpbXvN69/
ቲክቶክ:http://tiktok.com/.communcatio
ቴሌግራም:https://t.me/+J-1GwMayZ2Y4YzVk
ትዊተር:https://x.com/Habrucomncation

03/11/2026
03/11/2026
03/11/2026
03/11/2026
03/11/2026
03/11/2026

Address

Mersa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

0333330161

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habru Woreda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Habru Woreda Government Communication Affairs Office:

Shortcuts

Share