Southwest Revenue Bureau

Call Directions Contact the organization

Southwest Revenue Bureau የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የገቢዎች ቢሮ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ነዉ፡፡

ለተቋማዊ ግብ ስኬት ጠንካራ የቡድን መንፈስ፣የጋራ  ሥራ እና ቅንጅታዊ ጉዞ እጅጉን አስፈላጊ ነዉ - አቶ የሺዋስ  ዓለሙለውይይት የሚመች፣ዕዉቀት መር የሆነ ተናባቢና ተጠያቂነት ሥርዓት ያለዉ...
21/10/2026

ለተቋማዊ ግብ ስኬት ጠንካራ የቡድን መንፈስ፣የጋራ ሥራ እና ቅንጅታዊ ጉዞ እጅጉን አስፈላጊ ነዉ - አቶ የሺዋስ ዓለሙ

ለውይይት የሚመች፣ዕዉቀት መር የሆነ ተናባቢና ተጠያቂነት ሥርዓት ያለዉ ተቋም በመገንባት የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ እናሳካለን ።

ጥቅምት 11/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የተቋሙ አመራርና ፈፃሚ አንድ አሀድ ሆኖ በመንቀሳቀስ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በቅንጅትና በትብብር መንፈስ ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የገቢዎች ቢሮ ተቋሙን የተቀላቀሉ ከፍተኛ አመራሮች ከተቋሙ አጠቃላይ ፈፃሚዎች ጋር የተቋሙን ዘላቂ ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

አቶ የሺዋስ ዓለሙ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ክልሉ ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ በአዋጅ ተቆጥሮ የተሰጠውን ተግባር በመወጣት ለህዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ለመመለስ እንዲቻል የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ወረት ከግብርና ታክስ እንዲገኝ ሰፊ ርብርብ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

በዚህም ክልሉ ሲመሠረት 2014 በጀት ዓመት ከተሰበሰበው 3.2 ቢሊዮን ብር ገቢ በ2018 በጀት ዓመት 18.2 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ በ5.6% (ከአምስት እጥፍ በላይ) ማላቅ የተቻለ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ 29 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ከግብርና ታክስ በመሰብሰብ የክልሉን መንግስት የልማት መከወኛ ወጪ 64.5 በመቶ በላይ በሚሰበሰብ ግብርና ታክስ ለመሸፈን ከላይ እሰከ ታች ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።

አቶ የሺዋስ ለውይይትና ለሀሳብ ገበያ የሚመች ተቋም በመገንባት አመራሩና ፈፃሚው አንድ አሀድ ሆኖ በመንቀሳቀስ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በቅንጅትና በትብብር መንፈስ ተግባራትን በመፈፀም የሚቆጠር ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አክለው ተናግረዋል።

የተቋሙ ባለሙያዎችም በየዘርፋቸው ተግባራትን ሲከውኑ የቆዮበትን መንገድ አቅርበዋል፣ በቀጣይም የተቋሙን ሀገራዊና ክልላዊ ራዕይ ዳር ለማድረስ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ጠቁመዋል።

አቶ ዳዊት ገበየሁ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ተቋሙ ያለውን የሰው ሃብት እውቀት አቀናጅቶ በመጠቀም ክልሉ ባለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ልክ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ሁሉም በተሰማራበት የስራ ዘርፍ አሻራ የሚሆን ተግባር ለመፈፀም በትብብርና በወንድማማች መንፈስ መስራት ዓለብን ሲሉ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ብርቅነሽ ሻንቆ የተቋሙ ምክትል ኃላፊና የህግ ማዕቀፍ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ተቋሙ የተጣለበት የህዝብና የመንግስት ኃላፊነት በየዘርፉ ተግባራትን በመለዮት በጋራ የታችኛውን መዋቅር በማብቃት ውጤታማ ስራ በየምዕራፉ መከናወን አለብን ብለው ለዚህም በቅንጅትና በትብብር በንፁህ ልቦና እንነሳ ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ሰላም አደቆ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው እንዳሉት የሁላችንም አለቃ ስራችን በመሆኑ ተግባራትን የሙያና የስራ ላይ ስነ-ምግባር ተላብሰን ቅንጅታዊ አሰራርን በማላቅ ውጤት ለማስመዝገብ ሌት ከቀን መትጋት አለብን ብለዋል።

አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለተቋሙ ሁሉን አቀፍ ራዕይ ስኬት በአዲስ መንፈስ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማላቅ ሌት ከቀን መረባረብ እንደሚገባ በመድረኩን ሲያጠቃልሉ ተናግረዋል።

የሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከ453 ሚሊዮን  ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸየሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት 453 ሚሊዮን 6 ...
21/10/2026

የሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከ453 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

የሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት 453 ሚሊዮን 6 ሺህ 356 ብር ገቢ መሰብሰቡን የመምሪያው ኃላፊ አቶ በላቸው በቀለ ገልጸዋል።
‎
‎የመምሪያው ኃላፊ በሦስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
‎
ኃላፊው በመግለጫቸው በሁለት ከተማ አስተዳደሮች፤ሶስት ወረዳዎች እና ዞን ማዕከልን ጨምሮ በሦስት ወራት ወስጥ 668 ሚሊዮን 223 ሺህ 551 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 453 ሚሊዮን 006 ሺህ 356 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ይህም የዕቅዱን 68 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አብራርተዋል።
‎
‎በመደበኛ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ገቢን በሚመለከት በመደበኛ 614 ሚሊዮን 097 ሺህ 582 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 395 ሚሊዮን 572 ሺህ 795 ብር የተሰበሰበ ሲሆን የማዘጋጃ ቤት ገቢ 54 ሚሊዮን 125 ሺህ 969 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 57 ሚሊዮን 433 ሺህ 563 ብር የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎በየደረጃው የሚገኙ ግብር ሰብሳቢ ተቋማት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በቀጣይ በ90 ቀናት ውስጥ የበጀት ዓመቱን የ6ወር ዕቅድ 100 በመቶ ለማሳካት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
‎
‎ግብር ከፋይ ነጋዴዎችም ወደ ቅጣት ሳይገቡ የቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት በየሦስት ወሩ (25%) ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

ዘገባው የሸካ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ነው

የገቢ ኮሪደሮችን በአግባቡ ለይቶ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚመጥን ገቢ መሰብሰብ ይገባናል - አቶ ታጋይ ኤሊያስጥቅምት 11/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ) የጉራፈረዳ ወረዳ ገቢ...
21/10/2026

የገቢ ኮሪደሮችን በአግባቡ ለይቶ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚመጥን ገቢ መሰብሰብ ይገባናል - አቶ ታጋይ ኤሊያስ

ጥቅምት 11/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የጉራፈረዳ ወረዳ ገቢ ጽ/ቤት በ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከባለድረሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ የመድረኩ ዋና አላማ በወረዳው የውስጥ ገቢ አቅምን በማጠናከር የአከባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ የሚመጥን ሀብት በማሰባሰብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ በተባበረ ክንድ ምላሽ ለመስጠት ያለመ የምክክር መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

የጉራፈረዳ ወረዳ ገቢ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርብ ወልዴ የ1ኛ ሩብ አመትእቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ 589,072,442ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ እንደተያዘ ገልፀው ግቡ እንዲሣካ በሁሉም መስክ የሚሰሩ ጠንካራ አመራርና የገቢ ሠራዊት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።

መደበኛ የአመቱ የገቢ እቅድ 557,765,643 ብር ሲሆን 1ኛ ሩብ አመት እቅድ 139,441,410 ብር ሲሆን ክንውን 65,965,460 ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልፆል

ማዘጋጃ ቤታዊ የአመቱ እቅድ 31,306,799 ብር ሲሆን የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ 7,826,699 ብር ሲሆን 9,535,299 ብር መሰብሰቡ በቀረበው ሪፖርት ገልፀዋል

በአጠቃላይ ከመደበኛና ከመዘጋጃ ቤታዊ በ1ኛ ሩብ አመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 147,268,110 ብር ውስጥ 75,500,759 በላይ መሰብሰብ መቻሉን አቶ ደርብ ወልደ ገልፀዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የልማት ስራዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል የገቢ አቅምን ማሳደግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በ1ኛ ሩብ አመት የታዩ ጥንካሬዎችን በበለጠ በማስቀጠል ጉድለቶችን የዕቅዱ አካል በማድረግ በትኩረት መስራት አለብን ብለዋል።

