31/12/2023
የአበርገሌ ወረዳ የስራ እና ስልጠና ጽ/ቤት Aberglie Woreda Labor and Training Office
ስለ አበርገሌ ወረዳ ስራ እና ስልጠና ጽ/ቤት ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ክዋኔዎች መረጃ ያገኙበታል። ይወዳጁን!
31/12/2023
19/12/2023
ማስታወቂያ
ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ!
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ከሃገር ውስጥ እና በሃገር ውጪ ያሉ የስራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ባለው የሪፎርም ስራና በተዘረጋው ቴክኖሎጂ በአምስት ወራት(ወ.ሴ) ከ146,291 በላይ ዜጎች በውጭ ሃገር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል።
ሚንስቴር መስሪያቤቱ በውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት የዜጎቻችን ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሁም ብልሹ አሰራርን የሚከላከል ቴክኖሎጂ በውስጥ አቅም አልምቶ እጅግ ፈጣን የሆነ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በመሆኑም ሚንስቴር መስሪያቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በሚያከናውናቸው የሪፎርም ተግባራት እና በዘርፉ በሚሰጠው ፈጣን አገልግሎት እንዲሁም የስምሪት መደረሻዎችን ለማስፋት ከተለያዩ ሃገራት ጋር እየገባናቸው ያሉ አዳዲስ ስምምነቶች የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ በተዘረዘረው የሞያ መስክ ተመዝግበው ስልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆናቹ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት https://www.lmis.gov.et ድህረ-ገጽ ላይ ገብታቹ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
1. Driver - ሹፌር
2. Cleaner - የጽዳት ባለሞያ
3. Chef - በሼፍ
4. Laborer - በጉልበት ሰራተኝነት
5. Security Guard/ Security Officer - የጥበቃ ባለሞያ
6. Technician - ቴክኒሺያን
7. Carpenter - የእንጨት ባለሞያ
8. Store Keeper - የሱቅ ጠባቂ
ተመዝጋቢዎች ድህረ-ገጹ ላይ በሚደረገው ምዝገባ መረጃዎቻችሁን በትክክል የማስገባት ሃላፊነት ያለባችሁ ሲሆን መረጃዎቻችሁን አስገብታችሁ ስትጨርሱ ሲስተሙ በሚሰጠው የባዮሜትሪክስ ቁጥር አቅራቢያችሁ በሚገኙ አንድ ማዕከላት በመሄድ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በማደረግ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናስታውቃለን።
ማሳሰቢያ:
ለመመዝገብ የፓስፖርት ባለቤት መሆን የማያስፈልግ ሲሆን ፤ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ የሚያከናውኑ አንድ ማዕከላትን ዝርዝር https://lmis.gov.et/ossc-lists ከዚህ ላይ ማግኘት ይቻላል።
የሥራዎ ባለቤት እርስዎ ኖዎት !
07/10/2023
በUNDP በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የመስሪያና መሸጫ ማእከላት የግንባታና ጥገና ተጠናቆ ለምርቃት በቁ!
°°°
የአበርገሌ ወረዳ በባለፉት አመታት ተከፈተው የነበረው ጦርነት የሰው ህይወትን ያሳጣና የንብረት ውድመት እንዲሁም ህዝብ እንዲፈናቀል ምክንያት ሁኖ ቆይቷል ሁኖም አሁን የተገኘውን ሰላም በመጠቀም የተጎዳውን መሰረተ ልማት መልሶ ለማቋቋም መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም እየሰራ መሆኑን የአበርገሌ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የስራና ስልጠና ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ መኳንንቴ በግንባታው ምረቃ ስነ ስርኣት ላይ በመገኘት በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል።
የመስሪያና የመሸጫ ማእከላት ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ ምርቃቱ ላይ የዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስተዳደር ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ታደሰ ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የወረዳ ሴክተር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የከተማው የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እና የ01 ቀበሌ ማዋቅር ተገኝቷል።
ፕሮጀክቱ የመስሪያና የመሸጫ ማእክላት ጥገናው የበርና መስኮት እንዲሁም ጣሪያ እድሳትን በማካተት 2.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ሁኖ በአጠቃላይ 19 ኮንቲነሮች መጠገኑን የወረዳው ም/አስተዳደሪ እና የስራና ስልጠና ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ መኳንንቴ ገልፀዋል።
የወረዳው ም/አስተዳዳሪ በንግግራቸው አክለውም የወረዳው ስራ ፈላጊ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት የመስሪያና የመሸጫ ማእከላትን ለመገንባት ውለታ የወሰዱ በግንባታ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከታቀደለት ጊዜና በጥራት ገንብቶ በማስረከባቸው አመስግኗል።
አያይዞም የወረዳውን መሰረተ ልማት ወደ ነበረበት ለመመለስ ለሚደረገው ተግባር UNDP እያደረገ ላለው የገንዘብ ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም የወረዳውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በመቀረፅ የሚሰሩ ስራዎችን እንደሚደግፍ ቃል መግባቱን ጋር ተያይዞ አመስግነዋል።
የዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስተዳደር ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ተወካይ ኃላፊ የሆኑት አቶ አቶ ንጉሱ ታደሰ እነዚህ የመስሪያና የመሸጫ ማእክላት ላይ የወረዳው ስራ ፈላጊ ወጣቶች በመልመያ መስፈርቱ መስረት በመመልመል ወደ ስራ እንዲገቡና ራሳቸውን ችሎ ለማህበረሰባቸው አገልግሎት ለመስጠት እንዲጀምሩ መሰራት እንደሚገባ ገልፆ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ግንባታውን በአጭር ጊዜና በጥራት በመስራት ማስረከባቸውን ተከትሎ ኢንተርፕራይዞች መስራት እንደሚችሉ በተግባር ያስመሰከሩ መሆናቸውን በመክፈቻ ፕሮግራሙ ተገኝቶ ገልፀዋል።
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
°°°
Twitter;https://twitter.com/AbergelleW_PP
Telegram;https://t.me/AWPP_DSM
Youtube;https://www.youtube.com/
Facebook;https://www.facebook.com/AbergelleWoredaProsperityPartyOffice
27/06/2023
11/03/2023
በትብብርና ስልጠና አተገባበር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ክልል አቀፍ የምክክርና ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
የመንግስትና እና የግሉ ዘርፍ ትብብርና ቅንጅት ለክህሎት ልማትና ዘላቂ የስራ ዕድል ፈጠራ በሚል መሪ ቃል በትብብርና ስልጠና አተገባበር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ክልል አቀፍ የምክክርና ንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር እየተካሄደ ይገኛል።
በንቅናቄ መድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲስፋፉ ክልሉ በርካታ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ዕውቀት ፣ክህሎትና የተማረ የሰው ሃይል እንዲፈጠር ትኩረት ተሰጦት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሰልጥኖ የወጣ ሃይል የተሟላ ዕውቀት ኖሮት ስራን የሚጠብቅ ሳይሆን በራሱ ተንቀሳቅሶ ለውጥ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት ብለዋል።
ዶ/ር ጌታቸው አያይዘውም በሌላው አለም ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሰልጥነው የሚወጡ ወጣቶች በቀጥታ ወደ ኢንዲስትሪዎች የሚገቡ መሆኑን ጠቅሰው ይህ አይነቱ ሽግግር ለኛ አገር ፈተና መሆኑን ተናግረዋል።
ወጣቶች ክህሎትና ዕውቀትታቸውን ለስራ በማዋል ለክልሉም ሆነ ለአገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይጠበቃል ያሉት ክቡር ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ከውይይት መድረኩ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት መፍትሔዎችን ለይቶ ያስቀምጣል የሚል እምነት አለኝም ብለዋል።
የአብክመ የስራና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ አቶ አረጋ ከበደ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ከሌሎች በቀለም የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማት የሚለየው የስልጠና ፍላጎቱ ወቅታዊና ተጨባጭ የስራ ገበያው ከሚፈልገው የዕውቀትና የክህሎት ፍላጎት የሚነሳ በመሆኑ ነው ብለዋል ።
ቢሮ ሃላፊው በንግግራቸው በክልሉ በተለይም በከተሞች የስራ አጥነት ምጣኔው ወደ 19.7 በመቶ መድረሱን ገልጸው የሴቶች የስራ አጥነት ምጣኔ ከ28 በመቶ በላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የስራ ዕድል በመፍጠር ወጣቱ የኢኮኖሚ ልማቱ ዋነኛ ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆን ክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ምክር ቤትን በህግ መቋቋሙንም ተናግረዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ፣ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፣ ዶ/ር ጋሻው አወቀ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ፣የቢሮ ሃላፊዎች፣የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ አመራሮች እና ከንቲባች ተገኝተዋል።
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
08/03/2023
የአበ/ወ/ስራና ስልጠና ጽ/ቤት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ምዝገባ በጥራትና በፍጥነት እንዲሰራ ሰራተኞችን የስራ ስምሪት ሰጠ፤
በወረዳው በከተማ እና በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ለሚገኙ የኢፌድሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቅርቡ ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ ፈላጊ ዜጎችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ሀገር ለስራ ለመላክ መስማማቱ ይታወቃል።
እንደ ወረዳ 400 ኮታ የተሰጠን ሲሆን የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና እና ፈቃደኛ የወረዳችን ስራ ፈላጊ ዜጎችን መልምለን በማሰልጠን ለመላክ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ለሚቆይ ምዝገባ ስራውን በጥራትና በፍጥነት እንዲመዘግቡ ስምሪት ሰጥቷል።
የአበ/ወ/ስራና ስልጠና ጽ/ቤት
የካቲት 29/2015 ዓ.ም
ሰቆጣ
08/03/2023
ለበለጠ መረጃ ዞን አስተዳደር ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 እየመጡ መረጃ ያግኙ!
