Gurage Zone Revenue Department

Call Directions

Gurage Zone Revenue Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gurage Zone Revenue Department, Government Organization, Welkite, Welk'it'e.

ዛሬ ቅዳሜ በዞኑ ለሚገኙ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሁሉም የገቢ መዋቅሮች የሙሉ ቀን አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። ስለሆነም የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች እስካሁን የሚጠበቅባችሁን የግብር ...
07/11/2026

ዛሬ ቅዳሜ በዞኑ ለሚገኙ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሁሉም የገቢ መዋቅሮች የሙሉ ቀን አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

ስለሆነም የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች እስካሁን የሚጠበቅባችሁን የግብር ግዴታ በወቅቱ ያልተወጣችሁ ግብር ከፋዮች ግዴታቹን እንድትወጡ እናሳስባለን።

ጥቅምት 30/2019 የደረጃ "ሀ"ግብር መክፈያ ወቅት ይጠናቀቃል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ!!

📢 ​ለጉራጌ ዞን የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉ​ግብራችሁን በወቅቱ መክፈል እንድትችሉ በዞናችን በሁሉም የታችኛው መዋቅር መሥሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን ክፍት ሆኖ አገልግሎት እ...
06/11/2026

📢 ​ለጉራጌ ዞን የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉ

​ግብራችሁን በወቅቱ መክፈል እንድትችሉ በዞናችን በሁሉም የታችኛው መዋቅር መሥሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን ክፍት ሆኖ አገልግሎት እንደምንሰጥ ስንገልጽ በደስታ ነው።
"ግብሮን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ኃላፊነትዎን ይወጡ!"
የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ

ነገ ቅዳሜና እሁድ በክልሉ ለሚገኙ ለደረጃ'ሀ'ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ በሁሉም የታችኛው መዋቅር የሙሉ ቀን አገልግሎት እንደሚሰጥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አ...
06/11/2026

ነገ ቅዳሜና እሁድ በክልሉ ለሚገኙ ለደረጃ'ሀ'ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ በሁሉም የታችኛው መዋቅር የሙሉ ቀን አገልግሎት እንደሚሰጥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አሳሰበ

(ጥቅምት 27/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸምን ሙሉ በሙሉ ለማሳካትና የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ለማስቻል በቅዳሜና እሁድ በሁሉም የገቢ መዋቅሮች የሙሉ ቀን አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ቀመሪያ ረሻድ ይህን ያስታወቁት በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የገቢ አመራር አካላት ጋር በበይነ መረብ በተካሄደው ሳምንታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ነው።

ወይዘሮ ቀመሪያ የ100 ቀናት የገቢ ዕቅድን ግብ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ተግባራት ሳይንጠባጠቡ በዕለት ተዕለት ክትትልና ቁጥጥር መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የገቢ አመራርና ባለሙያዎችም የግብር ከፋዮችን ግዴታ በወቅቱ እንዲወጡ ለማስቻል የተመቻቸውን የአገልግሎት ዕድል በተሟላ ቁርጠኝነት በመጠቀም ሙሉ ጊዜያቸውን ለሥራ እንዲያውሉ ጥሪ ቀርቧል።

በተለይም እስካሁን ግብራቸውን ያልከፈሉ የክልሉ ደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች የተመቻቸውን የአገልግሎት ዕድል በመጠቀም ግብራቸውን ከቅጣትና ከተጨማሪ የወለድ ቅጣት ከመዳረጋቸው አስቀድመው በወቅቱ የሚጠጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

በግምገማው መድረክ የገቢ ዕቅዱን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሚያስችሉ ቁልፍ የትኩረት ነጥቦች እና የቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረ ሲሆን፣ ቀጣይ ሥራዎችን በቅንጅት፣ በተከታታይ ክትትልና በተጠያቂነት ለመፈጸም የጋራ ውሳኔ መደረሱም ተገልጿል።

06/11/2026

📢 ​ለጉራጌ ዞን የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉ

​ግብራችሁን በወቅቱ መክፈል እንድትችሉ በዞናችን በሁሉም የታችኛው መዋቅር መሥሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል።

​የአገልግሎት ቀናት፦

​🗓️ ቅዳሜ፦ 28/02/2009 ዓ.ም

​🗓️ እሁድ፦ 29/02/2009 ዓ.ም

​የአገልግሎት ሰዓት፦ ሙሉ ቀን

​ቦታ፦ በሁሉም የታችኛው መዋቅር መሥሪያ ቤቶች

​💡 ማሳሰቢያ፦ ግብሮን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ኃላፊነትዎን ይወጡ!