የገቢ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርብ ወልደ በወረዳው ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ መንግስት የህዝቡን የልማት ጥያቄ መመለስ እንዲችልና በየቀበሌው የተጀመሩ ልማቶች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ ገቢ ለሀገር ልማት እና ዕድገት የጀርባ አጥንት በመሆኑ በየደረጃው ያሉ የገቢ መዋቅሮች አመራሮችና ባለሙያዎች በህዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ሃላፊነትን በአግባቡ መዋጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል ሲል የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

በበጀት አመቱ የወረዳውን የገቢ አቅም በማሳደግ የህዝባችንን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት ይሰራል፦ አቶ ደመላሽ ጌዳጥቅምት 11/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ...
21/10/2026

በበጀት አመቱ የወረዳውን የገቢ አቅም በማሳደግ የህዝባችንን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት ይሰራል፦ አቶ ደመላሽ ጌዳ

ጥቅምት 11/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ጌዳ በወረዳው ስር የሚገኙ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶችን የ2019 በጀት አመት አንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀማቸውን በጽህፈት ቤታቸው ገምግመዋል።

በበጀት አመቱ የወረዳውን የገቢ አቅም በማሳደግና ወረዳው ያለውን ሀብት በአግባቡ በመሰብሰብ መጠቀም እንዲችል ሁሉም ታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች የገቢ አሰባሰብ ስርአታቸውን በማሻሻል የህዝባችንን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል።

የየኪ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኦኖ በበኩላቸው ወረዳው ከመዘጋጃ ቤቶች የሚሰበስበው ገቢ ከፍተኛ በመሆኑ ማዘጋጃ ቤቶች የገቢ አሰባሰብ ስርአታቸውን ሊያዘምኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማዘጋጃ ቤቶች ከመሬት አስተዳደርና ዝግጅት አንፃር፣ የማዘጋጃ ቤቶች የከተማ ፅዳትና ውበት በሚመለከት ፣ አዲስ መንገድ ከፈታና ያሉትን ነባር መንገዶች ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ፣ ከገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም አኳያ ፣ከጫት የሚገኝ ገቢ አሰባሰብ ስርዓት ፣ ከቄራ አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የበረት ኪራይ ገቢ፣ የመነኻሪያዎች አስተዳደር ስርአት በሚመለከት በሁሉም ዘርፍ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተካሂዷል።

ከመሬት አስተዳደር ስርአት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የህግ አሰራርን ተከትሎ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ የማዘጋጃ ቤት መሬት በወቅቱ ሳይጓተት ለተጠቃሚዎች ተላልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ ነው የተገለፀው።

በታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች የከተማ ፅዳትና ውበት እንዲሁም የገጠር ኮሪደር ስራዎች በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።

የየኪ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደራሻ በሰጡት አስተያየት የሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች በተፈቀደላቸው የገቢ መሰብሰቢያ አርዕስት ኮዶች ቅንጅታዊ የአሰራር ስርአትን በማጎልበት አቅምን አሟጦ በመጠቀም የወረዳውን ገቢ ሊሰበስቡ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የየኪ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አምሳሉ ከሲቶ በማጠቃለያቸው የማዘጋጃ ቤት ገቢ ሰብሳቢዎች ከገቢና ከከተማና ልማት ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት የወረዳውን የገቢ አቅም ለማሳደግ ሊሰሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ጌዳ የማዘጋጃ ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች በተቋም ግንባታ እና በእያንዳንዱ የገቢ አርዕስት ኮድ አቅማቸውን አሟጠው ገቢ ሊሰበስቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች የገቢ አቅማተውን ከፍ ለማድረግ የባዛር ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የየዘርፍ ኃላፊዎች፣ የታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች ስራ አስኪያጆችና ማናጅመንት አካላት ፣ የየኪ ወረዳ ከተማና ልማት ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊና ማናጅመንት አባላት፣ የወረዳው ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊና የገቢ አሰባሰብ ዳይሬክቶሬቶች በተገኙበት የታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች የ2019 አንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ተገምግሟል ።

ዘገባው የየኪ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ነው

የተደረገው ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል የዞኖችን የማስፈፀም አቅም በመገንባት ረገድ  አጋዥ ነው - አቶ የሺዋስ ዓለሙጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)የደምኢህክመ ገቢዎች ...
20/10/2026