08/03/2023
በአበርገሌ ወረዳ በንየረ-አቑ ከተማ እና በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ለምትገኙ ስራ ፈላጊዎች በሙሉ፡-
የኢፌድሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቅርቡ ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ ፈላጊ ዜጎችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ሀገር ለስራ ለመላክ ተስማምተዋል።
ስለሆነም የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ እና ፈቃደኛ የሆናችሁትን የወረዳችን ስራ ፈላጊ ዜጎችን መልምለን በማሰልጠን መላክ እንዳለብን ከክልል ስራና ስልጠና ቢሮ እና ከዋግ ኽምራ ብሔ/አስ/ር ስራና ስልጠና መምሪያ ተገልፆልናል፡፡ እናም በየደረጃው ያሉት ተቋማቶች ባሳወቁን የመመልመያ መስፈርት መሠረት ማለትም፡-
1, በሰቆጣ ከተማ በራሳቸው ወጭ ለ1 ወር በማስልጠኛ ማዕከላት ስልጠና መውሰድ የሚችሉ
2, ከስልጠና ቡኋላ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተፈትነው ማለፍ የሚችሉ
3, እድሜያቸው ከ18-40
4, የት/ት ደረጃ በማንኛውም የት/ት ደረጃ ላይ የሚገኙ
5, ፆታ ሴት ብቻ
6, ጠቅላላ የጤና ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነችና የአካል ጉዳት የሌለባቸው
7, መልካም ስነ-ምግባር ያላቸውና ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች ከፖሊስ ወይም ቀበሌ አስተዳደር ስለ መልካም ስነምግባራቸው ማፃፍ የሚችሉ
8, የጉዞ ወጭ በአስሪዎች የሚሸፈን ይሆናል።
9, ለወረዳው የተሰጠ ኮታ 400 ሴቶች ናቸው።
10, የመመዝገቢያ ጊዜ 29/06/2015 እስከ 02/07/2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት የአበርገሌ ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ጊዜያዊ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ 1 ቁጥር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአበርገሌ ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት
የካቲት 29/2015 ዓ.ም
ሰቆጣ
06/03/2023
አስቸኳይ ለአበርገሌ ወረዳ ነባር ኢንተርፕራይዞች!
በተለያዪ ጊዜያት በወረዳችን በሁሉም ቀበሌዎች በተለያዪ የስራ ዘርፎች/መስኮች በግልም ይሁን በማህበር ተሰማርታችሁ ስትሰሩ የነበራችሁ እና በጦርነቱ ምክንያት በመፈናቀል ሰቆጣ የምትገኙ ነባር ኢንተርፕራይዞቻችን ያላችሁበትን ተጨባጭ ሁኔታን ለማወቅና በቀጣይ ከኢንተርፕራይዞቻችን ጋር ለምናከናውናቸው ተቋማዊ ተግባራት መረጃችሁ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ከዛሬ 27/06/2015 -01/07/2015 ዓ.ም በጊዜያዊ ቢሮችን ዞን አስ/ር ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቀጥር 1 እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪ እያቀረብን ለመመዝገብ ስትመጡ
1. የታደሰ የበሌ መታወቂያ (ኮፒ)
2. የኢ/ዝ መመስረቻ ጽሁፍ (በእጃችሁ ካለ)
3. የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች በእጃችሁ ያሉ አስፈላጊ ናቸው የምትሏቸው መረጃዎችን (በኮፒ)
ይዛችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እዚሁ ሰቆጣ ተቀምጠው ሪፖርት በማያደርጉ ኢንተርፕራይዞች ተቋሙ እውቅና የማይሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
የአበርገሌ ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት
የካቲት 27/2015
03/03/2023
13/12/2022
#የቀጠለ....
