Alazar Behayilu

  • Home
  • Alazar Behayilu
Call Directions Website Contact the organization

Alazar Behayilu The kingdom of heaven Ministry

28/02/2026

❤ ❤
-----------------------
✍️መጽሐፍ ቅዱስ በቅዱሳን መካከል ሊኖሩ የሚገቡ መልካም ግንኙነቶችና ሊኖሩ የማይገቡ መልካም ያልሆኑ ነገሮች ምን መምሰል እንዳለባቸው ያስተምረናል ያዘናል።

✍️ መልካም የሆኑ ግንኙነቶች፦
---------------------
📌እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ። ቆላ 3:13
📌እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርህሩሆች ሁኑ። ቆላ 4:32
📌እርስ በርሳችሁ ምህረትን አድርጉ። ቆላ 3:16
📌እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ሮሜ 12:10
📌እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ሮሜ 15:7
📌እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ። ዕብ 10:25
📌እርስ በርሳችሁ ትህትናን ልበሱ። 1ጴጥ 5:5
📌እርስ በርሳችሁ ሰላምታን ተሰጣጡ። 1ጴጥ 5:14
📌እርስ በርሳችን ለፍቅርና ለመልካም ስራ እንተያይ።
ዕብ 10:24
📌እርስ በርሳችሁ በትህትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም በፍቅርም ታገሱ። ኤፌ 4:2

✍️መልካም ያልሆኑ ግኑኝነቶች፦
------------------------
👉እርስ በርሳችሁ ውሸትን አትነጋገሩ። ኤፌ 4:25
👉እርስ በርሳችሁ አትፈራረዱ። ሮሜ 14:13
👉እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ያዕቆ 4:11
👉እርስ በርሳችሁ አትበላሉ፣አትነካከሱ። ገላ 5:15
👉እርስ በርሳችሁ አትቀናኑ። ገላ 5:26

📌 የእግዚአብሔርን ምክሮች ሰምትን ማድረግ የምንችልበት ጸጋ ለእያንዳንዳችን ይጨመርልን።

✍️2 ቆሮንቶስ 13፡14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel truth Church Jimma

28/02/2026

❤ ??❤
================================

📌1 ቆሮንቶስ 2
15፤ መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል

✍️ይህን ጹሁፍ ያዘጋጀንበት ዋና አላማ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል እንደሚል የእግዚአብሔርን ቃል በአግባቡ እንደሚያጠና ሰው የቃሉን እውነትን ለመረዳትና ግራ ላለመጋባት የተዘጋጀ ነው። ልብ ልንል የሚያስፈልገን እውነት የቀኑ ጉዳይ ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል እንደሆነ ሁላችንም እንስማማለን።

✍️ብዙ ጊዜ የክርስትና እምነት ተከታዮች ኢየሱስ አርብ ቀን እንደተሰቀለና እንደተቀበረ ያምናሉ ከዚህም የተነሳ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ኢየሱስ 3 ቀን 3 ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ አድራለሁ ብሏል ስለዚህ ኢየሱስ አርብ ከተሰቀለና ከተቀበረ እሁድ ደግሞ በማለዳ ከተነሳ 3ቀን አይሞላም በማለት ቅዱሳንን ይሞግታሉ ቅዱሳንም ግራ ይጋባሉ።

📌 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
-------------------------

✍️“በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና፦ መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ። እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል” ማቴ. 12፡38-40

✍️ኢየሱስ ራሱ 3ቀንና 3ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ አድራለሁ ብሎ ካስተማረ ከዓርብ ማታ እስከ እሁድ ጠዋት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ሊመጣልን አይችልም።
ምክንያቱም በተራ የሂሳብ ስሌት እንኳ ብናሰላው ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ የቆየው ዓርብ ማታ፤ ቅዳሜ ቀን እና ቅዳሜ ማታ ነው። በሌላ አገላለጽ ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ ያሳለፈው በድምሩ ሁለት ሌሊቶችን እና አንድ ቀንን ብቻ መሆኑ ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ከሙታን የተነሳው እሁድ ሳይነጋ ገና በማለዳ በመሆኑ የእሁድ ዕለት የቀን ጊዜ ሊደመር አይችልምና። ይህ ደግሞ ኢየሱስ ካስተማረው ትምህርት ጋር አብሮ አይሄድም።

✍️ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቀን አቆጣጠር ብንመለከት ከጸሐይ መግብያ እስከ ጸሐይ መግብያ እንደሆነ ይታወቃል። ይህም በዘፍጥረት “መሸም ነጋም፤ አንድ ቀን” ተብሎ እንደተጻፈው ነው (ዘፍ. 1፡5፣8፣13)።

📌መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል 19
31፤ አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ _ትልቅ_ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ይላል