የተደረገው ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል የዞኖችን የማስፈፀም አቅም በመገንባት ረገድ አጋዥ ነው - አቶ የሺዋስ ዓለሙ

ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የክልሉን መንግስት የልማት መከወኛ ወጪ 64.5 በመቶ ለመሸፈን ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።

የበጀት ዓመቱን እቅድ በየምዕራፉ አሟጦ ለመሰብሰብ እንዲቻልም የቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች በየዞኑ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ አድርገዋል።

ቢሮው በ6ቱ ዞን የተከናወነውን የገቢ ተቋም ሙያዊና ቴክኒካዊ የድጋፍና ክትትል የመስክ መልስ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።

የድጋፍና ክትትሉ በተደራጀ ቼክ ሊስት በስድስቱም ዞን፣ በስድስቱ የከተማ ስተዳደሮች እና በተመረጡ ወረዳዎች ለአንድ ሳምንት ተካሄዷል።

አቶ የሺዋስ ዓለሙ የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የተደረገው ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል በየደረጃው ችግሮችን በመለየትና መፍትሄዎችን በማመላከት፣ እንዲሁም ተቋማዊ አሰራር ለመዘርጋት በልዩነት የተደገፈ በመሆኑ ይህም የዞኖቹን የማስፈፀም አቅም በመገንባት ረገድ አይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።

በድጋፍና ክትትሉ ወቅት የተገኙ ክፍተቶችን በቀጣይ የዕቅድ ትግበራ ወቅት በመሙላት የክልሉን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እየተከናወነ ያለው ተግባር ሁሉን አቀፍ ሆኖ ውጤታማ እንዲሆን የሚሰራው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የወረዳውን ገቢ አሰባሰብን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በዳውሮ ዞን ​የዲሳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና የሥራ ሃላፊዎ...
20/10/2026

የወረዳውን ገቢ አሰባሰብን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በዳውሮ ዞን ​የዲሳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና የሥራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት፣ የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀምን ማሻሻልና የታቀዱ ግቦችን ማሳካት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

​መድረኩን የመሩትና የስራ መመሪያ የሰጡት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አበራ፤ ማንኛውንም ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለማስፈጸም የዕቅዶች ሁሉ ሳንባና መሰረት ገቢ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

አቶ አብርሃም አበራ አክለውም፣ የገቢ አሰባሰቡን አቅም (ፖቴንሻል) ከፍ ለማድረግ በህብረተሰቡና በንግዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሊሠሩባቸው የሚገቡ አቅም ያላቸው አካባቢዎች ተለይተው በቁርጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

​በውይይቱ ላይ ተገኝተው ሃሳብ የሰጡት የወረዳው መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ በዛብህ ባይካ በበኩላቸው፤ በወረዳችን የሚታዩ የመሠረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የገቢ አቅምን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ በዛብህ አያይዘውም፣ የገቢ ኮሪደሮችን በጥንቃቄ በመለየት እና ለሥራው ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በጋራ በመቅረፍ አፈፃፀሙን ወደ የተሻለ ከፍታ ማሸጋገር እንደሚገባ አሳስበዋል።

​በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባለሙያዎቹ ከተነሱት አቅጣጫዎች በመነሳት በቀጣይ በባለቤትነትና በቅንጅት ለመሥራት ቃል የገቡ ሲሆን፤ ያጋጠሟቸውን ክፍተቶችና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማንሳት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ዘገባው የዲሳ ወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን ነው።

‎

በጀሙ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የገቢ  ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በጀሙ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ፣ የማዘጋጃ ቤት አገል...
20/10/2026

በጀሙ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የገቢ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በጀሙ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ፣ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችና በንግድ ዘርፍ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱ የገቢ፣ የማዘጋጃ ቤትና የንግድ ዘርፎች ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ለማስፈጸም፣ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታትና የከተማውን የልማት እንቅስቃሴ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሽፈራው ማናባ የከተማውን የገቢ አቅም ለማሳደግ፣ የማዘጋጃ ቤትና የንግድ ዘርፎችን አፈጻጸም ለማሻሻል እንዲሁም ለከተማው ዕድገት የሚያበረክቱ ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ማከናወን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

