Guraferda woreda communication

Call Directions Website Contact the organization

Guraferda woreda  communication ቢፍቱ ጉራፈርዳ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙአዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ በሆነው ብልጽግና ፓርቲ እጩ ተደርገው የቀረቡት የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ  !  !  !
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ

! ! !

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ የመመስረቻ ስብሰባ ላይ የብሔራዊ መዝሙር ሥነ-ሥርዓት - በምስል
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ የመመስረቻ ስብሰባ ላይ የብሔራዊ መዝሙር ሥነ-ሥርዓት - በምስል

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የምሥረታ ሥነ ሥርዓት (በምሥል) !  !  !
05/10/2026

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የምሥረታ ሥነ ሥርዓት (በምሥል)

! ! !

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ***********************የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበ...
05/10/2026

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***********************

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

አቶ ደስታ ሌዳሞ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ***************************የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ...
05/10/2026

አቶ ደስታ ሌዳሞ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***************************

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም አቶ ደስታ ሌዳሞን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

05/10/2026
መጪዎቹ ታሪካዊ መስከረሞች  አዲሱ ዓመት፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚበሰርበት የኢትዮጵያውያን መስከረም ሁልጊዜም ልዩ ትርጉም አለው። ከመጪዎቹ መስከረሞች የሚጠበቀው ግን ተራ...
05/10/2026

መጪዎቹ ታሪካዊ መስከረሞች

አዲሱ ዓመት፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚበሰርበት የኢትዮጵያውያን መስከረም ሁልጊዜም ልዩ ትርጉም አለው።

ከመጪዎቹ መስከረሞች የሚጠበቀው ግን ተራ የቀን መቁጠሪያ ሽግግር ብቻ ሳይሆን፤ ሀገሪቱ ከገጠሟት ውስብስብ ፈተናዎች ተሻግራ የማንሰራራት ዘመኗን የምታውጅበትና የብልጽግናዋን መሰረት በጸና አለት ላይ የምታኖርበት ወሳኝ የጉዞ አቅጣጫ ነው፡፡

በምርጫ የዜጎችን ይሁንታን ያተረፈው አዲሱ መንግሥት በህጉ መሰረትና በሕዝብ ሙሉ ቅቡልነት ምስረታውን አካሂዶ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ ሲጀምር፤ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውድ የማረጋጋት ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥልበታል።

መጪዎቹ አምስት መስከረሞች ቀደም ሲል የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ስራዎች የሚጠናቀቁበት እንዲሁም አዳዲስ የሚጀመሩበትና ፍሬ የሚያፈራበት ይሆናሉ።

ከመሰረተ ልማት እስከ ታላላቅ የኃይል ማመንጫዎች፣ ግብርናን ከማዘመን እስከ ወደብና ትራንስፖርት ትስስር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ መስፋፋትና ዲጂታላይዜሽን ጋር ተያይዘው የተወጠኑት ታላላቅ ትልሞች ሀገሪቷን ወደ አዲስ የኢኮኖሚ ልዕልና ምዕራፍ ያሸጋግራሉ፡፡

ይህ ስኬት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን እውን ከማድረጉ ባሻገር፤ ለመጪው ትውልድ ጠንካራና ራሷን የቻለች ሀገር የመረከብ ተስፋን ያረጋግጣል።

በመሆኑም እነዚህ መስከረሞች የኢትዮጵያን ዳግም ማንሰራራት በይፋ የሚያውጁ የተስፋ ዘመናት ይሆናሉ።

እኚህ የስኬትና የተስፋ ዘመናት ግን መንገዳቸው አልጋ በአልጋ ላይሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ከየትኛውም የእድገትና የመትጋት ጉዞ ጀርባ ፈተናን የሚጋርጡ በርካታ ውስጣዊና ውጫዊ አስጊ ሁኔታዎች ይጠበቃሉና፡፡

የሀገርን ሰላምና አንድነት ለማናጋት፣ የሕዝብን የእርስ በእርስ መስተጋብር የሚያሻክሩና የውጭ ጠላቶችን ፍላጎት በማስፈጸም የልማት ጉዞውን ለማስተጓጎል የሚሰሩ አካላት የሚፈጥሩት ስጋት ቀላል የሚባል አይሆንም።

ነገር ግን ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሲያስመሰክሩት እንደኖሩት፤ በጽናትና በሀገር ፍቅር ስሜት እጅ ለእጅ በመያያዝ እንደሚሻገሩት ቅንጣት ጥርጣሬ አይኖርም፡፡

