26/05/2026
ለተከበራችሁ መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችና ለክልላችን ነዋሪዎች ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ይህ ታላቅ በዓል የፍቅር፣ የአንድነትና የመተሳሰብ ተምሳሌት እንደመሆኑ መጠን፤ ለእናንተና ለቤተሰባችሁ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!
ዒድ ሙባረክ!
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
23/05/2026
የሀረሪ ክልል የሸሪአ ፍርድ ቤት የኅብረተሰቡን ቅሬታዎች ለመቅረፍ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
*************
የሀረሪ ክልል የሸሪአ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ በኅብረተሰቡ ዘንድ ይነሱ የነበሩ በርካታ ቅሬታዎችንና የአሠራር ክፍተቶችን ሥር ነቀል በሆነ መልኩ ለመለወጥ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
የሀረሪ ክልል የሸሪአ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሸኽ ነስረዲን አሊ ተቋሙ የነበሩበትን የአገልግሎት ማነቆዎችና የተገልጋዮችን ቅሬታ ለመፍታት እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሸኽ ነስረዲን አሊ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኅብረተሰቡን አመኔታና ፍላጎት በአግባቡ ለመመለስ ዋነኛው መፍትሔ የሰው ኃይል ጥራትን ማስተካከል በመሆኑ፣ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በጉብኝቱም የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት የተከበሩ አቶ ሰለሀዲን ተውፊቅ ባስተላለፉት መልእክት፤ የሸሪአ ፍርድ ቤቱ የነበሩበትን የአሠራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በግልጽ አምኖ በመቀበል፣ ችግሮቹን ለመፍታትና ተቋሙን መልሶ ለማደራጀት እየተደረጉ ያሉ የሪፎርም ጥረቶች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፕሬዝደንቱ አክለውም፣ የተጀመሩት የለውጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የሕዝቡ ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ምላሽ እንዲያገኝ አስፈላጊው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደማይለይ አስገንዝበዋል።
በተመሳሳይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አሻ አሚኔ በበኩላቸው፤ የፍትህ ሥርዓቱ ዋነኛ ዓላማ የኅብረተሰቡን አመኔታ ማግኘት መሆኑን አስታውሰው፣ የሕዝቡን የቅሬታ ድምጽ በመስማት አሠራሩን ለማስተካከልና አዳዲስ ቃዲዎችን በመመደብ የተጀመረውን ይህንን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ መግፋት እንደሚገባ በንግግራቸው አሳስበዋል።
በመጨረሻም የጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩት የፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች በሸሪአ ፍርድ ቤቱ እየተገበሩ ያሉትን የአገልግሎት ማሻሻያ እርምጃዎች የተመለከቱ ሲሆን፣ ያሉትን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ተቋሙን ለኅብረተሰቡ ምቹና ታማኝ የፍትህ መድረክ ለማድረግ በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
21/05/2026
“በማንኛውም ሀገር የፍትህ ሥርዓት መሠረቱ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ፍርድ ቤት የፍትህ የመጨረሻ መቋጫ ሲሆን፣ የዚህ ተቋም የጀርባ አጥንት ደግሞ ዳኛው ነው፡፡ ዳኝነት በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚቀሰም የሕግ እውቀትና ከመሸምደድ ባለፈ፣ ጥልቅ የሆነ ስብእናንና የባህሪ ልህቀትን የሚጠይቅ ከባድ ኃላፊነት ነው::”
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እሻ አሚኔ
20/05/2026
በሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስለ ጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
****************
በሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የካንሰር በሽታን አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ፣ በተለይም ስለ ጡት ካንሰር ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ልዩ መድረክ ተካሄደ።
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አሻ አሚኔ በመድረኩ በመገኘት ለሠራተኞቹ ባስተላለፉት መልእክት፤ ሠራተኞች በሥራ ውጥረት ውስጥ ሆነውም እንኳ ለጤናቸው ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ክብርት ምክትል ፕሬዝደንቷ አክለውም፣ እንዲህ ዓይነት የጤና ግንዛቤ መድረኮች ሠራተኛው ራሱንና ቤተሰቡን ከከፋ የጤና እክል እንዲጠብቅና በሥራው ላይም ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸው፣ ፍርድ ቤቱ ለሠራተኞቹ ደህንነትና ጤና ሁልጊዜም ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ ላይ በዘርፉ የታወቁ የህክምና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን፣ ዶ/ር ሚኪያስ ሻውል እንገለፁት በሽታውን በሳይንሳዊ መንገድ እንዴት መከላከል እንደሚቻልና የጡት ካንሰር ደረጃዎችን በጥልቀት አብራርተዋል።
