Gurage Zone Abeshige Woreda Communication affairs office

Call Directions

Gurage Zone Abeshige Woreda Communication affairs office Abeshige woreda government communication affairs dep't!

የጉራጌ ዞን አስተዳደር በዛሬው ዕለት በተጓደሉ ቦታዎችና በማሸጋሸግ የተለያዩ የአመራር ሹመቶችን ሰጠበዚህም መሰረት፦1) ወይዘሮ አርሽያ አህመድ፦ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ2)...
21/10/2026

የጉራጌ ዞን አስተዳደር በዛሬው ዕለት በተጓደሉ ቦታዎችና በማሸጋሸግ የተለያዩ የአመራር ሹመቶችን ሰጠ

በዚህም መሰረት፦

1) ወይዘሮ አርሽያ አህመድ፦ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ

2) አቶ በህሩ ኸይረዲን፦የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ

3) አቶ መብራቱ ተክሌ፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ

4) አቶ ዘውዱ ዱላ፦የደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ

5) አቶ ብስራት ገብሩ፦የፕላን ልማት መምሪያ ኃላፊ

6) አቶ እንዳለ ስጦታው፦የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ

7) አቶ ከበደ ሀይሌ፦የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ

8) አቶ አብድላዚዝ ከማል፦የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ

9) አቶ ሸምሱ ሸሀቡዲን፦ስራና ክህሎት መምሪያ ምከትል ኃላፊና የከተማ ስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሀላፊ

10) ወይዘሮ ጠጄ ደነቀ፦ስራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የገጠር ስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሀላፊ

11) አቶ ሙራድ ያሲን፦ት/መንገድ ልማት መምረያ ምክትል ኃላፊና ሁ/አቀፍ የቀ/ገጠር ተደራሽ መ/ል/ዘ/ኃላፊ

12) አቶ ሰፊ ቅባቱ፦ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊና ወጣት ዘርፍ ኃላፊ

13) አቶ ሰሙ ዳዊት፦የከ/ል/ኮንስትራክሽን መምረያ ምክትል ኃላፊና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ

ሆነው ተሹመዋል።

መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለን።

በአበሽጌ ወረዳ አዳዲስ የበቆሎ ምርጥ ዘር ዝርያዎች ላይ ያተኮረ የሙከራና ሰርቶ ማሳያ የአርሶአደር በዓል ተካሄደ፤ወልቂጤ ፣ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ፣በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ቱባ ተሊሎ ...
21/10/2026

በአበሽጌ ወረዳ አዳዲስ የበቆሎ ምርጥ ዘር ዝርያዎች ላይ ያተኮረ የሙከራና ሰርቶ ማሳያ የአርሶአደር በዓል ተካሄደ፤

ወልቂጤ ፣ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ፣በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ቱባ ተሊሎ ቀበሌ ከ«ሲድ ኮ» (Seed Co) የበቆሎ ምርጥ ዘር አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር SC 719፣ SC 627 እና SC 657 የበቆሎ ዝርያዎች የሙከራና ሰርቶ ማሳያ የአርሶአደር በዓል በቱባ ተሊሎ ቀበሌ ተካሄደ።

በዕለቱ የዝርያዎቹ አፈፃፀም፣ ምርታማነት እና የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ጠቃሚ ውይይቶች ተካሂደዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት፣ በዓመታት ውስጥ በአንድና ሁለት ዓይነት የበቆሎ ዝርያዎች ብቻ ተወስኖ ሲቸገር ለነበረው የወረዳው አርሶአደር አዳዲስ ዝርያዎች ማግኘት ትልቅ አማራጭና እፎይታ ነው።

መሬት በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ዝርያ ሲዘራ እንደሚያረጅ ሁሉ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ምርጥ ዘሮችን መጠቀም መሬቱን አዲስ እንዲሆን እና እንዲያክር ከማድረግ ባሻገር ትርፋማ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

ወረዳው በ2018 የምርጥ ዘር ፍላጎትን ለማሟላት ከፍተኛ መስዋዕትነት መከፈሉን ጠቁመው፣ ነባሮቹ የፓይነር እና ሌሎች ዝርያዎች የሚተኩበት አማራጭ መገኘቱ ለአርሶአደሩ መልካም አጋጣሚ መሆኑን አንስተዋል።