📌 ነበረና ይለናል ስለ ሰንበት በዘሌዋውያን መጽሐፍ ስናጠና የተለያዩ ሰንበቶች እንዳሉ ይናገራል ከሰንበቶች መካከልም የሳምንት ሰንበት ቅዳሜና በአመት አንድ ጊዜ የሚከበረው ታላቁ ሰንበት አለ። በአመት አንድ ጊዜ የሚከበረው ይህ ታላቁ ሰንበት ከሰኞ እስከ እሁዳ ባለው በአንዱ ቀን ሊያርፍ ይችላል።ስለዚህ በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ያገኘነው ሰንበት የአመቱ ሰንበት ከሆነ የሳምንቱ ሰንበት ቅዳሜ እንዳልሆነ ይነግረናል። ብዙ ክርስቲያኖች ሰንበት ስለተባለ ቅዳሜ ይመስላቸዋል ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ አርብ እንደሰቀለ አድረገው ያስባሉ ያምናሉም።እንደዛ ከሆነ ደግሞ ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ 3ቀንና ሌሊት መቆየት ላይ ጥያቄ ይፈጥራል።

✍️በተጨማሪም በተሰቀለበትና በተነሳበት 3 ቀናት መካከል 2 ሰንበቶች አልፈዋል የመጀመሪያው ታላቁ ሰንበት በማንኛውም አዘቦት ቀን ላይ የሚውለው በሞተበት ቀን ላይ ጀንበር ስትገባ የሚጀምር እና ሁለተኛው ሰንበት ቅዳሜ ሲሆን መቃብር ውስጥ ከትንሳኤው በፊት ለ3ኛ ቀን ያደረባት እስከ ጀንበር መጥለቅ የነበረችው ናት።

✍️የእግዚአብሔር ቃል እንደሚገባ ለሚያጠና ክርስቲያን በዮሐንስ ወንጌል 19:31 መሰረት ታላቁ ሰንበት ቅዳሜ እንዳልሆነ ይረዳል። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ለ3 ቀንና ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ እንዳደረና በሳምንቱ በፊተኛው ቀን (እሁድ) ሳይነጋ በሌሊት እንደተነሳ እናገኛለን። ስለዚህ ኢየሱስ በተሰቀለበት ቀን ጠዋት ከ3 ሰዓት እስከ ቀን 9 ሰዓት መስቀል ላይ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። የታላቁ ሰንበት መዘጋጀት ነበረና ስጋቸው መውረድና መቀበር ነበረበት ከዚህም የተነሳ ለ3 ቀንና ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ቆይቶ እሁድ ሳይነጋ ሌሊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተነሳ። ደግሞም እሁድ ሲነጋ በማለዳም ሴቶቹ እነመግደላዊት ማርያም የኢየሱስን ስጋ ሽቶ ለመቀባት ሲሄዱ መልአኩ ኢየሱስ ክርሰቶስ እንደ ተናገረው በ3ኛው ቀን እንደተነሳና መቃብሩ ባዶ እንደሆነ የትንሳኤውን የምስራች ይነግራቸዋል እነርሱም ለሐዋርያቱ ሐዋርያቱም ለእኛ በመጽሐፍ ጽፈው መስክረውልናል።1ቆር 15:3-4

📌1 ቆሮንቶስ 15 (1 Corinthians)
3፤ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን፡ ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፡— መጽሐፍ እንደሚል፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥
4፤ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል፡ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥

📌ሐዋ. ሥራ 2 (Acts)
31፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ።
32፤ ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤

✍️ይሁዳ 1 (Jude)
17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤

✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

📌 ማሳሰቢያ
------------------
ከዚህ በታች ባለው ቻርት ላይ መሲሐውያን አይሁድ አሁን ካሉበት ካሌንደራቸው ወደ ኋላ በመቁጠር ታላቁ ሰንበት በወቅቱ ያረፈበትን ቀን ያወቁበትና የሰሩት የወቅቱ አቆጣጠር ምን እንደሚመስል መመልከት ይቻላል።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth Church Jimma.

28/02/2026

♥ ♥
=====================

📌 (5)
-------------------

✍️እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረው ሰው ያለሕግ እና ያለመልካም ስራ በነጻ በክርስቶስ የቤዛነት ስራ በማመን በጸጋ ብቻ መጽደቅ ይችላል።

✍️ ሀጥያተኛ ሰው የሚጸድቀው ጸጋውን በእምነት በመቀበል ብቻ ነው!!!

