Gazo Woreda Government Communication Office

Call Directions Website Contact the organization

Gazo Woreda Government Communication Office ጋዞ ወረዳ በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው።

08/10/2026
ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ1.  አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2.  ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦  የውጭ...
08/10/2026

ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ

1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

3. አቶ አዲሱ አረጋ፦ የግብርና ሚኒስትር

4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፦ የገንዘብ ሚኒስትር

5. መሐመድ እድሪስ ፦ የመከላከያ ሚኒስትር

6. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፦ የትምህርት ሚኒስትር

7. ሀና አርያስላሴ ፦ የፍትህ ሚኒስትር

8. ያስሚን ወሃብረቢ፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፦ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር

10. ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፦ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር

11. ዶክተር መቅደስ ዳባ፦ የጤና ሚኒስትር

12. አቶ አወሉ አብዲ፦ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር

13. ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ፦ የገቢዎች ሚኒስትር

14. አቶ በረከት ፍሰሃጽዮን፦ የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር

15. ሰላማዊት ካሳ፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

16. ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፦ የማዕድን ሚኒስትር

17. አቶ ሳዳት ነሻ፦ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር

18. ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ፦ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

19. አቶ ሙሳ አደም፦ የሰላም ሚኒስትር

20. ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

21. ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን፦ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር

22. ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር)፦ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር

23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር)፦ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን የግብ ተኮር ተግባራት ማሳለጫ አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ተገለፀ።ወልድያ:- መስከረም 27/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪ...
07/10/2026

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን የግብ ተኮር ተግባራት ማሳለጫ አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ተገለፀ።

ወልድያ:- መስከረም 27/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የሪፎርም አፈፃፀም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከዞን መምሪያ ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የሰሜን ወሎ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድምነው ወዳጅ እንደገለጹት፣ የሪፎርም ስራዎችን በተግባር በመተርጎም ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቅንነት የተሞላበት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ሙሉ አድሴ በበኩላቸው፣ የሪፎርም መሳሪያዎች መደበኛ ተግባራትን ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ጠቁመው፤ "አብዛኞቹ መምሪያዎች የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገቡ ቢሆንም፣ ወጣ ገባ የሚሉ መምሪያዎች ደግሞ አሰራራቸውን በማስተካከልና ክፍተቶቻቸውን በመሙላት መስራት አለባቸው" ሲሉ ተናግረዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለ ባዬ መድረኩን በበላይነት በመሩበት ወቅት የሪፎርሞች መተግበር የግብ ተኮር ስራዎቻችነን የምናሳከበት ነው።

የሪፎርም ስራዎች በዞኑ በሁሉም መስኮች ውጤት እንዲያመጡ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል

ከይስሙላ በዘለለ በእምነት ይዞ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን መተግበር ከቻልን የፓርቲን፣ የመንግስትን እና የህዝብን ፍላጎት ማሳካት እንችላለን ያሉት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ይልማ ናቸው።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት በሪፎርም ትግበራና በአበይት ተግባራት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መምሪያዎች የእውቅና ስነ-ስርዓት ተፈጽሟል።

ምክር ቤቱ የተከበሩ አቶ ታምራት ደምሴን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል።የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም 41ኛ ዙር 14ኛ ዓመት 4...
07/10/2026

ምክር ቤቱ የተከበሩ አቶ ታምራት ደምሴን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም 41ኛ ዙር 14ኛ ዓመት 42ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሔድ ጀምሯል።

የተከበሩ አቶ ታምራት ደምሴ የእውቀትና የምርምር ሰው፤ በበርካታ መንግሥታዊና መንግሥትዊ ባልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት የካበተ ልምድ ያላቸው፣ እውቀትን ከሥነ-ምግባር አቀናጅተው የያዙ፤ እስከ ዛሬዋ ዕለትም የአብክመ ማዕድን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሁነዉ ሕዝብና መንግሥትን በማገልገል ላይ የነበሩ ስለመሆናቸው ተገልጿል።

ምክር ቤቱም የተከበሩ አቶ ታምራት ደምሴ አወቀን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም

"የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባቸውን አካሂደዋል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥ...
06/10/2026

"የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባቸውን አካሂደዋል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ በማይናወጥ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንድትጸና፣ ዜጎቿም ለሀገር ብልጽግና ያላቸው ርዕይ፣ የጋለ መሻት እና የነገውን ትውልድ ባሰበ የአገልጋይነት መንፈስ የሚተጉ እንዲኾኑ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

የሀሳብ ጥልቀት፣ የዕውቀት ደርዝ፣ የሥነ ምግባር ከፍታ፣ የእሳቤ ባለቤት እና የመከወን ተነሳሽነት አንጡራ ሃብቶቻችን የኃይል ምንጮቻችን ይኾናሉ ብለዋል።

የሀገራችንን የተለምዶ የፖለቲካ ማጠንጠኛ ውርስ ከኾነው ከአምባጓሮ አመጽ እና የግጭት ጎዳና መላቀቅ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። "የጠመንጃ ባሕልን እና የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት ማስቀረት ይገባል" ብለዋል።

የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላም፣ በንግግር፣ በዕውቀት እና በመደማመጥ ላይ እንዲመሠረት መንግሥት ከፍ ያለ ትኩረት ይሰጣል ነው ያሉት። ለዚህም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በውይይት የዳበሩ ሀገራዊ ሀሳቦች ወደ መሬት እንዲወርዱ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ሙስናን እና ሌብነትን አምርሮ የሚታገል ማኅበረሰብ ለመፍጠር መንግሥት የጀመራቸው እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

ለኢትዮጵያን የሚመጥናት ሰላም፣ እድገት፣ ብልጽግና እና አንድነት በመኾኑ ሴራን እና ግጭትን የሚጠነስሱ የአዕምሮ እና የሀሳብ ውቅሮችን መንግሥት አምርሮ ይታገላል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያዊነት እሳቤ በእያንዳንዱ ጋሬጣ የሚደናቀፍ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንጊዜም ከእውነት እና ከታሪክ ጋር የሚሰለፍ አስተዋይ ሕዝብ ነው ብለዋል። መንግሥትም ይህንን ዕሴት አክብሮ እንደሚያስከብር አረጋግጠዋል።

!

!

#ኢትዮጵያ🇪🇹

የጋዞ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት የ2019በጀት አመት የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ የ1ኛ ሩብ አመት የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ!እስታይሽ ፦መስ...
06/10/2026

የጋዞ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት የ2019በጀት አመት የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ የ1ኛ ሩብ አመት የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ!

እስታይሽ ፦መስከረም 26/2019 ዓ.ም(ጋዞ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

በሰሜን ወሎ ዞን የጋዞ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት የወረዳው ጠቅላላ አመራር እና ሚኒ ካቢኒ በተገኙበት በ2019 በጀት አመት በአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ መሰረት በማድረግ በሁሉም ክላስተሮች በ1ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈፃፀም በወረዳው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መብት አለሙ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ጥንካሬና ድክመቶችን በመለየት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይም በትኩረት ተይዘው የሚከናወኑ ዋና ዋና የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በዝርዝር ተለይተው ቀርበው አቅጣጫ ተቀምጧል ።

የውይይት መድረኩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃብቴ ካሳው እና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ /ጽ/ቤት አቶ ዝናቡ ገረመው በጋራ መርተውታል።

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ***************የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አ...
06/10/2026

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
***************

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡ እና ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያራምዱ ሕጎችን እንዲያወጡ አሳሰቡ።

ፕሬዚዳንቱ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴረሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ይህ ታላቅ ምክር ቤት ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ ብቻ የሚገኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ አባላቱ ይህንን ተገንዝበው የተጣለባቸውን አደራ በታማኝነት ሊፈጽሙ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ላይ ሊሆን እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ በተለይም ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን መግታት የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ የላቀ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የጤና እና የትምህርት ዘርፎችን ከፍ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ከፍታ የሚያሸጋግሩ ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጂ እና በመሳሰሉት መስኮች የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ላቀ ውጤታማነት ማደግ እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በመልዕክታቸው አስምረውበታል።

! ! !

"የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን መሆን ስለማይችል በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
05/10/2026

"የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን መሆን ስለማይችል በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazo Woreda Government Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gazo Woreda Government Communication Office:

Shortcuts

Share