North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/

Call Directions

North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/ Prosperity party is ruling party committed to realize Ethiopia's PROSPERITY.

የሰሜን ወሎ ዞን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ተገመገመ።ወልድያ:- መስከረም 26/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን የ2019 በጀት...
06/10/2026

የሰሜን ወሎ ዞን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ተገመገመ።

ወልድያ:- መስከረም 26/2019 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ ከዞን መምሪያ ኃላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተካሄደ።

በግምገማ መድረኩ ላይ ዞኑን በቅርበት የሚደግፉ የክልል ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የሩብ ዓመቱ የእቅድ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችና አለአሰራ ያሉ ሁኔታዎች በዝርዝር ተገምግመዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለ ባዬ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በሩብ ዓመቱ በተከናወኑ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት የተመዘገቡ አዎንታዊ ውጤቶችን እንደ መልካም መነሻ በመጠቀም በዞኑ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በተገኙ ውጤቶች ላይ በመመስረት በየዘርፉ የተመዘገቡ አፈጻጸሞችንና ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ለቀጣይ ስራዎች መሰረት እንደሚሆኑም ጠቁመዋል።

በዞኑ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ የሁሉም ስራዎች ማዕከል መሆኑን በመጠቆም የህዝቡን ደህንነትና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የተጀመሩ የሰላም ግንባታ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

አቶ ደሳለ አክለውም የተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ የዞንና የወረዳ አመራሮች የመንግሥት ሰራተኞች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች በቅንጅትና በባለቤትነት ስሜት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሚሺነር ደጀኔ ልመንህ በበኩላቸው በዞኑ የተጀመሩ የልማትና የሰላም ስራዎችን ዳር ለማድረስ አመራሩ ተግባራትን በየጊዜው እየገመገመ መምራት አለበት የክልሉ መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ሐራ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ መክሮአል።‎‎በሐራ ከተማ አስተዳደር የብልጽ...
06/10/2026

በሰሜን ወሎ ዞን ሐራ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ መክሮአል።
‎
‎በሐራ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ "ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ቃል የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ አካሄደ።
‎
‎ በኮንፈረንሱ ላይ የፓርቲው አባላት፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የቀበሌ የህብረት አባላት በጋራ የተገኙ ሲሆን፤ የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማም የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀሞችን ለመገምገም እና በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎችን የተጠናከሩ እንድሆኑ ማድረግ ነው ተብሏል።
‎
‎በወቅቱ የተገኙት የሐራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታው በለጠ፤ ይህ ኮንፈረንስ የብልጽግና ፓርቲ የምስረታ በዓልን ካካሄደበት ማግስት መከናወኑ በአይነቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
‎
‎ ኃላፊው አክለውም የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዳዎች ተባብረው ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ባሴሩበት ወቅት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመተው ወደለመዱት ጉድጓድ እንዲገቡ የተደረገበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በ2019 የበለጠ ለማስቀጠል እና ተጠናክሮ ለመቀጠል ይህ ኮንፈረንስ አይነተኛ ሚና እንዳለው ጠቃሚ ውይይቶች መደረግ እንዳባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
‎
‎የሐራ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ጀሚላ ፋሪስ በበኩላቸው፤ የሐራ ከተማ በብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ትግበራዎችን በመፈጸም የፓርቲውን ደረጃ ማስጠበቅ መቻሉን ገልጸዋል።
‎
‎ ይሁን እንጂ በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት የሚደረጉባቸው በርካታ ተግባራት እንዳሉ በመገንዘብ፤ በከተማችን የአባል ምዝገባ ሥራን ማጠናከር፣ ጠንካራ መዋቅር መፍጠር፣ እንዲሁም በአደረጃጀቶች አፈጻጸም ጥራት ያለው የፖለቲካና የሥልጠና ሥራዎች ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።
‎
‎በተጨማሪም ሁሉም ተግባራት በአደረጃጀቶች አሠራር መሠረት እንዲከናወኑና በወቅቱ እንዲጠናቀቁ የክትትል ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
‎
‎ በዘርፉ የሚከናወኑ ሥራዎች የፓርቲውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከላይ እስከ ታች ያለው የዘርፍ አመራርና አባል እንዲሁም የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚመጥንና ከወትሮ በተለየ አሠራር አቅምን ማሳደግ እንዳለበት፣ እንዲሁም የፓርቲውን አደረጃጀት ማሻሻል የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እየተነደፉና በተግባር እየተንቀሰቀሰ ያለ መሆኑን ኃላፊዋ አብራርተዋል።
‎
‎ባለፉት 3 ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ተጨማሪ አቅም በማድረግ፣ አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ በማጎልበት በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችን አቅም ማጠናከር፣ እንዲሁም በየደረጃው ያለ የፓርቲ መዋቅር ኃላፊነቱን መወጣት የሚችልበትን ተልዕኮ በመሰጠት የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል።

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ***************የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አ...
06/10/2026

"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
***************

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡ እና ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያራምዱ ሕጎችን እንዲያወጡ አሳሰቡ።

ፕሬዚዳንቱ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ይህ ታላቅ ምክር ቤት ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ ብቻ የሚገኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ አባላቱ ይህንን ተገንዝበው የተጣለባቸውን አደራ በታማኝነት ሊፈጽሙ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ላይ ሊሆን እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ በተለይም ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን መግታት የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ የላቀ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የጤና እና የትምህርት ዘርፎችን ከፍ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ከፍታ የሚያሸጋግሩ ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጂ እና በመሳሰሉት መስኮች የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ላቀ ውጤታማነት ማደግ እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በመልዕክታቸው አስምረውበታል።

! ! !

በለሚ ታደሰ

06/10/2026
06/10/2026
"የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን መሆን ስለማይችል በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
06/10/2026

"የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን መሆን ስለማይችል በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

05/10/2026
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት*************የመደመር ዕሳቤን በማፍለቅ፣ ሀገር ወዳድነትን በራዕይ በማጣመር እና ፈጠራን ከትጋት ጋር በማዋሐድ ለውጦችን የመሩት ጠ...
05/10/2026

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
*************

የመደመር ዕሳቤን በማፍለቅ፣ ሀገር ወዳድነትን በራዕይ በማጣመር እና ፈጠራን ከትጋት ጋር በማዋሐድ ለውጦችን የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት።

የመደመር መንግሥት ምሥረታ አዲስ የሥልጣን ጅማሮ ብቻ አይደለም፤ ከሕዝብ የተሰጠ አደራ እንደገና የተረከበበት ኃላፊነት ነው። በቀጣይም የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል፣ ያሉ ችግሮችን ማረም፣ የሰላምን መሠረት ማጽናት፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማፋጠን እና ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ የሀገር መሠረት መጣል ዋና ዋና ተልዕኮዎቹ ይሆናሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ሀገራችንን በቅንነት፣ በጥበብ እና በጥልቅ የዓላማ ስሜት እንደሚያገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ። በአገልግሎት ዘመንዎ የላቀ ስኬት እንዲኖርዎት እመኛለሁ።

05/10/2026
"ቁጭት መነሻ እንጂ መድረሻም ማዳረሻም አይሆንም"ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
05/10/2026

"ቁጭት መነሻ እንጂ መድረሻም ማዳረሻም አይሆንም"

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Woldia

Telephone

+251967237301

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share