​🏢 የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ

06/11/2026

የ2018 የግብር ዘመን አመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር አሳዉቆ መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዉታል።

እርስዎስ ከፍለዋል?

ያልተከፋፈለ ትርፍ“ያልተከፋፈለ ትርፍ” ማለት የኩባንያው የሒሳብ ዓመት ካለቀ በኋላ ባሉት አስራ ሁለት (12) ወራት ውስጥ ለባለአክሲዮኖች ያልተከፋፈለ ወይም የኩባንያውን ካፒታል ለመጨመር ያ...
05/11/2026

ያልተከፋፈለ ትርፍ

“ያልተከፋፈለ ትርፍ” ማለት የኩባንያው የሒሳብ ዓመት ካለቀ በኋላ ባሉት አስራ ሁለት (12) ወራት ውስጥ ለባለአክሲዮኖች ያልተከፋፈለ ወይም የኩባንያውን ካፒታል ለመጨመር ያልዋለ ወይም የኩባንያውን አክሲዮን ለመግዛት ያመለከቱ ባለአክሲዮኖችን የአክሲዮን ዋጋ ለመክፈል ያልዋለ የተጣራ ትርፍ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የንግድ ሥራ ለሚያካሂድ የውጭ አገር ኩባንያ ያልተላከ ትርፍን ያካትታል።

ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፋፈለ እና መልሶ ኢንቨስት ያልተደረገ የተጣራ የድርጅቱ ትርፍ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር ይከፈልበታል።
ምንጭ ገቢዎች ሚኒስተር

05/11/2026

የ2018 የግብር ዘመን አመታዊ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር አሳዉቆ መክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዉታል።

እርስዎስ ከፍለዋል?

ቀን 25/02/2019 ዓ.ምወልቂጤ የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በጉመር ወረዳና በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የክህሎት ስልጠና ተሰጠ።ስልጠናው የተሰጠው በፌደ...
04/11/2026

ቀን 25/02/2019 ዓ.ም
ወልቂጤ
የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በጉመር ወረዳና በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው የተሰጠው በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ሲሆን በስልጠና በጉመር ወረዳና በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ ግብር ከፋዮች በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ፣ ስለሚጠበቅባቸው መብትና ግዴታዎች እንዲረዱ እንዲሁም የግብር አከፋፈልና አስተዳደር ሥርዓትን በተሻለ ሁኔታ እንዲተገብሩ ለማስቻል ነው።

በስልጠናው ላይ የአዋጁ ማሻሻያዎች፣የግብር ከፋዮች ሕጋዊ ግዴታዎች፣ የታክስ አስተዳደር አሠራሮችና ከአዋጁ ጋር ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ተሰጥቷል።

በስልጠናውም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ም/ኃላፊ እና የታክስ ትምህርትና ስልጠና ቅሬታ አጣሪ እና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አሰፋ እና የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚነወር ሀያቱ የተገኙ ሲሆኑ ከግብር ከፋዮች የተነሱ ጥያቄዎች ተቀብለው ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ስልጠናው ግብር ከፋዮች የግብር ሕጎችን በተገቢው መንገድ እንዲረዱና እንዲያከብሩ፣ የታክስ አስተዳደርን ውጤታማ ከማድረግ ባሻገር የመንግሥትን ገቢ ለማሳደግ የሚኖራቸውን ሚና እንዲወጡ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

04/11/2026
 #የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 105 ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት- ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ:- -...
03/11/2026

#የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 105 ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

- ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ:-

- ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ) እና
- ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ) ቅጣት ይከፍላል፡፡
- በዚህ አንቅጽ መሰረት የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ እዳ መብለጥ የለበትም፡፡
-መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 50(4) (በታክስ ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ የቅሬታ ማስታወቂያ) መሰረት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
ይህ አንቀጽ የዚህ አዋጅ አንቀፅ 106 (ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ) በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

Address

Welkite
Welk'it'e

Telephone

+251113302254

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Nearby government services


Other Government Organizations in Welk'it'e

Show All