በወረዳው ከ37 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ወቅቱ በቆሎውን በማንሳት ሽንብራ የሚዘራበትና ሁሉንም የውሃ አማራጮች በመጠቀም መስኖ የሚለማበት ጊዜ ነው ብለዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልከሪም ናሲር በበኩላቸው፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት ለአርሶአደሩ ምርታማነት ማነቆ እንዳይሆን በየምርት ዘመኑ በርካታ ጥረቶች በማድረግ የአርሶአደሩን ፍላጎት መሸፈን ተችሏል።

ችግሩ ለመቅረፍ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ አርሶአደሩ ከተለመዱት ዝርያዎች ወጥቶ ለሰነ-ምህዳሩ ተስማሚና ምርታማነታቸው የተረጋገጡ አዳዲስ ዝርያዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በድርጅቱ አማካኝነት በቱባ ተሊሎ እና በቁሊት ሁለት ቀበሌ የሙከራ ስራዎች መስራቱን ገልፀው የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመረው የሙከራ ትግበራ በቀጣይም በጥራትና በስፋት ለማድረግ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የሲድ ኮ (Seed Co) ካምፓኒ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮነን ገላው በበኩላቸው፣ ካምፓኒው በበቆሎ ምርምር ዕድሜ ጠገብ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት በወረዳው በሙከራ ላይ ያሉት SC 657፣ SC 719 እና SC 627 ዝርያዎች እጅግ ምርታማ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት እነዚህ ዝርያዎች በተለይም SC 657 እና SC 719 በአርሶአደር ማሳ ላይ በአማካይ በሄክታር 126 ኩንታል እና በላይ ምርት መስጠት የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ዝርያዎቹ በንፋስ የመውደቅ አደጋን የመቋቋም አቅም እንዳላቸው ገልጸው፣ ድርጅቱ በስንዴ እና በሽንብራ ሰብሎች ላይም በሰፊው እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ለአርሶአደሩ በሚመች መልኩ አቅርቦቱን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።

በጉብኝቱ የነበሩ አርሶአደሮች እና የግብርና ባለሙያዎች በበኩላቸው ምርጥ ዘሩ በ2018 የነበረው የአየር ፀባይ ተቋቁሞ ለዚህ መብቃቱን አድንቀው ዘሩ በወቅቱ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።

በፕሮግራሙ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ተወካዮች ፣የሲድ ኮ የበቆሎ ምርጥ ዘር ድርጅት አቅራቢ ተወካዮች ፣የግብርና ጣቢያ ባለሙያዎችና ሞዴል አርሶአደሮች ተሳትፈዋል።

ፔጃችን ስለምትከታተሉ እያመሰገንን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጫን የተቋማችን የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡-
‎‎👉://www.facebook.com/profile.php?id=100070918473865&mibextid=kFxxJD
‎
‎👉http://tiktok.com/
‎
‎👉 ቴሌግራም፦ https://t.me/awc567
‎
‎👉 ዩቲዩብ:- https://youtube.com/?si=8HvFtXplAUMiEnmx
‎
‎👉 instagram :-
‎https://www.instagram.com/abeshigeworeda?igsh=MjQyMXN5bnhkb2d2
‎
‎👉X
‎https://x.com/AWoreda5717?t=x9hbuUQi9Esw9XahIjQkWQ&s=09

በጉራጌ ዞን የመንግሥትና የፓርቲ የመጀመሪያ ዙር  የ100 ቀናት የንቅናቄ ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።ጥቅምት 11/2019(ወልቂጤ)በጉራጌ ዞን የመንግሥትና የፓርቲ የመጀመሪያ ...
21/10/2026

በጉራጌ ዞን የመንግሥትና የፓርቲ የመጀመሪያ ዙር የ100 ቀናት የንቅናቄ ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጥቅምት 11/2019(ወልቂጤ)በጉራጌ ዞን የመንግሥትና የፓርቲ የመጀመሪያ ዙር የ100 ቀናት የንቅናቄ ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት ወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የመደመር መንግሥት ያስቀመጣቸውን ግቦች በማሳካት የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የሕዝብ ተሳትፎንና የአመራሩን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።

በእቅዱ የሰላምና ደህንነት ስራዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተመላክቷል።

በመቶ ቀናት ውስጥ የፓርቲና የመንግሥት ተቋማት የሥራ ቅንጅትን በማሳደግ፣ የአመራሩን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማጠናከር፣ የሕዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ማስቀጠልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተግባር መፍታት እንደሚያስፈልግ ትኩረት ተሰጥቷል።