📌ኢየሱስ ክርስቶስን በማመናችሁ በጸጋው ድናችኋል ይህም እናንተ በራሳችሁ ያገኛችሁትን ሳይሆ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
መዳን ለምናደርገው መልካም ተግባር የሚሰጥ ዋጋ አይደለም "ማንም ሰው ደህንነትና ያገኘሁትበበጎ ስራዬ ነው ሊል አይገባም"። (ሕያው ቃል) ኤፌ 2:8-9

👉 መጽሐፍስ ምን አለ፦
-----------------
📌24). የተጠራነው በክርስቶስ የጸጋ ወንጌል ነው (ገላ 1፡6)

📌25). ከጸጋ ወንጌል ውጭ የሚሰብክ ማንኛውም ፍጥረት በመለኮታዊ እርግማን ስር ነው።

ገላትያ 1 (Galatians)
8፤ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

📌26). በጸጋ ከዳንን የሕግ ሰባኪዎች አርነታችንን (ነጻነታችንን) እንዲሰልሉ ልንፈቅድላቸው ፈጽሞ አይገባም። (ገላ 2፡3-5)
ገላትያ 2 (Galatians)
5፤ የወንጌልም እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር ለአንድ ሰዓት እንኳ ለቅቀን አልተገዛንላቸውም።

📌27). የወንጌል እውነት ጸንቶ እንዲኖር ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳን ወደ ሕግ ፈቀቅ ቢሉ ሊወቀሱ ይገባቸዋል (ገላ 2፡11-21)
ገላትያ 2 (Galatians)
11፤ ነገር ግን ኬፋ (ጴጥሮስ) ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።

📌28). ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ሕግን በመፈጸም ከቶ ሊጸድቅ አይችልም፡፡

ገላ 2፡16
ነገርግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ስራ እንዳይሆን አውቀን ስጋን የለበሰ ሁሉ በህግ ስራ ስለማይጸድቅ እኛ ራሳችን በህግ ስራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል)

📌29. የእግዚአብሔርን ጸጋ መጣል አይገባም።
ገላትያ 2 (Galatians)
21፤? የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።

📌30. ጽድቅ የሚገኘው ሕግን በመፈጸም ከሆነ ክርስቶስ መሞት አያስፈልገውም ነበር።
ገላትያ 2 (Galatians)
21፤ የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።

✍️ገላትያ 2 (Galatians)
21፤ የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።

ይቀጥላል........

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጂማ
Gospel Truth Ministry Jimma.

28/02/2026

❤ #ሰባቱ #ዘመነ- #መግቦቶች
( , )❤

(4)
=====================

❤
========================

📌2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት(በትክክል)የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

❝Give diligence to present yourself approved to God, a workman unashamed, rightly dividing the Word of Truth.❞
2Tim 2: 15 (LITV)

📌4). ጋር የተደረገ ውል (Dispensation of the Promise) በዋናነት ለ 430 ዓመታት
----------------------
✍️የተስፋውቃል(ክርስቶስ )እስኪገለጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም እና ለ #ዘሩ (ለክርስቶስ) የሰጠው የተስፋ ቃል ነው። [ዘፍ 15:6 ገላ 3:6-18,
ሮሜ 4:3]።
❤በዚህ ውል እግዚአብሔር አብርሃምን፥ "በአንተ ምክንያት አሕዛብ ይባረካሉ" በማለት ወንጌል ሰብኮ ነበር[ገላ 3:8]።
ነገር ግን ይህ ተስፋ ሳይፈጸም በመሃል የሕግ ዘመን ጣልቃ ገባ። ገላ 3:16

❤ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ከአብርሀም ጋር የገባው የተስፋው ቃል በስድስተኛው ውል ላይ ይፈጽመዋል። ወደ በኋላ እናያለን።

👉ሮሜ 11 (Romans)
33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።
36፤ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ይቀጥላል...........

📌2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth Church Jimma

28/02/2026

❤ #ሰባቱ #ዘመነ- #መግቦቶች
( , )❤
------------------------
(3)

📌2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት(በትክክል)የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

❝Give diligence to present yourself approved to God, a workman unashamed, rightly dividing the Word of Truth.❞
2Tim 2: 15 (LITV)

📌3). ከኖኅ ጋር ተደረገ ውል(Dispensation of the Human government)
ለ1205 ዓመታት

✍️የውሉ ቅድመ ሁኔታ፦ እግዚአብሔር ከጥፋት የተረፉቱን ስምንት ሰዎችን ወደ አለም ሁሉ እንዲበተኑና እንዲበዙ አዟቸው ነበር [ ዘፍ 9:1-6]።

✍️ነገር ግን የሰው ልጅ እምቢ በማለት ስማቸውን የሚያስጠራ ታላቅ መንግስት ለመመስረት ብለው የባቢሎን ግምብ ለመስራት በአንድነት ተነሱ [9:20-23፤ 11-1-4]።

✍️ እግዚአብሔር ውሉን ስላላከበሩት ቋንቋቸውን በማደበላለቅ እንዲበተኑ አድርጓቸዋል [ዘፍ 11:5-9]። ይህ ውል ከዚህ በፊት እንደነበሩት ውሎች በሰዎች እንቢተኝነት ፈርሷል።

ይቀጥላል...........