በሽታው በጊዜ ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ መፈወስ የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ሚኪያስ፣ ሠራተኞች በተለይም ሴቶች አዘውትረው ራሳቸውን እንዲመረምሩና የሕክምና ክትትል እንዲያደርጉ መክረዋል።
ዶ/ር ይህነው ታደለ በበኩላቸው የጡት ካንሰርን አስቀድሞ ለማወቅ የሚረዱ የመጀመሪያ ምልክቶችንና አጠቃላይ የጤና አጠባበቅ ዘይቤዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን መከተልና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በሽታውን ለመከላከል ያለውን አስተዋጽኦም አብራርተዋል።
በተጨማሪም ሲስተር አና ሳሙኤል (የጨረር ሕክምና ኦንኮሎጂ ነርስ) የጡት ካንሰር ሕመምተኞች የሚያልፉባቸውን የሕክምና ሒደቶችና በሕክምናው ወቅት የሚያስፈልጋቸውን የነርሲንግና የበጎ አድራጎት እንክብካቤዎች ያብራሩ ሲሆን፣ በጨረር ሕክምና ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችም ግንዛቤ አስጨብጠዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የ"ሙሉ ሰርቫይቫል" ተወካዮች የካንሰር በሽታን አሸንፈው የዳኑበትን የራሳቸውን የሕይወት ተሞክሮ በማካፈል፤ በሽታው ቢገኝ እንኳ ተስፋ አለመቁረጥና ሕክምናን በአግባቡ መከታተል ሕይወትን እንደሚያድን በመግለጽ ለሠራተኞቹ ትልቅ ብርታትና ተስፋ የሚሰጥ መልእክት አስተላልፈዋል።
በግነዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ስለ በሽታው የነበራቸውን የተሳሳተ አመለካከት በመቀየርና ቅድመ ምርመራ የማድረግን አስፈላጊነት በሚገባ እንዲረዱ በማድረግ ተጠናቋል።
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
19/05/2026
የዳኝነት አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ
*************************
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
በመድረኩ ላይ የሕዝብን የፍትሕ ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ሰልሀዲን ቶውፊቅ ሰፊና ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በሪፖርታቸው እንዳብራሩት፤ ባለፉት 9 ወራት ፍርድ ቤቱ የሕዝብን ቅሬታ የሚያስነሱ አሠራሮችን በመለየት በርካታ አበረታችና ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል ብለዋል።
በተለይም የዳኝነት ጥራትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን የሕዝብ ጥያቄ የሆኑ የፍርድ ቤት መዝገቦችን በፍጥነት ውሳኔ በመስጠት፣ ለዓመታት ሳይቋጩ የቆዩ የክምችት መዝገቦችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ እንዲሁም የመንግሥትን የበጀትና የሰው ኃይል ስምሪት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ በማዋል ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ፕሬዝዳንቱ በዝርዝር አስረድተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሠራሮች (Digitalization) እና የተቋማዊ አቅም ግንባታ ሥራዎች የሕብረተሰቡን የእርካታ ደረጃና በፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን አመኔታ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርትና በተመዘገቡት ጥንካሬዎች ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ባለፉት 9 ወራት የሥራ ጉዞ ውስጥ ያጋጠሙ የአፈጻጸም ክፍተቶችንና ማነቆዎችን በጥልቀት ፈትሿል።
በዚህም መሠረት በአንዳንድ ዘርፎች የሚስተዋሉ የክትትልና የቁጥጥር ጉድለቶች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየቶችና ከሕብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎች በአፋጣኝ ተለይተውና በኃላፊነት ስሜት ተገምግመው ፈጣን ምላሽ ሊያገኙ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሰልሀዲን ቶውፊቅ ከኮሚቴው አባላት ለተነሱት መሠረታዊ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፊ ሙያዊ ማብራሪያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ከተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተሰጡትን ሁሉንም ገንቢ ግብዓቶችና የክትትል አቅጣጫዎች በመውሰድ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረም ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ምክር ቤት የህግ አስተዳደርና ሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ፈሪሀ መሐመድ ባስተላለፉት መመሪያዊ መልእክት፤ የፍትሕ አካላት የተጣለባቸውን ታሪካዊና ተቋማዊ አደራ በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
15/05/2026
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
15/05/2026
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት (ECMAT) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::