ሌላኛው ፈተና የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ የዓለም አቀፍ የነዳጅና የሸቀጦች ዋጋ መናር እንዲሁም ቀጣናዊ ግጭቶች በሀገራዊ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነት ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖ ትልቅ ውጫዊ ስጋት ነው።

መጪዎቹ መስከረሞች ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን ታላላቅ የልማት ስራዎች አጠናቅቃ አዳዲሶችን በማብሰር ወደ ብልጽግና የምትሸጋገርበትን የታሪክ በር የሚከፍቱ ወሳኝ ምዕራፎች ናቸው።

ነገር ግን ይህ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው የሌብነትን እሾህ በመንቀል፣ የአፍራሽና ተላላኪ ኃይሎችን ሴራ በጥበብና በጽናት በመመከት እንዲሁም የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ርምጃዎችን ከመንግሥት ጋር በመሆን በመደገፍ ነው።

ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራትና ለአዲሱ ትውልድ ብሩህ ተስፋ፣ መጪዎቹ አምስት መስከረሞች የእውነትም የኢትዮጵያ ብልጽግና ማብሰሪያ ይሆናሉ።(ኤፍ ኤም ሲ)

በወረዳው በተጠናቀቀው በጀት አመት 2,818.75 ቶን የታጠበና ቅሽር ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ መላኩ ተገለፀ።መስከረም 23/2019 ዓ/ም :-የጉራፈረዳ ወረዳ የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ...
03/10/2026

በወረዳው በተጠናቀቀው በጀት አመት 2,818.75 ቶን የታጠበና ቅሽር ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ መላኩ ተገለፀ።

መስከረም 23/2019 ዓ/ም :-የጉራፈረዳ ወረዳ የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት የቡና ጥራት እና ቁጥጥር አስተባባሪ ግብረ ሃይል እንድሁም የቡና እደሳት ተግባራት በተመለከተ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩም በዋናነት የቡና ጥራት፣የቡና ሽፋን በማሳደግ ምርታማነትን መጨመር፣ የቡና ጉንደላ፣ የቡና አሰባሰብና ግብይት እና ማህበረሰቡ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እንድሻገር በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ሀሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጎል።

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ የቡና አሰባሰብ ሂደቱ ከአምና በተሻለ መልኩ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሰበሰብና የግብይት ሥርአት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዉ ለዚህም ተፈጻሚነት የሁሉም ማህበረሰብና ባለ ድርሻ አካላት የበኩላዉን ሚና መወጣትን ይጠይቃል ብለዋል።

የወረዳው የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ እርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አቡሽ ሀይሌ ባቀረቡት ሪፖርት የቀይ እሸት ቡና አሰባሰብ ዕቅድ 13,000 ቶን ሲሆን፣ 12,095.89 ቶን በመሰብሰብ 93.04 አፈጻጸም እንደተመዘገበና የታጠበ ቡና የተሰበሰበው 10,382.72 ቶን ሲሆን፣ 2,473.615 ቶን ደግሞ ወደ ስፔሻሊቲ ቡና ዝግጅት መዞሩ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የታጠበ ቡና ዝግጅት ዕቅድ 2,600 ቶን ሲሆን፣ የተመዘገበው ክንውን 1,816.98 ቶን ከሆነ 69.88 አፈጻጸም መኖሩንና 2018 ዓ.ም የጀንፈል ቡና አሰባሰብ ዕቅድ 5,000 ቶን ሲሆን 4,311.15 ቶን በመሰብሰብ 86.22 አፈጻጸም ተመዝግቧል።

ወደ ማዕከላዊ ገበያ የተላከውን ቡና በተመለከተም:- ቅሽር ቡና 2,500 ቶን ለመላክ ታቅዶ 990.25 ቶን በመላክ 46.33 አፈጻጸም ሲመዘገብ የታጠበ ቡና 2,600 ቶን ለመላክ ታቅዶ 1,828.5 ቶን በመላክ 70.32 አፈጻጸም መመዝገቡን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡

በአርሶ አደሩ በኩል ያልበሰለ ቃሪያ ቡና መልቀም ፣ በአልጋ አሰጥቶ ያለማድረቅ ፣ ለረጅም ጊዜ በተለያዩ እቃዎች ማከማቸት ፣ ቡናን በወቅቱ ለዓለም ገበያ አለማቅረብ እና የግብይት ማዕከላትን ለታለመለት አላማ አለማዋል የቡናን ጥራት የሚፈታተኑ ተግዳሮቶች መሆናቸው በመድረኩ ተነስቷል።