❤ 2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth Church Jimma

28/02/2026

❤ #ሰባቱ #ዘመነ- #መግቦቶች
( , )❤
---------------------------------
(1)

📌2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት(በትክክል)የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

❝Give diligence to present yourself approved to God, a workman unashamed, rightly dividing the Word of Truth.❞
2Tim 2: 15 (LITV)

📌1). (Dispensation of Innocency) ከአዳም ጋር የተደረገ ውል ነው።
------------------------------

✍️አዳም ከተፈጠረ - ከአትክልቱ ስፍራ (ከኤደን ገነት) እስከተባረረ ጊዜ ድረስ ያለው ነው።

✍️ይህ ውል እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ አዳም "Innocent" ነበር። ማለትም ክፉንና ደጉን ለይቶ አያውቁም ነበር ማለት ነው።

✍️የውሉ ቅድመ ሁኔታ፦ መልካሙንና ክፉን የሚያስታውቀውን ዛፍ አለመብላት ነበር [ ዘፍ 2:15-17]። ግን ኋላ ላይ አዳም ውሉን አፈረሰ [ ዘፍ 3:6፤7] ፤

✍️ውጤቱም ፦ በመንፈስ ሞቶ ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ከኤደን ገነትም ተባሮ እናያለን [ ዘፍ 3:17-19፤ 3:22-24]።

📌ሮሜ 11 (Romans)
33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።.....
36፤ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

✍️2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

ይቀጥላል...........

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth Church Jimma

28/02/2026

❤ #ሰባቱ #ዘመነ- #መግቦቶች
( , )❤

#መግቢያ
=====================
📌2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት(በትክክል)የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

❝Give diligence to present yourself approved to God, a workman unashamed, rightly dividing the Word of Truth.❞
2Tim 2: 15 (LITV)

✍️ ልዑል እግዚአብሔር ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ አለም መጨረሻ ድረስ ከሰው ልጆች ጋር ብዙ ውሎችን፣የተለያዩ ዘመናትን ገብቷል፤ የገባቸውን ውሎችንም ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው፥ እርሱ ታማኝ አምላክ ስለሆነ። አብዛኛው ውሎቹ(ዘመናት) ግን በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እግዚአብሔር "እናንተ፡ እንዲህ ብታደርጉ እና እንዲያ ባታደርጉ "
፥ እኔ ደግሞ "እንዲህና እንዲያ አደርግላችኋለሁ" በማለት ውል ሲገባ ነበር። ሰውም የተገባውን ውል ሲያፈርስና በውሉም መሠረት እግዚአብሔር ሲፈረድባቸው፤ ከእንደገና ሌላ ውል ሲያደርግ እንመለከታለን።

✍️ # #የዘመን #መጨረሻ እና #የአለም #መጨረሻ #የተለያዩ #መሆናቸውን #መረዳት #አለብን:: ከዚህ በፊት 5 የተለያዩ ዘመናት አልፈዋል አሁን የምንገኝው 6ኛው ዘመን ላይ ነው የፀጋ ዘመን ይባላል ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ 7ኛው
ዘመን የሺው አመት መንግስት ይቀጥላል።

🤔🤔 ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ (ገላ 4:4) #የዘመኑ #ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ ይላል።
(ሮሜ10:4) የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ #ክርስቶስ #የሕግ #ፍጻሜ #ነው።
በማለት የሕግ ዘመን ፍጻሜ እንዳገኝ እና የሚያምኑ ሁሉ የሚጸድቁበት የጸጋ ዘመን አንደጀመረ ያበስራል።
በኤፌሶን መልዕክት ደግሞ ኤፌሶን 1 (Ephesians)
9፤ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
10፤ #በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። በማለት ከጸጋ ዘመን በኃላ ስላለው የሺው ዓመት ዘመን ያወራል።

❤❤❤ NB) ግን በዚህ ሁሉ ውል ውስጥ በሰው ብቃትና ችሎታ፤ የሰው እጅ ሳይገባበት የተመሰረተ አንድ ውል አለ እርሱም መግቦት ነው።
_
✍️ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያደረጋቸው ዘመነ መግቦቶች ምን ምን ናቸው በሚቀጥለው አንድ በአንድንድ አብረን እናጥና።

ሮሜ 11 (Romans)
33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።

ይቀጥላል......

✍️2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth Church Jimma

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alazar Behayilu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Alazar Behayilu:

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed government service?

Share