************
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ የሚገኘውን የፍትሕ አገልግሎት ይበልጥ ለማዘመንና የዳኝነት አካላትን አቅም ለመገንባት የሚያስችለውን ወሳኝ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት (ECMAT) ጋር በጋራ ተፈራርሟል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሐዲን ተዉፊቅ ባስተላለፉት መልእክት፣ የካፒታል ገበያ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ ጠቁመው፣ ዘርፉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የሕግ ክርክሮችን በብቃት ለመዳኘት የዳኝነት አካላትን አቅም መገንባት አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ይህ ስምምነት ዳኞች በዘመናዊ የሕግ ማዕቀፎች ታግዘው ፍትሐዊና ፈጣን ውሳኔዎችን እንዲሰጡ ትልቅ በር የሚከፍት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ክቡር ዳኛ አብነት ዘርፉ በበኩላቸው፣ የካፒታል ገበያ ሕጎች ወጥ በሆነ መልኩ ተተርጉመው በተግባር ላይ እንዲውሉ የክልል ፍርድ ቤቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋማቸውም ለሐረሪ ክልል ዳኞችና ዓቃቤ ሕግ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ያካተቱ የሥልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀትና ብቁ አሰልጣኞችን በማቅረብ ሙያዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።
ከስምምነቱ ጎን ለጎንም ለክልሉ ዳኞችና ዓቃቤ ሕግ ስለ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ የሕግና የቁጥጥር ማዕቀፍ ግንዛቤ የሚፈጥር ሥልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናው የፍትሕ አካላቱ የካፒታል ገበያ ጉዳዮችን በብቃት እንዲከታተሉ፣ እንዲያስፈጽሙና ውሳኔ እንዲሰጡ የሚያስችል የሕግ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚቆየው ይህ የተቀናጀ ተቋማዊ ትብብር፣ ሁለቱ ወገኖች በጋራ በሚያወጡት የበጀትና የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተከታታይነት ባለው መልኩ የሚከናወን ይሆናል።
ይህ ስምምነት በሐረሪ ክልል በቴክኖሎጂ የተደገፈና ለተገልጋዩ ማኅበረሰብ ፈጣንና ጥራት ያለው ምላሽ የሚሰጥ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እየተከናወነ ያለውን ሰፊ የሪፎርም ሥራ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።
ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
11/05/2026
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/
05/05/2026
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጸሙን በመገምገም፤ ለቀጣዩ ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ
****************
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የየዳይሬክቶሬቱ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሳለጥና ተቋማዊ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ ላይ በየደረጃው የሚገኙ የዳይሬክቶሬት የሥራ ኃላፊዎች የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለይም በመዝገብ አያያዝ፣ በውሳኔ አሰጣጥ ፍጥነት እና በስራዎችን ቅልጥፍናና በጥራት ላይ የተገኙ ውጤቶችና የታዩ ክፍተቶች በግልጽ ተለይተዋል።
የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሐዲን ተውፊቅ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዳይሬክቶሬቶች የፍትሕ ሥርዓቱን ለማዘመንና የሪፎርም ሥራዎችን ለማሳካት የሚሰሩት ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን በማስፋትና የቆዩ መዝገቦችን በፍጥነት በመቋጨት የሕዝብን የፍትሕ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አሻ አሚኔ በበኩላቸው፣ በግምገማው ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የተለዩ ድክመቶች ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ታርመው ለተሻለ ውጤት መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ዳይሬክቶሬቶች ለቀጣዩ አራተኛ ሩብ ዓመት በልዩ ትኩረትና በታቀደ መልኩ እንዲዘጋጁም አሳስበዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ አመራሮቹ በቀጣይ አራተኛው ሩብ ዓመት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦችን ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሠረት የዓመታዊ ዕቅዱን አፈጻጸም መቶ በመቶ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ማሳለጥ፣ እንዲሁም የሪፎርም ሥራዎችን እስከ ታችኛው የፍትሕ እርከን ድረስ ተደራሽ ማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው ተመልክቷል።
ተሳታፊ ዳይሬክተሮችም በቀረቡት ግብረ-መልሶችና በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ ለዓመቱ ማጠቃለያ ስኬታማነት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] https://web.facebook.com/hararicourts
[Telegram] https://t.me/hararicourts
[Website] http://www.hsc.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/Hararicourts
[Instagram] https://www.instagram.com/hararicourts/