Kolfe keranyo sub-city Woreda 06 Communication office

  • Home
  • Kolfe keranyo sub-city Woreda 06 Communication office
Call Directions Website Contact the organization

Kolfe keranyo sub-city Woreda 06 Communication office This is official page of Kolfe Keranio Woreda 6 Communication office

Official news,Public announcement,community update& government information

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በ27ቱም የቅዳሜና  እሁድ ገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ምርቶች በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርበዋል።በቀን 28-29/2019 ዓ.ም የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር...
07/11/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በ27ቱም የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ምርቶች በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርበዋል።

በቀን 28-29/2019 ዓ.ም የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል ነዋሪዎቻችን በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የገበያ አማራጭ በተጠቀሰው ዋጋ ኑ ሸምቱ በማለት የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

“የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ  አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ  መድረክ ማስተናገዷ  ለሁላችንም ታላቅ  ኩራት  ነው”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር).
06/11/2026

“የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር).

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ትምህርት ጽሕፈት ቤት ባለፉት ሦስት ወራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተቋማዊ አፈጻጸምን ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ...
06/11/2026

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ትምህርት ጽሕፈት ቤት ባለፉት ሦስት ወራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተቋማዊ አፈጻጸምን ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ኮልፌወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 27/ 2019

ጽሕፈት ቤቱ ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነትን እውን ለማድረግ፣ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ለማጠናከር እንዲሁም ዘመናዊ አሰራሮችን በመዘርጋት ብቁ ትውልድ ለማፍራት በትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እዬብ ተ/ማርያም እንደገለጹት፤ ባለፉት የሩብ ዓመት ጊዜያት የመልካም አስተዳደር አሰራሮችን ከማስፈን፣ የሪፎርም ስራዎችን ከመተግበር እና ከተቀመጡ ስትራቴጂካዊ ግቦች አንጻር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ኃላፊው አክለውም በፅህፈት ቤቱ አማካኝነት በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቅንጅት ለመቅረፍ፣ የትምህርት ሽፋንን ለማስፋት እና አዲስ የሚመጡ ህጻናትን ተቀብሎ ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ስታንዳርድ እንዲያሟሉ የማያቋርጥ የሙያዊ ድጋፍና ክትትል የተደረገ ሲሆን፤ የዕቅድ አፈጻጸሞችን ከትምህርት ቤት መሪዎች ጋር በየወሩና በየሩብ ዓመቱ በመገምገም ክፍተቶችን በጊዜው የማስተካከል ስራዎች መከናወናቸውን አቶ እዬብ ተ/ማርያም አብራርተዋል።

የወረዳው አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከፍተኛ መሻሻል ማሳየታቸውን ተገልጋዮች ገለጹ!ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም በኮልፌ ቀ...
06/11/2026

የወረዳው አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከፍተኛ መሻሻል ማሳየታቸውን ተገልጋዮች ገለጹ!

ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለህብረተሰቡ የተሰጡት ሁለገብ አገልግሎቶች ፈጣንና ቀልጣፋ መሆናቸውን እንዲሁም የታዩ መሻሻሎች አበረታች መሆናቸውን የአካባቢው ተገልጋዮች ገለጹ።

ተገልጋዮች በሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል ይወስዱ የነበሩ ረጅም ቀጠሮዎችና መዘገዮች ተቀርፈው አገልግሎቶች በአንድ ማዕከልና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ መደረጉ እና የአገልግሎት ሰጪ አካላት እንግዶችን በክብር የመቀበልና ግልጽ መረጃ የመስጠት ባህል ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳየ ገልጸዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ የወረዳው ነዋሪዎች እአያይዘው እንደገለጹት፤ በአገልግሎት ቀን በተደረገው ልዩ ዝግጅት የሚፈልጉትን ጉዳይ ያለ ምንም እንግልት ማጠናቀቃቸውን ጠቅሰው፣ ይህ ዓይነቱ ቀልጣፋ አሰራር በተደበኛ የሥራ ቀናትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

 #በብዛህነት የደመቀች በምክክር የፀናች ሀገር በሚል መሪ ቃል የብሄር ብሄረሰብ ቀን አስመልክቶ ፖናል ውይይት ተደረገ።ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽንበኮልፌ ቀራንዮ ክ...
05/11/2026

#በብዛህነት የደመቀች በምክክር የፀናች ሀገር በሚል መሪ ቃል የብሄር ብሄረሰብ ቀን አስመልክቶ ፖናል ውይይት ተደረገ።

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ምክር ቤት እና ፐ/ሰ/የሰ/ሃ/ልማት ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል"በብዛህነት የደመቀች በምክክር የፀናች ሀገር " በሚል መሪ ቃል የወረዳዉ ሰራተኞች ጋር በፓናል ዉይይት ተካሄደ፡፡

በዉይይቱ ላይ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ኢሳያስ ፈቀደ እንዳሉት፡- የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበትን ህዳር 29 ቀን ለመዘከር እለቱ በየዓመቱ የብሔረሰቦች ቀን ሆኖ እንዲከበር በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዚያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም የተወሰነበትን ቀን በማሰብ፤ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች በየዓመቱ በመከበሩ በአገራችን የሚገኙ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት በሚገባ እንዲታይና እንዲታወቅ በማድረግ ረገድ የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል፡፡

