South Ethiopia Regional State Police Commission

Directions Website Contact the organization

South Ethiopia Regional State Police Commission ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው። ገፁን ላይክ ሼርና ኮሜንት በማድረግ ፖሊሳዊ መረጃዎችን በየዕለቱ ይከታተሉ! https://t.me/Southpolicecomm

የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ተግባር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ታቅዶ በመሠራቱ በክልሉ የወንጀል ድርጊት መጠን መቀነሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።ወላይታ ሶዶ መስከረ...
10/10/2026

የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ተግባር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ታቅዶ በመሠራቱ በክልሉ የወንጀል ድርጊት መጠን መቀነሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ መስከረም 30/2019 ዓ/ም(ደኢፖኮ)በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ እሩብ አመት ከባለፈው ተመሳሳይ ሩብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የወንጀል ድርጊት መቀነሱም ተገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ዘርፎች፣ምክትል ዘርፎችና ዳይሮክቶሬቶች በገኙበት ገምግሟል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ አደረጃጀት ከተዋቀረ ወዲህ የክልሉ ሰላም ማረጋገጥና የወንጀል መከላከል ተግባር የፀጥታ አባላት፣ ህብረተሰቡና የመስተዳድር አካላትን አሳትፎ በመሠራቱ በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተማማኝ ሠላምና ደህንነት ማስፈን መቻሉን ተገልጿል።

በትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር፣በወንጀል ምርመራና በተለያዩ አስተዳደራዊ ስራዎች በሩብ አመቱ የሚያበረታታ ውጤት መመዝገቡ በግምገማው ተነስቷል።

በ2019 ዓ/ም በጀት አመት ቀጣይ ጊዜያት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራባቸው አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን የአባላት አመለካከት፣ፖሊሳዊ ስነ-ምግባርና ከዘመኑ ጋር የሚሔድ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የስራ መመሪያና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ያመላከቱት ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው እንደገለጹት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና በስሩ ያሉ መዋቅሮች ከሌሎች የፀጥታ ሀይላት ጋር በመሆን ላስመዘገቡት ውጤትና በክልሉ ለሰፈነው ሰላም የፀጥታ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ይህ ሳያዘናጋን በቀጣይ ፖሊሳዊ ቁመናና ስነ-ምግባር ያለው አባል እንዲኖረን በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።

ለቀጣይ መቶ ቀናት በየዘርፉ የሚተገበሩ እቅዶች ከዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር የተዛመዱ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው በዋዛ ፈዛዛ ቲክቶክ እየሠሩ ሲለቁ የነበሩ 3 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን  የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት...
10/10/2026

የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው በዋዛ ፈዛዛ ቲክቶክ እየሠሩ ሲለቁ የነበሩ 3 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት አባላቱ ከፖሊስ ደንብና መመሪያ ባፈነገጠ መልኩ የተከበረውን የደንብ ልብስ ለብሰው በቲክቶክ ፌዝ ና ቀልድ በመልቀቅ የተቋሙን ክብር ና ዝናን በሚያስንቅ ተግባር በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፃ መሠል ተግባር ላይ የተሠማሩ የፖሊስ አባላት ላይም ጥብቅ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።

ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃበባሳለፍነው አንድ ሳምንት 9 የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክቶሬት አስታወቀ።ወላይታ ...
08/10/2026

ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃ

በባሳለፍነው አንድ ሳምንት 9 የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክቶሬት አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ መስከረም 28/2019 ዓ.ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ) አደጋው የደረሰው በክልሉ ስር በሚገኙ 7 ዞኖች መሆኑ ተገልጿል።

በደቡብ ኦሞ ዞን በተለያዩ ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሁለት ሰው ላይ ሞት ሲያስከትል አንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱን ከተላከልን መረጃ ማወቅ ተችሏል።

በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ አካባቢ ከአርባምንጭ ወደ ዘይሴ ሲንቀሳቀስ የነበረው ላንድኩሬዘር የፖሊስ ተሽከርካሪ እግረኛ ገጭቶ 1ሰው ሞትና1 ሰው ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ ጥንቃቄ ጉድለት እንደሆነ መረጃው ተናግሯል።