ተሳታፊዎች በቡና ምርት ዝግጅትና ጥራት ቁጥጥር የግብይት ሂደቱ መንግስት ትኩረት በማድረግ የአርሶ አደሩን የኑሮ ሁኔታ ከማሻሻል በተጨማሪ ወረዳውን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።።
የጉራፈረዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኦይሳ አለሙ እንደገለፁት በወረዳው በየቀበሌው የፀጥታ ተግባርን ማስቀደም እንደሚያስፈልግ ገልፀው የቡና ምርታማነትና ጥራት ማሻሻል የአርሶ አደሩን ኑሮ ከመለወጥ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም አቶ ኦይሳ አለሙ በየቀበሌው የችግኝ ጣቢያ በማዘጋጀት በቡና ንግድ የሚታዩ ህገ ወጥ ድርጊቶችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት መቅረፍ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የጉራፈረዳ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን አስፋው አርሶ አደሩ ቡናውን ጥራት ባለው መንገድ በመልቀም በአልጋ ላይ በማድረቅ ጥራት ያለው ቡና ለገበያ አቅርቦ በተሻለ ዋጋ ሽጦ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ወስዶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አክለውም አቶ መስፍን የተለያዩ የማህበረሰብ የመልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ሕገ ወጥ የቡና ዝዉዉር መቆም እንዳለበት አብራርተዉ ሕዝብና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እያጣ በመሆኑ ሕገ ወጦችን በመከላከል የተሻለ የቡና ምርት ዝግጅትና የግብይት ሥርአት እንዲሰፍን በጋራ መጠበቅ አለብን ብለዋል።

በመድረኩ መጨረሻ አቶ ታጋይ ኤሊያስ በዘርፉ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በጉድለት የታዩትን በማሻሻልና የተቋቋመውን የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አስተባባሪ ግብረሃይልን ችግር ፈቺ በማድረግ ወረዳን በቡና ልማት ዘርፍ ታዋቂ ለማድረግ መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።

የቡና ጥራትን በማስጠበቅና ምርት መጠን በማሳደግ  ለኢኮኖሚ እድገት ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ። አቶ ታጋይ ኤሊያስየጉራፈረዳ ወረዳ የ2019 በጀት አመት የቡና ጥራት እና ቁጥጥር አስተባባ...
03/10/2026

የቡና ጥራትን በማስጠበቅና ምርት መጠን በማሳደግ ለኢኮኖሚ እድገት ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ። አቶ ታጋይ ኤሊያስ

የጉራፈረዳ ወረዳ የ2019 በጀት አመት የቡና ጥራት እና ቁጥጥር አስተባባሪ ግብረ ሃይል እንድሁም የቡና እደሳት ተግባራት የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ እንዳሉት ቡና የሁላችንም የኢኮኖሚ ምንጭና መነሻ በመሆኑ ልማቱን በማስፋት ጥራቱን በመጠበቅ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል ።
‎
አክለውም አቶ ታጋይ ኤሊያስ የቡና ጥራትና ቁጥጥርን በማጠናከር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት በ2019 ዓ.ም ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ይጠበቅብናል ብለዋል ።

የጉራፈረዳ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን አስፋው እንደገለፁት ከቡና ሽፍን፣የምርት መጠን እና ጥራት ማረጋገጫ ስራዎች ባሻገር ጤናማ የግብይት ስርዓት ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች ለ2019 ዓ/ም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም አቶ መስፍን አስፍው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም እንከን በሰላም ተጠናቆ ፓርቲያችን አብላጫ ድምፅ አምጥቶ የክልል መንግስት በተመሰረተ ማግስት ምክክሩን ማካሄዳችን ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

ወረዳችን በዞኑ በቡና ሽፍን ግንባር ቀደም መሆኑን ገልፀው በ2019 ዓ/ም በምርትና በጥራት ግንባር ቀደም እንድሆን ትኩረት ሰጥተን መስራ አለብን በማለት አቶ መስፍን አስፋው ተናግረዋል።

በመድረኩም የቡና ጥራት እና ቁጥጥር በአስተባባሪ ግብረ ሃይል በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ሰነድ የወረዳው የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ እርሻ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አቡሽ ሀይሌ እየቀረበ ነው።

Address

Biftu
Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guraferda woreda communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Guraferda woreda communication:

Shortcuts

Share