በተለይም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከርና ባህላቸው፣ አልባሳቶቻቸው፣ እሴቶቻቸውን በማስተዋወቅ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የበዓሉ ሚና የላቀ መሆኑን ዋና አፈ-ጉባኤዉ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የበዓሉ መከበር ዋነኛ ፋይዳ በአገራችን ሕገ መንግስትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ዙሪያ ህብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ በህዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ የመኖር ኢትዮዽያዊ እሴቶችን ጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ዘንድሮ የሚከበረው በዓል ዋናው ትኩረት፡- የሀገራችን ህዝቦች የጋራ ትስስር በማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት ግንባታ ሂደት እንደ ወረዳ የበኩሉን እንደሚያበረክት የሚጠበቅ ሆኖ ይህ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ሁሉም ተቋማት የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ አፈ-ጉባኤዉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ለፓናል ውይይቱ መነሻ እንዲሆን ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም ባለድርሻ አካላት በቀረበዉ ሰነድ ላይከተወያዮ በኋላ የጋራ ተግባቦት ተፈጥሮ የፓናል ዉይይቱ ፍፃሜ ለመሆን ችሏል።

አለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ቀዳሚ መዳረሻ ከተማ አዲስ አበባአዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች እያስመሰከረ...
05/11/2026

አለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ቀዳሚ መዳረሻ ከተማ አዲስ አበባ

አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች እያስመሰከረች ትገኛለች።

የከተማዋ ዕምቅ ሀብትና አቅም መሰረት በማድረግ የተገነቡ በርካታ መሰረት ልማቶች ለበርካታ ታላላቅ ስብሰባዎችና ኮንፈረንሶች ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።

በተለይም በከተማዋ የተገነቡ ውብ የኮሪደር ልማት የእግረኛ፣ የተሽከርካሪና የሳይክል መንገዶች፣ ንፁህ አረንጓዴ ሥፍራዎች ለዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶች እና ጉባኤዎች ተመራጭ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ መዲናዋን ለነዋሪዎች እንዲሁም አለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ውብ እና ምቹ ትሆን ዘንድ በተከናወነው ዘርፈ ብዙ ግዙፍ የልማት ስራ በዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አዘጋጆች ዘንድ ያላትን ተመራጭነት ከፍ እንዲል አድርጓል።

በተጨማሪም ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተገነባው አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር እና አደዋ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች ትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖችን በኩራት ማስተናገድ የሚያስችሉ ስፍራዎች ለከተማዋ ተጨማሪ አቅም የፈጠሩ ናቸው ፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከዋና ከተማነት በላይ የሆነች በፈጣን ለውጥ ላይ ያለች እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች መስህብ እና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ መዲና በመሆን እራሷን የለወጠች ከተማ ለመሆን ችላለች፡፡

በባሌ ዞን የክረምት እርሻ አፈጻጸምን ተመልክተናል። በዘንድሮው ክረምት ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሥጋት የነበረ ቢሆንም በመንግሥትና በሕዝብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መልካም የሚባል  አፈጻጸም ተመዝ...
04/11/2026

በባሌ ዞን የክረምት እርሻ አፈጻጸምን ተመልክተናል።
በዘንድሮው ክረምት ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሥጋት የነበረ ቢሆንም በመንግሥትና በሕዝብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መልካም የሚባል አፈጻጸም ተመዝግቧል። ኢኮኖሚያችን አይበገሬ ሆኖ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን እንዲቋቋም፣ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር).

አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ በርካታ ተግባራትን በማከናውን ላይ ትገኛለች: መዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ...
04/11/2026

አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ በርካታ ተግባራትን በማከናውን ላይ ትገኛለች:

መዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ዘርፉን ወደ ታዳሽ ሃይል በመለወጥ በርካተ ተግባራትን በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ በተለይም አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያን የሲቪል መሠረት የሚያጠናክር የተፈጥሮ ሀብቶችን መጠቅም የሚያስችል ታሪካዊ የሆነ የኢነርጂ ሽግግር በማድረግ ምሳሌ መሆን ችላለች ፡፡.

በዚህ አዲስ ታሪካዊ በሆነ ሽግግር መዲናችን አዲስ አበባ በቅርቡ 26 የከተማ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ በመለወጥ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች።.

ይህ ታሪካዊ ሽግግር የሕዝብ ትራንስፖርትን ወጪ በመቀነስና የአየር ብክለትን በማስቀረት፣ የኢኮኖሚ አቅም በመደገፍ፣ ቀደም ሲል ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ወጪ በመቀነስ፣ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቆጠብ የሀገርን ሀብት ከወጪ በማዳን የዜጎችን ኑሮ በማቅለል ፤የጉዞ ታሪክ በመቀንስ እንዲሁም የትራንስፖርት አቅርቦትን ችግር በመፍታት፣ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ለውጥ በማምጣት ዋጋን በማረጋጋት እና ለኢንዱስትሪዎችና አምራቾች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የሀገርን እድገት ከፍ ወዳለ ስልጣኔ ማድረስ ያስችላል ።.