ስልጠና ቤተሰቦች
10) “ቋሚ የሥራ ዕድል” ማለት የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ ፈጥረው የሚሰሩ ወይም በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በቋሚነት ተቀጥረው በፔይሮል ክፍያ በማግኘት የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ማለት ነው::
11) “ጊዜያዊ የሥራ ዕድል” ማለት በጥሪት ማፍሪያ ፕሮጀክቶች የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊነት በማቋቋም ወይም በፔይሮል ክፍያ በማግኘት ከአንድ ዓመት ላነሰ ጊዜ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ማለት ነው::
12) "የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት" ማለት የኢንተርፕራይዞቹን ችግር የለየና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የተሟላ መረጃ ማደራጀትና የመስጠት፣ ሥልጠና ድጋፍ፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ግብይት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡
13) "የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና" ማለት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፎች ለተሠማሩና ለሚሠማሩ የኀብረተሰብ ክፍሎች፣ ባለሙያዎች አንድን ምርት ወይም አገልግሎት በብቃት ለማቅረብ፣ ጥራትና ምርታማነትን በቀጣይነት ለማሻሻል፣ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት አመለካከት፣ ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ በተሰማሩበት ወይም በሚሰማሩበት መስክ ላይ ዕሴትን በመጨመር ልማትን ለማፋጠን እንዲያስችል የሚሰጥ ሙያዊ ሥልጠና ነው፣
14) "የንግድ ሥራ አመራር ሥልጠና" ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አዋጪ የንግድ መስክን በመምረጥ፣ በማቋቋምና በመምራት ሂደት ውስጥ በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራት፣ በማስተባበርና በመቆጣጠር ውጤታማ እንዲሆኑ የሚሰጥ ሥልጠና ነው፣
15) “የገበያ ትስስር” ማለት ለአንድ ኢንተርፕራይዝ የገበያ ዕድል ለመፍጠር ከመንግስት ተቋማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በአገር ውስጥ ከሚገኙ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በግብዓት፣ በምርትና አገልግሎት አቅርቦት በጎንዮሽና በተዋረድ ግንኙነት የሚፈጠር የግብይት ወይም የሥራ ትስስር ነው::
16) “ጠቅላላ ሃብት” ማለት የአንድ ኢንተርፕራይዝ የተከፈለ እና በብድር የተገኘ ሀብት ነው::
17) ”ጠቅላላ ካፒታል” ማለት ህንፃን ሳይጨምር ከኢንተርፕራይዙ ጠቅላላ የቢዝነሱ ሀብት ላይ ዕዳው ተቀንሶ የሚገኝው ካፒታል ማለት ነው፡፡
18) “የምርት ወይም የአገልግሎት ማስተዋወቂያ ዘዴዎች” ማለት ምርትን ወይም አገልግሎትን ለማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙሃን፣ ንግድ ትርዒትና ባዛር፣ ድረ-ገፅ፣ በራሪ ወረቀት፣ ቢዝነስ ካርድ፣ ቋሚ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ ማሸጊያ እና የመሳሰሉትን ያካትታል::
19) "የሙያ ብቃት ምዘና" ማለት አንድ ባለሙያ በተዘጋጀው የሙያ ደረጃ መስፈርት መሰረት የሚጠበቅበትን ብቃት መያዙ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ነው።
20) "ቴክኖሎጂ” ማለት ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ መሣሪያዎችን እና እነዚህኑ ለመጠቀም የሚያስችሉ ማኑዋሎችን፣ የአሰራር መመሪያዎችና አደረጃጀትን ያጠቃልላል፡፡
21. “ገበያ” ማለት በአካባቢ፣ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኝና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎት በተወዳዳሪ ዋጋ የሚቀርብበት ነው፡፡
22. “የገበያ ትስስር” ማለት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ እድል ለመፍጠር ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የአነስተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በግብዓት፣ በምርትና አገልግሎት አቅርቦት (በግዢና ሽያጭ) በጎንዮሽና በተዋረድ ግንኙነት የሚፈጠርበት የገበያና ግብይት ስርዓት ነው፡፡
23. “ሞዴል ኢንተርፕራይዝ” ማለት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮግራም ታቅፎ በራስ ጥረትና የተደረገለትን ድጋበራስ ጥረትና የተደረገለትን ድጋፍና ግብአት በመጠቀም ለላቀ ውጤት የበቁና በልማታዊ አመለካከቱ ለሌሎች መሰል ኢንተርፕራይዞች አርአያ በመሆን በማስፋፋት ስትራቴጂ ላይ ግንባር ቀደም የልማት ሀይል የሆነ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