አክለውም የገቢ አሰባሰብን ማጠናከር፣ የተግባራትን አፈጻጸም በቅርበት መከታተልና ለነዋሪዎች የተሻለ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ማሞ በበኩላቸው የግብር ከፋዮችን ግንዛቤ በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የግብር አሰባሰብን በማረጋገጥና ሁሉንም የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመሰብሰብ የገቢ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ማሙዬ የከተማውን የገቢ አቅም ማሳደግ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ማስፈን እና ለነዋሪዎች የተሻለ አገልግሎት ማቅረብ የሁሉም አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ ልያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ሽፈራው ማናባ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ማሞ፣ የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ማሙዬን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
ዘገባው የጀሙ ከተማ ኮምንኬሽን ነው።

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሰበሰበጥቅምት 10/2018 ዓ.ም. (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ...
20/10/2026

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሰበሰበ

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም. (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምንና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በበይነ መረብ ገምግሟል።

የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ የሩብ ዓመቱን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን እያደገ የሚመጣውን የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄና የአገልግሎት ፍላጎት በአግባቡ ለመመለስ የፋይናንስ ምንጮችን ማሳደግና ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀረበው ሪፖርት በመደበኛ 1 ቢሊዮን 715 ሚሊዮን 842 ሺህ 459 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊዮን 474 ሚሊዮን 173 ሺህ 611 ብር መሰብሰብ ተችሏል ይሄም ከሩብ ዓመቱ አንጻር 81%

ከማዘጋጃ 153 ሚሊዮን 160 ሺህ 998 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 163 ሚሊዮን 420 ሺህ 953 ብር መሰብሰብ ተችሏል ይሄም ከሩብ ዓመቱ አንጻር 106%

በድምር 1 ቢሊዮን 869 ሚሊዮን 003 ሺህ 457 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊዮን 637 ሚሊዮን 594 ሺህ 564 ብር መሰብሰብ ተችሎ ከሩብ ዓመቱ አንጻር 87% እንደሆነ ተገልጿል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ እንዳሉት የሕዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የልማት ማነቆዎችን ለመፍታት ሀብትን በአግባቡ ማሰባሰብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የገቢ አሰባሰብ ሥራዎችን የሚያደናቅፉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት ዕቅዱን በየጊዜው በመገምገምና አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙን ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በተጨማሪም የግብር ከፋዮች መረጃና ቁጥር በትክክል ሰንዶ በመያዝ ሕገወጥ አሠራሮችን መከላከል የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና የተለዩ ክፍተቶችን በተቀናጀ አሠራር ማረም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በግምገማው ወቅት የመብራት ኃይልና የሲስተም መቋረጥ፣ የሕገወጥ ነጋዴዎች ቁጥር መጨመር፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የሚሰበሰበው ገቢ መቀነስና ደረሰኝ ያለመስጠት ከታዩት ተግዳሮቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት፣ የግብር ሕግን ማስከበር፣ የደረሰኝ አሰጣጥን መቆጣጠርና ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መከላከል እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ የደረጃ ለ ግብር ከፋዮችን በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ማድረግ የመደበኛና የማዘጋጃ ቤት ውዝፍ ዕዳዎችን መከታተል እና መሰብሰብ የደረሰኝ አሰጣጥን በአግባቡ በመቆጣጠር ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት እንደሆኑ ተገልጿል

ዘገባው የገቢዎች መምሪያ ነው

የሰሜን ቤንች ወረዳ የገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር የ90 ቀናት የተግባር ንቅናቄና የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ተገምግሟል።ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን...
20/10/2026

የሰሜን ቤንች ወረዳ የገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር የ90 ቀናት የተግባር ንቅናቄና የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ተገምግሟል።