ከዚህ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናሎችን በተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች በመገንባትና ለኤሊክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጃርጅ ማድረጊያ ቦታዎችን በየቦታዉ በመገንባት በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ህብረተሰቡን ከዝናብና ፀሀይ በመከላከል የትራንስፖርት ፍሰትን በማሳለጥ ፣ የትራፊክ አደጋን መቀነስን ጨምሮ ለዘርፋ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ያመላክታል ።.

በቀጣይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ መጨናነቅን በከፍተኛ ደረጃ የሚያቃልሉና የትራንስፖርት ፍሰቱን የሚያሳልጡ የነዋረውን ጊዜ የሚቆጥቡ ተጨማሪ አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ቁጥራቸው 400 የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎችን በመገንባት መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በተግባር በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡.

በወረዳው የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ምቹ መሆናቸውን ባለጉዳዮች በሰጡት አስተያየት ገለፁ።ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 25/2019 ዓ.ምበኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተ...
04/11/2026

በወረዳው የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ምቹ መሆናቸውን ባለጉዳዮች በሰጡት አስተያየት ገለፁ።

ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር አገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ያነጋገርናቸው ባለጉዳዮች እንደገለፁት የሚሰጡ አገልግሎቶች ከዚህ ቀደሙ በየጊዜው እየተሻሻሉ በመምጣታቸው ጊዜያችንንና ድካማችንን ቀንሶልናል ሲሉ ተናግረዋል።፥

የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የአገልግሎት ቀናት የሆኑትን ረቡዕ እና አርብን ምክንያት በማድረግ በተቋማቱ ምልከታ ያደረገ ሲሆን ተገልጋዮችንም አነጋግሯል።

በምልከታው ወቅትም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከዚህ ቀደሙ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ምቹ መሆኑን የገለፁልን ሲሆን አገልግሎቶች ከበፊቱ አንፃር በጣም መሻሻሎች መኖራቸውን ገልፀውልናል።

ተገልጋዮቹ አክለውም፣ በአገልጋይና በተገልጋይ መካከል ያለው የመረጃ ተደራሽነት መሻሻሉንና መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት መቻላቸው ጊዚያቸውን እየቆጠበላቸውና እንግልቶችን እየቀነሰ መምጣቱን ጠቁመዋል።

በተለይም የወረዳው አስተዳደር የተገልጋይን ምልልስና ምሬት ለመቀነስ እየሰራ ያለው ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ገልፀዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ምክር ቤት 2ኛ የምርጫ ዘመን 14ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሔዷል። ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽንጥቅምት 24/2019 ዓ.ምየኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተ...
03/11/2026

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ምክር ቤት 2ኛ የምርጫ ዘመን 14ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሔዷል።

ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ምክር ቤት 2ኛ የምርጫ ዘመን 14ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን የወረዳ አመራሮች፣ አስፈፃሚ አካላት፣ የምክር ቤት አባላት እንዲሁም የክብር እንግዶች በተገኙበት 2ኛ የምርጫ ዘመን 14ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።

በጉባኤው ላይም የወረዳው ምክር ቤት በዛሬው ውሎው የ2ተኛ ምርጫ ዘመን 13ኛ ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ላይ ውይይት በማካሔድ የማፀደቅ የወረዳ አስተዳደሩን የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የምክር ቤት ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የምክር ቤት አባላት ላነሱት ጥያቄና አስተያየት የወረዳው አስፈጻሚ አካላትና የወረዳው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እንድሪስ ይማም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የወረዳው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እንድሪስ ይማም የወረዳ አስተዳደሩ በርካታ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በስራ እድል ፈጠራ የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማጠናከር አንጻር፣ ከሌማት ቱሩፋት ፣የኑሮ ውድነትና ገበያን ለማረጋጋት የእሁድ ገበያ ማጠናከር፣ ቸመብራትና ውሀ አቅርቦት፣ በሰላምና የፀጥታ ስራዎች የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የተከወኑ ተግባራት አፈፃፀማቸው የተሻለ እንደነበር አመላክተዋል።

አክለውም የወረዳ አስተዳደሩ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች ለመደገፍ ምክር ቤቱ እያደረጉ ያሉ ጥረቶችን ያመሰገኑ ሲሆን በጉባኤው የተነሱ ጥያቄዎችንና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ የልማት የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በቀጣይ የወረዳው አስተዳደር የትኩረት መስክ አድርጎ እንደሚሰራ እና የምክር ቤት አባለት ከአስተዳደሩ ጎን ሆነው የተለመደውን ድጋፍ እንዲሰጡና የተሻሉ ሰራዎችን መከወን እንድንችል ሲሉ አሳስበዋል።

Address

Bethel

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe keranyo sub-city Woreda 06 Communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kolfe keranyo sub-city Woreda 06 Communication office:

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed government service?

Share