24. “ኮንስትራክሽን ዘርፍ” ማለት በሥራ ተቋራጭነት በንዑስ ሥራ ተቋራጭነት፣ ባህላዊ የማዕድን ሥራዎች፣ የከበሩ ድንጋዮች ልማት፣ ጌጠኛ ድንጋይ (ኮብልስቶን) ሥራዎች፤ የመሠረተ ልማት ግንባታ ንዑስ ተቋራጭነት የሥራ ዘርፎች ማለት ነው::
25. “የንግድ ዘርፍ“ ማለት የሀገር ውስጥ ምርቶችን በጅምላ ሽያጭ፣ በችርቻሮ ንግድና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ላይ የሚሰራ የሥራ ዘርፍ ነው::
13/12/2022
ስልጠና ቤተሰቦች
ለዞን፣ ለወረዳ ስራና ስልጠና ፅ/ቤት፣ ለአንድ ማዕከላት ባለሙያዎች እና አመራሮች በሙሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ትርጓሜዎች በአግባቡ እንድታዉቋቸው እና ግንዛቤ እንድትይዙባቸው ለማድረግ ያህል ነው፡፡
1. ትርጓሜ
በ2010 ዓ.ም በወጣው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር አፈፃፀም እና የገበያና ግብይት ሞዴል መመሪያ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፤
1) ”ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ እስከ አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው:፡
2) ”አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,001 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በከተማ ግብርና፣ በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራና በግንባታ ዘርፍ ከብር 100,001 (አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1,500,000 (አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው::
3) “ኢንዱስትሪ ዘርፍ” ማለት ማኑፋክቸሪንግ (በጥቃቅን ብቻ)፣ ከተማ ግብርና፣ ባህላዊ ማዕድን እና ግንባታ ዘርፎችን ያካትታል፡፡
4) “አገልግሎት ዘርፍ” ማለት ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጪ ሆኖ አገልግሎት በመስጠትና በሀገር ውስጥ ምርቶች ንግድና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ላይ የሚሰራ የሥራ ዘርፍ ነው::
5) “የኢንተርፕራይዝ ደረጃ ሽግግር” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ ባለበት የዕድገት ደረጃ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ላይ በዋጋ፣ በጥራትና በአቅርቦት ተወዳዳሪ ሆኖ የቀጣይ የዕድገት ደረጃ የሽግግር መስፈርቶቹን በማሟላት መሸጋገር ሲችል ነው::
6) “የምሥረታ/ጀማሪ ደረጃ” ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመሥረት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በየደረጃው የሚጠበቅባቸውን ትምህርት በማጠናቀቅና በማህበር እና በግለሰብ በሕግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ የገቡትን የሚያካትት ነው:: የምሥረታ /ጀማሪ ደረጃ ኢንተርፕራይዝ ሕጋዊ አቋም ይዞ የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባር የሚጀምርበት ነው::
7) “የታዳጊ/መስፋፋት ደረጃ” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ላይ በዋጋ፣ በጥራትና በአቅርቦት ተወዳዳሪ ሲሆንና ትርፋማነቱ በቀጣይነት ሲረጋገጥ ነው:: በዚህ ደረጃ ያለ ኢንተርፕራይዝ በምሥረታ ደረጃ ከነበረው ቀጥሮ የሚያሠራው የሰው ኃይል ቁጥርና የጠቅላላ ሀብት መጠን ዕድገት ይኖረዋል:: በተጨማሪም ኢንተርፕራይዙ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የሚጠቀም ይሆናል::
8) “የመብቃት ደረጃ” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ የገበያ ድርሻውን ለማሳደግ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በሥራ ላይ ካዋለና ለዘርፉ የተቀመጠውን ትርጓሜ መሥፈርት በማሟላት ወደ ታዳጊ መካከለኛ ሲሸጋገር ወይንም በአለበት ደረጃ በመሆን በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን ነው::
9) “ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ” ማለት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተቀመጠውን የሰው ሃይልና ጠቅላላ ሃብት መጠን የመብቃት የዕድገት ደረጃ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Aberglie
Abergele
