Debub Bench Woreda Education Office

Call Directions

Debub Bench Woreda Education Office Debub Bench Woreda Education Office (የደቡብ ቤንች ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ?

25/08/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ከምሽት 1፡00 ጀመሮ ማየት ይቻላል።

የሀገረ አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የሚታይባቸውን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቱ የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉም አሳውቋል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

አያይዞም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን ምአገልግሎቱ ያሳውቃል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

23/08/2026

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ማጠቃለያ
************

👉100% ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
2017 ዓ.ም፦ 62 ትምህርት ቤቶች
2018 ዓ.ም፦ 88 ትምህርት ቤቶች

👉ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች
2017 ዓ.ም፦ 1,232 ትምህርት ቤቶች
2018 ዓ.ም፦ 565 ትምህርት ቤቶች

👉የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science)
ወንድ፦ 591.6 ከኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (አዳማ)
ሴት፦ 583.0 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት (እንጅባራ)

👉የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science)
ወንድ፦ 576.25 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ (ኦሮሚያ)
ሴት፦ 569.10 ከሱፐር ሆሊ ሴቪየር (አዲስ አበባ)

ምንጭ፡- የትምህርት ሚኒስቴር

*የ2018 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች በወረዳ ደረጃ የተጠቃለለ ውጤት ትንተና መግለጫ* ¶ መደበኛ (ቀን ተማሪዎች) ፈተና ላይ የተቀመጡ ወ= 652 ሴ = 546 ድ =119...
17/08/2026

*የ2018 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች በወረዳ ደረጃ የተጠቃለለ ውጤት ትንተና መግለጫ*
¶ መደበኛ (ቀን ተማሪዎች) ፈተና ላይ የተቀመጡ ወ= 652 ሴ = 546 ድ =1198 ከዚህ መካከል ያለፉ ወ = 435 ሴ = 336 ድ = 771 አፈፃፀም 64.36% ከ50ና በላይ ያስመዘገቡ ወ = 303 ሴ =216 ድ = 519 አፈፃፀም 43.32%
¶ የግል ተፈታኝ (ግል ተማሪዎች) ፈተና ላይ የተቀመጡ ወ= 114 ሴ = 159 ድ = 273 ከዚህ መካከል ያለፉ ወ =50 ሴ = 64 ድ = 114 አፈፃፀም 41.76% ከ50ና በላይ ያስመዘገቡ ወ = 330 ሴ =35 ድ = 65 አፈፃፀም 23.81%
¶ በሁሉም ፕሮግራም ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና ላይ የተቀመጡ ወ= 766 ሴ = 705 ድ = 1471 ከዚህ መካከል ያለፉ ወ = 485 ሴ = 400 ድ = 885 አፈፃፀም 60.16 % ከ50ና በላይ ያስመዘገቡ ወ = 333 ሴ =251 ድ =584 አፈፃፀም 39.7% ናቸው ። ከ2017 ዓ.ም አንጻር ሲነፃፀር መደበኛ ተማሪ ከ30.37% የነበረው ወደ 64.36% የግል 12.29% የነበረው ወደ 41.76% በሁሉም ፕሮግራም 26.63% የነበረው ወደ 60.16% ዕድገት አሳይቷል።

21/06/2026

Address

Debrework(ደብረወርቅ )
Mizan Teferi

Telephone

+251953676949

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debub Bench Woreda Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share