በተለይም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግሩን ለማፋጠን፣ የልማት ውጤቶችን ለሕዝቡ በተጨባጭ ለማድረስና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ዕቅዶች በተቀናጀና በውጤት ተኮር አኳኋን መፈጸም እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የልማት እንቅስቃሴዎችን በማስፋፋትና የሕዝብን የአገልግሎት ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ የሚጠበቀውን ለውጥ ለማምጣት የ100 ቀናት የንቅናቄ ዕቅዱ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የሚሰሩ የሌማት ትሩፋትና የሰንበት ገበያ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም፣የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣የዞኑ አስተባባሪ አካላት፣የመምሪያ ኃላፊዎችና የወረዳ እና የከተማ አስተዳር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

መረጃው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው

የግሉ ሴክተር ተሳትፎ በማጠናከር ዞኑ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጉራጌ ዞን  ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ።ጥቅምት 10/20...
20/10/2026

የግሉ ሴክተር ተሳትፎ በማጠናከር ዞኑ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

ጥቅምት 10/2019 (ወልቂጤ)

መምሪያው የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አመተሩፍ ሁሴን እንደገለፁት የግሉ ሴክተር ተሳትፎን በማሳደግ ዞኑ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ፀጋዎችን የመለየት፣ መረጃዎችን የመሰብሰብና የማስተዋወቅ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

ባለፉት ሶስት ወራት በዞኑ በግብርና በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ ለሚሰማሩ 11 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ገልፀዋል።

እነዚህ ፈቃድ የወሰዱ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለ2 ሺህ 299 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

እንደ ኃላፉዋ ገለፃ ባለፉት ሶስት ወራት ከፈቃድ ኪራይ ሥራዎች 76 ሺህ 500 ብር በመሰብሰብ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል ብለዋል።

በተለያዩ የዞኑ መዋቅሮች ለልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚውል 250 ሄክታር መሬት የተዘጋጀ ሲሆን በዘርፉ ውጤታማ የሆኑና የመንግስትን ፖሊሲ ተከትለው ለሚሰሩ ባለሀብቶች እንደሚተላለፍ አስረድተዋል።

በከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች በተለያዩ የሥራ መስክ ለተሰማሩ ለ68 የግል ድርጅቶች ክትትልና ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ባለሀብቶቹ ለማበረታታትና ከዘርፉ የሚጠበቀው ውጤት ለማስገኘት መንግስት እየሰራ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ተደርጓል።

በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት ባሻገር በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ተሳትፏቸው ለማጠናከር እየሰሩ መሆናቸውን ኃላፉዋ ጠቁመው በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት በምርጥ ዘር፣ ቡና፣ አትክልትና የግብርና መሣሪያዎች አቅርቦት ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ወይዘሮ አመተረኡፍ አስረድተዋል።

በዞኑ 11 አምራቾች 3.75 ሚሊዮን ዶላር የገቢ ምርት እንዲተኩ ታቅዶ፣ ለ10 ፋብሪካዎች በተደረገ ድጋፍ 3.25 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻላቸውን አውስተዋል።

ኢንዱስትሪዎቹ በሙሉ አቅም ማምረት እንዲችሉ በየመዋቅረየ የሚስተዋለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ አስረድተዋል።

የኢንቨሰትመንት መስፋፋት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሲሆን የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች ግብር፣ ከትትፍ ግብርና ከመሬት ኪራይ ከፍተኛ ገቢ እያስገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሩብ አመቱ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ሲሆኑ ዞኑ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ማጠናጀር ይገባል ብለዋል።

የመደመር መንግስት አመራር ውሃ እና ቴክኖሎጂ ተኮር ግብርናን በማሳካት የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ ማተኮር ይኖርበታል:- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ጥቅምት 10/2019(ወልቂ...
20/10/2026

የመደመር መንግስት አመራር ውሃ እና ቴክኖሎጂ ተኮር ግብርናን በማሳካት የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ ማተኮር ይኖርበታል:- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

ጥቅምት 10/2019(ወልቂጤ) "የተቀናጀ ግብርና ትጋት ለተመጣጠነ ምርታማነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) እንደገለጹት መላው አመራር ውሃ እና ቴክኖሎጂ ተኮር ግብርናን በማሳካት የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ ማተኮር ይኖርበታል።

