Yeki Woreda Communications

Call Directions

Yeki Woreda Communications Teppi

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ******************* የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳ...
05/10/2026

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ
*******************

የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሐሙድ፣ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዳግም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የአገልግሎት ዘመናቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የሶማሊያ እና ኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።

የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ ቀጠናን ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር በጥብቅ ትብብር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

! ! !

#የመደመርመንግሥት

የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መናገሪያ ቋንቋ መሆኑን አረጋግጠናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (ዶ/ር)
05/10/2026

የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መናገሪያ ቋንቋ መሆኑን አረጋግጠናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ...
05/10/2026

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ 7ኛውን ምርጫ በቀላሉ እንዳልመረጠ ጠቁመዋል።

ነገር ግን ህልውናውን ለማጽናት ፈተናዎችን ሁሉ በጽናት አልፎ ውሳኔውን ማሳወቁን እና በዚህም ጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት ለመሥራት የሚያስችል መሠረት መጣሉን ገልጸዋል።

ዓለም በተለያየ መልኩ እየተቀያየረች እና አይገመቴነት በሰፈነበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ወሳኝ ሥራ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ማንኛውም አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ዓለም በርካታ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ሲያሳልፍ ለሀገራችን የደረሳት ትራፊው ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደ ሀገር ቀድሞ ካለመዘጋጀት የሚመጣውን ችግር ለመቋቋም አሁናዊ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

! ! !

ዓለም አዲስ መልክና ቅርጽ ለመያዝ እየታገለች ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ቶሎ የነቁና ዝግጁ አቅም የገነቡ ሀገራት ማሸነፋቸዉ አይቀሬ ነዉ፡፡ እኛ አዲሱን የመደመር መንግሥት የምንመሰርተዉና የህዝብ ተ...
05/10/2026

ዓለም አዲስ መልክና ቅርጽ ለመያዝ እየታገለች ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ቶሎ የነቁና ዝግጁ አቅም የገነቡ ሀገራት ማሸነፋቸዉ አይቀሬ ነዉ፡፡

እኛ አዲሱን የመደመር መንግሥት የምንመሰርተዉና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባዔዉን የምንጀምረዉ ዓለም በዚህ የለዉጥ ንፋስ እየተመታ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

! ! !

"በሕጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው በድምፃቸው ቅቡል መንግሥት ለማፅናት በተግባር ለታመኑ 54 ሚሊዮን ዜጎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር...
05/10/2026

"በሕጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው በድምፃቸው ቅቡል መንግሥት ለማፅናት በተግባር ለታመኑ 54 ሚሊዮን ዜጎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

! ! !

አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ  7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።...
05/10/2026

አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም አቶ አሕመድ ሽዴን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም  በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ...
05/10/2026

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።

በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች ስንጓዝ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓለማችን በፍጥነትና በማይገመት ሁኔታ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መጪውን ዘመን በተጠንቀቅ መጠበቅ ትልቅ ምንዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።

ስለዚህም ለሀገር የሚበጀውን በጥበብ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቅ አደራ መሆኑን በንግግራቸው አስተላልፈዋል።
‎
‎
‎

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።




#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙአዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ በሆነው ብልጽግና ፓርቲ እጩ ተደርገው የቀረቡት የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
ኤፍ ኤም ሲ

አቶ አልማው ዘውዴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ተሾሙአቶ አልማው ዘውዴ በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አስተምህሮ ኮሚቴ ጸ...
05/10/2026

አቶ አልማው ዘውዴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ተሾሙ

አቶ አልማው ዘውዴ በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አስተምህሮ ኮሚቴ ጸሐፊ ሆነው ተሹመዋል።

Address

Tepi

Telephone

+251984910016

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeki Woreda Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share