በጌዴኦ ዞን በተለያዩ ሁለት ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ አራት ሞት ሊያደርስ ችሏል።

በኮንሶ ዞን ከጎሜ ቀበሌ ወደ ባስቃ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሞተር ሳይክል እግረኛ ገጭቶ 1ሰው ላይ ሞትና 1 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ የተላከልን መረጃ ያመላክታል።

በወላይታ ዞን ከወላይታ ወደ ቦዲቲ ሲንቀሳቀስ የነበረ የጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪ ከጭነት ኤፌሳር ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ 1 ሰው ላይ የሞት አደጋ ያደረሰ መሆኑ ታውቋል።

በጎፋ ዞን ከመሎ ወደ ማዜ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪ እግረኛ ገጭቶ 1 ሰው ላይ የሞት አደጋ ያደረሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ ጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን መረጃው ያሳውቃል።

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቻ ቀበሌ አካባቢ አርባምንጭ ከተማ ውስጥ ለውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የከተማ ታክሲ ተገልብጦ 10 ሰው ላይ ቀላል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ ጥንቃቄ ጉድለት ነው ተብሏል።

የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!!

በሪፖርተር ፅጌረዳ እያሱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው የተመራ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር ልዑክ በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ በፀጥታ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ ...
06/10/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው የተመራ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር ልዑክ በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ በፀጥታ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ድንገት በተከፈተ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ አባላት ቤተሠቦችን በስፍራው ተገኝተው አጽናንተዋል።

ወላይታ ሶዶ መስከረም 26/2019 ዓ/ም(ደኢፖኮ)

መስከረም 17/2019 ዓ/ም በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ውስጥ ለኢንቨስትመንት በተሠጠ የእርሻ መሬት አካባቢ ድንገት በተፈጠረ ግጭት ፀጥታ ለማስከበር የተሠማሩ 10 የፀጥታ አካላት ተሠውተዋል።

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው የተመራው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማኔጅመንት በወረዳው ተገኝቶ የሟች ቤተሠቦችን አጽናንቷል።

በዚሁ ወቅት ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው እንደገለጹት ሰላም ለማስከበር በተሠማራ የፀጥታ ሀይል ላይ ያጋጠመው አደጋ ማስተዋል የጎደለው ሊሆን የማይገባውና ሁሉም የሚያወግዘው እኩይ ተግባር ነው ብለዋል።

ፖሊስ የዚህን ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ለማስጠየቅ እየተሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት ተለይተው በህግ አግባብ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለተከበረው የፖሊስ ሞያ ታምነው በማገልገል ላይ እያሉ የህይወት ዋጋ የከፈሉ አባላቶቻችን በተቋማችን ሁሌም የሚዘከሩ ጀግኖቻችን መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሟች ቤተሠቦችን የመደገፍና የማቋቋሙ ስራ ኮሚሽኑ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

በማጽናኛ ፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ፖሊስ ማኔጅመንት፣ የጋሞ ዞን አስተዳደር ሀላፊዎችና የፖሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።

ለሟቾች ነብስ ይማር በማለት ለቤተሠቦቻቸውና ለክልሉ ፖሊስ አባላት ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ወቅታዊ ዞናዊ የሰላም ሁኔታ ላይ ዉይይት በማድረግ የቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ አቅጣጫ ተቀመጠወላይታ ሶዶ መስከረም 25/2019 ዓ/ም (ደኢፖኮ)የጌዴኦ ዞን ፖሊስ በወቅታዊ እና ትኩረት በሚያ...
05/10/2026

ወቅታዊ ዞናዊ የሰላም ሁኔታ ላይ ዉይይት በማድረግ የቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ አቅጣጫ ተቀመጠ

ወላይታ ሶዶ መስከረም 25/2019 ዓ/ም (ደኢፖኮ)

የጌዴኦ ዞን ፖሊስ በወቅታዊ እና ትኩረት በሚያሻቸዉ ፖሊሳዊ ተግባራት ዙሪያ ከፖሊስ አመራሩ ጋር ዉይይት አድርጓል።

በዉይይቱም ወቅቱ አርሶ አደሩ ምርቱን የሚሰበስብበት እንደመሆኑ መጠን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ምርቱን ሰብስቦ እንዲያጠናቅቅ ፖሊስ በኃላፊነት መስራት ይገበዋል።