ኢትዮጵያ በስፋት እና በአይነት የምታመርት፣ የምግብ ሉአላዊነቷ የተረጋገጠ፣ በዓለም አደባባይ ተደማጭ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ የተከበረች ታላቅ እንድትሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።

የመደመር መንግስት በግብርና ልማቱ መስክ ጸጋዎችን ለይቶ በማልማት ልዩ ልዩ አቅሞችን አሰባስቦ ደምሮ እና አቀናጅቶ ለአዳዲስ ውጤቶች ማሳለጫ አድርጎ ለመጠቀም የፈጠራ እና የፍጥነት ቅኝት እየተከተለ ይገኛል ሲሉም ጠቅሰዋል።

የተቀናጀ ግብርና ልማት የምግብ ሉአላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ የግብርና ሽግግርን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ዛሬ የምንጀምረው የበጋ ወቅት የግብርና ንቅናቄ መደበኛ የእርሻ ስራ ሳይሆን፤ የልማት፣ በምግብ ራስን የመቻል፣ በምግብ ሉአላዊነትን በማረጋገጥ የኢኮኖሚ ጥንካሬያችን ማረጋገጫ ታላቅ ክልላዊ ንቅናቄ መሆኑን ጠቅሰዋል።

​የበጋ ወቅት የግብርና ስራዎች የተፈጥሮ ዝናብን ብቻ ጠብቆ ከማልማት ወጥተን፣ ያለንን የውሃና የመሬት ሀብት በአግባቡ በመጠቀም በዓመት ከሶስት እስከ አምስት ጊዜ የማረት አቅማችንን የምናሳድግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ባለፉት ዓመታት በበጋ ስንዴ እና በመስኖ ልማት ያመጣናቸው ስኬቶች እንደሚያሳዩት፣ የላቀ ጥረት ካደረግንና የተፈጥሮ ጸጋዎቻችንን ከተጠቀምን የራሳችንን ፍላጎት ማሟላት ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ማቅረብ እንደምንችል አረጋግጠናል።

ይህንን የእንችላለን መንፈስ ተላብሰን ለአዳዲስ ውጤቶች በፈጠራ እና በፍጥነት ቅኝት መትጋት ይኖርብናል ሲሉም አብራርተዋል።

የመደመር መንግስት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚሰራ፣ የመደመር አመራርም ለዚሁ ተልዕኮ የተሰለፈ ኃይል መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አስጠብቀን፣ ሁለንተናዊ ሉአላዊነታችንን አረጋግጠን፣ በስፋት አምርተን፣ የመደመር ስልጣኔን የምንገነባበት ሀገራዊ ስትራቴጂ እውን ለማድረግ በላቀ ቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማ ሱሩር በበኩላቸው ከመደመር መንግስት ምስረታ ማግስት ጠንካራ መንግስት በመገንባት በክልሉ ለግብርና ሽግግር ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ብለዋል።

የንቅናቄ መድረኩ ግብናን ለማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምግብ ሉአላዊነታችንን በቤተሰብ እና በሀገር ደረጃ ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ ስለመሆኑ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ግብርና የሀገራችን ኢኮኖሚ መሰረት ነው ያሉት አቶ ኡስማን የምግብ ሉአላዊነት እና ብልጽግና ማረጋገጫ እንዲሁም የሀገራዊ ማንሰራራት ዋነኛ ምሶሶ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያካሄድናቸው ተሳትፏዊ እና አካታች ንቅናቄዎች የክልሉን ጸጋዎች ለመለየት፣ለማልማት እና ወደ ሀብት ለመቀየር ብሎም የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው አቶ ኡስማን አስታውሰዋል።

ያለፉት ዓመታት ንቅናቄዎች ዓላማ ሀገራዊ እና ክልላዊ አቅጣጫዎቻችን የጋራ መግባባት በመፍጠር እቅዶችን በማስፈጸሚያ ስልቶች ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሮ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለውጤታማነቱ የተቀናጀ፣የተናበበ ስልት በመቀየስ የህዝብ ተጠቀቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ምንጭ፣ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምና የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።ጥቅምት 10/2...
20/10/2026

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምና የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2019 በጀት አመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምና የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኩሪያ ተመስገን እንዳሉት በበጀት አመቱ ጥራት ያለው እቅድ በማቀድ ወደ ተግባር መገባቱ አመላክተው የ100 ቀናት እቅድ በተገቢው በመተግበር በዘርፉ የተያዙ ግቦች ማሳካት እንደሚገባ አመላክተዋል።