ጥቅምት 10/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሞ፣ በቀጣዮቹ 90 ቀናት የገቢ አሰባሰብን በማጠናከር የወረዳውን የልማት ፍላጎት ለመደገፍ ያለሙ የውይይትና የዕቅድ ማጠናከሪያ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የሩብ ዓመቱ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች በጥልቀት የተገመገሙ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 90 ቀናት የገቢ አሰባሰብን በትኩረት፣ በቅንጅትና በተጠናከረ ክትትል ለማከናወን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በተለይም የጣሪያና የግድግዳ ግብር አሰባሰብን ማጠናከር፣ የሊዝ ክፍያዎችን በወቅቱ ማስፈጸም፣ የቁርጥ ግብር ክፍያዎችን በአግባቡ መለየትና ማሰባሰብ፣ የገጠር መሬት አጠቃቀም ንቅናቄን ወደ ተግባር ማሸጋገር እንዲሁም መደበኛ ገቢዎችን በተቀናጀ አሠራር መሰብሰብ በዋናነት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው።

የሰሜን ቤንች ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ትግሉ ኡኩሪያአብ በመድረኩ እንደገለጹት፣ በወረዳው የገቢ አሰባሰብ ሂደትን ይበልጥ ለማሳለጥ፣ የአሠራር ቅልጥፍናን ለማሳደግና የታቀዱ ገቢዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት በቁርጠኝነት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ ትግሉ አክለውም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በሥራ አፈጻጸሙ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ የቀጣይ ሥራ አካል በማድረግ ለማረም በትኩረት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

የወረዳውን የመሠረተ ልማት ፍላጎቶች በተገቢው ሁኔታ ለመመለስና የመንግሥትን ወጪዎች በራስ ገቢ ለመሸፈን የገቢ አሰባሰብ ወሳኝ ሚና እንዳለው ያስገነዘቡት ኃላፊው፣ ይህንንም ለማሳካት ባለሙያዎችና ተጠሪ አካላት በቁርጠኝነት፣ በተጠያቂነትና በተቀናጀ አሠራር ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ የ90 ቀናት የገቢ አሰባሰብ ትኩረት በወረዳው የገቢ አቅምን ለማሳደግ፣ የታቀዱ ገቢዎችን ለማሳካትና የማኅበረሰቡን የልማት ፍላጎቶች ለመደገፍ የሚያስችል ውጤታማ አሠራር እንዲጠናከር ያለመ ነው።
ዘገባው የወረዳው የመንግስት ኮምንኬሽን ነው።

የገቢ አሰባሰብን ለማቀላጠፍና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ሕግን ለማስከበር የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደረሰጥቅምት 09/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በዳውሮ ዞን በኢኮኖሚው ከሚመነጨው...
19/10/2026

የገቢ አሰባሰብን ለማቀላጠፍና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ሕግን ለማስከበር የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደረሰ

ጥቅምት 09/2019 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በዳውሮ ዞን በኢኮኖሚው ከሚመነጨው ሀብት ላይ ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ በሚቻልበት እና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ሕግን በማስከበር ዙሪያ ያተኮረ ሰፊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በውይይቱም በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ መከናወን ስላለባቸው ዋና ዋና ተግባራት ላይ አቅጣጫም ተቀምጧልም።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደገለጹት ለመደበኛ እና ለማዘጋጃ ቤት ገቢዎች ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል በማለት የገቢ ኮሪደሮችን በጥልቀት በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመደበኛ ገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ መሥራት እንዳለበትም አቶ ዳዊት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የዳውሮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስፋው ደሳለኝ በበኩላቸው ማኅበረሰቡ ማንኛውንም ግብይት በሚፈጽምበት ወቅት ደረሰኝ ጠይቆ የመውሰድ ዜጋዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም ገልጸዋል።

ደረሰኝ በማይሰጡ ግብር ከፋዮች ላይ ግን ጥብቅ የሆነ የሕግ ማስከበር ሥራ እንደሚሠራም ምክትል አስተዳደሩ አስገንዝበዋል።

የዳውሮ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ አበሻው ጉተማ በበኩላቸው በተለያዩ ምክንያቶች የደረጃ ‘ለ’ ግብር ግዴታቸውን ሳይወጡ የቆዩ ግብር ከፋዮች ተጨማሪ ጊዜ ሳይጠብቁ በአስቸኳይ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የማዘጋጃ ቤት ገቢን በተመለከተም በወጣው አዲስ የታሪፍ ምጣኔ መሠረት በትኩረት መሥራትና ገቢውን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀረቡት አቅጣጫዎች ላይም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ዘገባው የዳውሮ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ነው

Address

Mizan Teferi

Telephone

+251900452940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Revenue Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Southwest Revenue Bureau:

Shortcuts

Share