ወቅቱን እንደምቹ አጋጣሚ በመቁጠር የወንጀል ድርጊቶች በስፋት የሚፈጸሙ ስለሆነ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የወንጀል መከላከል ስራዎችን በቅንጅት መስራት ይገባል ተብሏል።

በወቅቱ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን በፍጥነት በማስቆምና ጥራት ያለ የወንጀል ምርመራ በማድረግ ተገቢዉን ፍትህ በአጭር ግዜ እንዲያገኝ በትኩረት ሊሰራ ይገባል።

የመረጃ ስርዓቱን በማዘመን ቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ ላይ በማተኮር ዉጤት ያለዉን ስራ መስራት ዉጤቱ ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል።

መድረኩን የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ብሩ ማርቆስና የዞኑ ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ መርተዉታል።

በዉይይቱም የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ አጠቃላይ ማናጅመንት አመራሮች እንዲሁም የታችኛዉ ፖሊስ መዋቅሮች አዛዦች እና ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አስተባባሪዎች ተገኝተዉበታል።

በቡሌ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች የቀድሞ ሚሊሻ አባላትን በማጣራትና አዳዲስ አባላትን በማደራጀት የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ለማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።‎ወላይታ ሶዶ መስ...
02/10/2026

በቡሌ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች የቀድሞ ሚሊሻ አባላትን በማጣራትና አዳዲስ አባላትን በማደራጀት የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ለማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።
‎
ወላይታ ሶዶ መስከረም 22/2019 ዓ.ም (ደኢፖኮ)
‎
‎በወረዳ በሁሉም ቀበሌ በዚህም ሂደት 387 የሚሊሻ አባላት ተመልምለውና ተደራጅተው መሠረታዊ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
‎
‎ስልጠናው አባላቱ በአካባቢያቸው ሰላምና ጸጥታን በማስከበር፣ ህግና ሥርዓትን በማስፈን እንዲሁም ከህዝቡ ጋር በቅንጅት የሚሰሩበትን አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑ የቡሌ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ፉላሳ ገልጿል።
‎
‎የሚሊሻ አባላት በአካባቢው ሰላምና ጸጥታ እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ለሚከናወነው የሰላም ሥራ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማበርከት መሆኑም ተጠቁሟል።
‎
‎በወቅቱ የቡሌ ወረዳ ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ነጋሽ መኩሪያ እንደገለጹት በቀጣይም ሚሊሻ አባላቱ የሚሰጣቸውን ስልጠና በአግባቡ በመጠቀም ለአካባቢው ሰላምና ልማት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።

ቡሌ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን

ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃባሳለፍነው አንድ ሳምንት 3 የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።ወላይታ ሶዶ...
01/10/2026

ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃ

ባሳለፍነው አንድ ሳምንት 3 የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ መስከረም 7/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ) አደጋው የደረሰው በክልሉ ስር በሚገኙ 3 ዞኖች መሆኑ ተገልጿል።

ባሳለፍነው አንድ ሳምንት በጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ ተገልብጦ 4 ሰው ላይ ሞት 12 ሰው ላይ ከባድ አደጋ ሲያስከትል 27 ሰው ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱ ከተላከልን መረጃ ማወቅ ተችሏል።

በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ እግረማ ዌቀ ቀበሌ ከአርባምንጭ ወደ ዳራማሎ ሲንቀሳቀስ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍኤሳር ተሽከርካሪ ከባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል ጋር ተጋጭቶ በ1 ሰው ላይ የሞት አደጋ አስከትሏል ተብሏል።

ሌላው አደጋ በወላይታ ዞን በዴሳ ከታማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ከጎፋ ወደ አዲስ አበባ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኤፍኤሳር የጭነት ተሽከርካሪ ከአይሱዚ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል ተብሏል።

ወንጀልና የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!!