መምሪያው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት አቶ መኩሪያ የሰንበት ገበያን በማጠናከርና ለማህበረሰቡ የፍጆታ እቃዎች በስፋት ማቅረብ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ጥራት ያላቸው ምርቶች በተገቢው ማቅረብ ይገባል ያሉት ኃላፊው አምራቹ በቀጥታ ከሸማቹ ጋር የማገናኘቱ ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የተለያዩ ምርቶች በሰንበት ገበያ በስፋት በማቅረብ
ረገድና ህገ ወጥናትን በመከላከል ረገድ በሩብ አመቱ የተሻለ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት ነጋዴዎች ፈቃዳቸውን እንዲያድሱና የቀለጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ በተሰሩ የዲጂታል ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ አስረድተዋል።

በውይይት መድረኩ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መኩሪያ ተመስገን ፣የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሄሪያ ወርቁ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊዎችና ባለሙያተኞች ፣ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ፣ የነጋዴ ሴቶች ማህበር ፣የህዝብ ክንፍና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን

የጉራጌ ዞን መስተዳድር ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም እየተገመገመ ይገኛል።ጥቅምት 9/2019(ወልቂጤ)፦የጉራጌ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት የ2019 በ...
19/10/2026

የጉራጌ ዞን መስተዳድር ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም እየተገመገመ ይገኛል።

ጥቅምት 9/2019(ወልቂጤ)፦የጉራጌ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት የ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ነው።

በሩብ ዓመቱ ህዝቡን የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማቀድና በመለየት ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል።

በተቋማት ከፈፃሚ ዝግጅት ጀምሮ ለአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ተደራሽነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ መቆየቱ ተመላክቷል።

በግብርና፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በትምህርት፣ በትራንስፖርትና መንገድ ፣በጤና ፣በስራ እድል ፈጠራ፣በሰላምና ጸጥታ፣ በፋይናንስና በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር ተመላክቷል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በማዘመን ማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ መሰራቱ ተመላክቷል።

የመንግስት ፣የበጎ አድራጊ ድርጅቶች፣የባለሀብቱና የማህበረሰቡ አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንዲመለሱ አስችሏል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም፣የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ጨምሮ የመስተዳድር ምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የወልቂጤ ጠቅላላ ሆስፒታልና የመሰረተ ልማት ክላስተር ቢሮዎች ግንባታን ጎበኙ።ጥቅምት 08/2019(ወል...
18/10/2026

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የወልቂጤ ጠቅላላ ሆስፒታልና የመሰረተ ልማት ክላስተር ቢሮዎች ግንባታን ጎበኙ።

ጥቅምት 08/2019(ወልቂጤ)

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየተካሄዱ የሚገኙትን የወልቂጤ ጠቅላላ ሆስፒታል ግንባታ እና የመሰረተ ልማት ክላስተር ቢሮዎች ግንባታ ሂደትን ጎበኙ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው ወቅት የፕሮጀክቶቹን አጠቃላይ የእድገት ደረጃና የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን፥ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳና ጥራት ተጠናቀቀው ለህብረተሰቡ ፈጣንና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በተለይም የወልቂጤ ጠቅላላ ሆስፒታል ግንባታ መጠናቀቅ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የሚታየውን የመልካም አስተዳደርና የጤና አገልግሎት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገገፁ ሲሆን፥ የመሰረተ ልማት ክላስተር ቢሮ ግንባታም የአካባቢውን የተቀናጀ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በመስክ ምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፣የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና እየተሳተፉ ይገኛል።

የጉራጌ ህዝብ በራስ አገዝ  አካባቢውን በማልማት እና በጠንካራ የማህበራዊ ትብብር እሴቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በአርአያነቱ የሚጠቀስ ታላቅ ህዝብ ነው !!
18/10/2026

የጉራጌ ህዝብ በራስ አገዝ አካባቢውን በማልማት እና በጠንካራ የማህበራዊ ትብብር እሴቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በአርአያነቱ የሚጠቀስ ታላቅ ህዝብ ነው !!

የመደመር መንግስት ታላቁ ስትራቴጂያዊ ግብ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የኢትዮጵያን ስልጣኔን እውን ማድረግ ነው፦ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)ጥቅምት 8/2019(ወል...
18/10/2026

የመደመር መንግስት ታላቁ ስትራቴጂያዊ ግብ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የኢትዮጵያን ስልጣኔን እውን ማድረግ ነው፦ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)

ጥቅምት 8/2019(ወልቂጤ)"በመደመር መንግስት የህዝብ ድምጽ የጋራ ተሳትፎ የጋራ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር የትምጌታ አስራት እንዳሉት የጉራጌ ህዝብ ራስ አገዝ ድርጅት በማቋቋም አካባቢውን በማልማትና በጠንካራ ማህበራዊ እሴቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ አርአያ የሆነና ለብዙዎች በምሳሌነት የሚጠቀስ ህዝብ ነው።

በዚህም መንገድ በመስራት፣ ትምህርት ቤት በመገንባትና መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ረገድ የሚታወቅ ህዝብ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ለክልሉና ለሀገር ተሞክሮ የሚሆን እንደሆነ ገልጸዋል።

የጉራጌ ባህላዊ የሰፈራና የመንገድ አሰራር ጥበብ የሆነው ጀፎረና የክትፎ አዘገጃጀትን በዩኔስኮ አለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ሰፊ የጥናትና የዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ በመሆኑ የክልሉ መንግስትም ይህ እውን እንዲሆን እንደሚሰራም አመላክተዋል።

የመደመር መንግስት ታላቁ ስትራቴጂ ግብ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የኢትዮጵያን ስልጣኔ መገንባት ስለመሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ የመደመር ስልጣኔ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የመደመር ስልጣኔ ምሶሶ፣ወጋግራና ማገር የመደመር ፍልስፍና ነው ያሉት ዶ/ር የትምጌታ የመደመር ፍልስፍና መለያየትን ሳይሆን አንድነትን፣ መከፋፈልን ሳይሆን መሰብሰብንና ተነሳሽነትን ወስዶ ለጋራ ግብ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ይበልጥ ለማስቀጠል በስሜት ሳይሆን በማስተዋል፣ በመለያየት ሳይሆን በአንድነት በሀሜት ሳይሆን ተግቶ በመስራት ዞኑ፣ ክልሉና የሀገሪቷን ብልጽግና በጋራ ለማልማት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም እንዳሉት የመደመር መንግስት አንድነትና ትብብር ፣ የተለያዩ ማንነቶችና ሀሳቦችን ማክበር፣ የዜጎች ተሳትፎ ማበረታታትና ከግል ጥቅም ይልቅ የጋራ ጥቅም ማስቀደምና የሀገር ሀብትና አቅም አሰባስቦ ለልማት ማዋል መሰረታዊ እሴቶቹ ናቸው።

ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ዘላቂ ኢኮኖሚ መገንባት፣ የዜጎች ተሳትፎን ማሳደግ፣ ድህነት መቀነስና የተቋማት አቅም መገንባትና የሀገር ብልጽግና ማረጋገጥ አላማ አድርጎ የሚሰራ መንግስት ነው።

የጉራጌ ህዝብ የመደመር መንግስት መርሆችና አላማዎች ቀድሞ የተረዳ፣ በተግባር የኖረና እየኖረው ያለ በየትኛውም ቦታ ልዩነቶችን አክብሮና ተቻችሎ የሚኖር ፣በአንድነትና በትብብር የሚያምንና ከግል ጥቅም ይልቅ በጋራ መልማትና መበልጸግ የሚያስቀድም ነው።

ጉራጌ ጉልበቱ እውቀቱና ገንዘቡን ደምሮ የመንግስት ጉድለት እየሞላ ኢትዮጵያን የሚያለማ፣እንደዚሁም ድህነትን ለማሸነፍና ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ ታታሪና ስራ ወዳድ ህዝብ ነው።

በባለፉት አመታት ለለውጡ መወለድና መጽናት ሚናው ከፍተኛ እንደነበር አንስተው፣ ከለውጡ ትሩፋቶችም መጠቀም የጀመረ ህዝብ ነው ብለዋል።

የጉራጌ ህዝብ የፓርቲው እሳቤዎችና ፕሮግራሞችን ተረድቶ፣ ተገንዝቦና ተቀብሎ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በዞኑ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ታአማኒነት ያለውና በፓሪቲው አብላጫ ድምጽ አሸናፊነት እንዲጠናቀቀ ሚናውን ተወጥቷል ብለዋል።

Address

Wolkite
94

Telephone

0113301423

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Abeshige Woreda Communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share