በሪፖርተር ፅጌረዳ እያሱ

16 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒት መያዙን የኮንሶ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ**** ወላይታ ሶዶ መስከረም 21/2019 ዓ.ም (ደኢፖኮ) የኮንሶ ዞን  ፖሊስ  በህ...
01/10/2026

16 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒት መያዙን የኮንሶ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ
****

ወላይታ ሶዶ መስከረም 21/2019 ዓ.ም (ደኢፖኮ)

የኮንሶ ዞን ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒቱ መስከረም 21 ቀን2019 ዓ/ም ለሊት 11:30 ላይ በባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ተጭኖ ከከና ወረዳ መስመር ወደ ካራት ከተማ ሊገባ ሲል ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋል ችሏል።

በፖሊስ በህግ ቁጥጥር ሥር የዋለው ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒት ግምቱ 16,000,000 (አስራ ስድስት ሚሊየን)ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ህገ ወጥ የሰው መዲኃኒቱ ወደ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮንሶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ገቢ የተደረገ ሲሆን ፖሊስ የህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎአል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ውስጥ ፖሊሳዊ ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ላይ ድንገት በደረሰ ጥቃት ህይ...
01/10/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ውስጥ ፖሊሳዊ ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ላይ ድንገት በደረሰ ጥቃት ህይወታቸውን ባጡ አባላት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ይህንን እኩይ ተግባር የፈፀሙ አካላትን ተከታትሎ በመያዝ እንዲጠየቁ የማድረጉን ስራ እየተሠራ እንደሆነ ገልጾ ህይወታቸው ባለፈ የፀጥታ ሀይሎች የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የክልሉ ፖሊስ አባላት መጽናናትን ይመኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን።
21/2019 ዓ/ም(ደኢፖኮ)

ዜና ችሎት የጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል በመፈፀም ድርጊቱን በመቅረጽ በቲክ ቶክ ያሰራጨ ተከሳሽ  በሃያ ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ ።ወላይታ ሶዶ ፣ መስከረም ...
29/09/2026

ዜና ችሎት

የጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል በመፈፀም ድርጊቱን በመቅረጽ በቲክ ቶክ ያሰራጨ ተከሳሽ በሃያ ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ ።

ወላይታ ሶዶ ፣ መስከረም 19/2019 ዓ.ም (ደኢፖኮ)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍ/ቤት ጠለፋና የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል በመፈጸም በቲክቶክ ቪዲዮ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ ላይ ሃያ ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ተከሳሽ መልካሙ ዳዊት ዕድሜ 18 ሲሆን ነሐሴ 24/2018ዓ.ም ዕለተ ዕሁድ የግል ተበዳይን ለጊዜው በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከምዕራብ ዓባያ ወረዳ (ቆላ ባራና ቀበሌ) ጠልፎ በመውሰድ ጫካ ውሰጥ በማስገባት አስገድዶ የመድፈር ሙከራ በማድረግ ቪዲዮ ቀርጰው በቲክቶክ የፖሰቱ ሲሆን ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል ተከሳሹን በሠላምበር ከተማ ከተሸሸገበት በቁጥጥር ስር አውሎታል።

ምርመራውንም በአግባቡ አጣርቶ ለሚመለከተው የህግ አካል ልኳል።

የዚህን ወንጀል የማርመራ መዝገብ የደረሰው አቃቤ/ህግም መዝገቡን ከመረመረ በኃላ በተከሳሽ ላይ በክስ 1 የኢፌዴሪን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 587 (1) እና በክስ
2 የኢፌዴሪን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620 (2)መን በመተላለፍ ክስ በመክፈት የሰው የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃ አደራጅቶ ለምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል።

በዚህ መሠረት ተከሳሽ አቃቢ /ህግ ያቀረባቸውን የሰው የሰነድ የቪዲዮ ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሰሰባቸው በሁለቱም ክሶች ጥፍተኛ በማለት መስከረም 19/2019ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችን ከመሰል ድሪጊት እንዲቆጠቡ ያደረጋል ያለውን 22 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።

መስከረም 19ቀን 2019 ዓ.ም
የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍርድ ቤት

Address

Wolaita
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional State Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Ethiopia Regional State Police Commission:

Shortcuts

Share