የደባርቅ ልጆች እና የሰሜን ዋልያ

የደባርቅ ልጆች እና የሰሜን ዋልያ

Share

ኑ ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንወያይ

07/04/2022
23/01/2022
18/12/2021
27/11/2021

አባቴ ዘግይቶ አይግባህ!

ኮንጎዎች ለነፃነታቸው የታገለውን ሉሙምባን ገድለው ማዕድናቸውን ከዘረፉ ቤልጂየሞች ጋር ፈንድቀዋል። ቡርኪናፋሶ ምርጥ መሪያቸውን ቶማስ ሳንካራን ገድለው ከፈረንሳዮች ጋር ውስኪ እየተራጩ ደንሰዋል። ኢራቃዊያን ነዳጃቸውን የግላቸው ያደረገውን ሳዳምን ከአሜሪካ ጋር አብረው ገለው ባደባባይ ጨፍረዋል። ሊቢያውያንም በረሀዋን ሀገር ለውጦ ዳቦ ያበላቸውን ጋዳፊ ገለው ሬሳዉ ላይ እያስካኩ ፎቶ ተነስተዋል። ዛሬ ላይ የኮንጎ ማዕድን አምራችም ነጋዴም ደላላም የምዕራብ ካምፓኒዎች ናቸው። ቡርኪናፋሶ ፈረንሳይ ካልፈቀደች ምርጫ እንኳን የማካሔድ አቅም የላትም። የሊቢያና የኢራቅ ነዳጅ ማንም እየቀዳ የሚሸጠው የመንገድ ላይ ኩሬ ሆኗል። እነዚህ ሀገራት ነጮቹ ሳይፈቅዱ የገዛ ሀብታቸውን የሚሸጡበትን ዋጋ እንኳን መተመን የማይችሉ ደካሞች ሆነዋል። ዜጎቻቸው ዛሬ የነጭ ወሬ አምነው የገደሏቸውን መሪዎቻቸውን እየናፈቁ ይኖራሉ። እናም አባቴ ሀገርህን ለመሪህ ብለህ ሳይሆን ለራስህና ለልጅ ልጅህ ስትል ጠብቅ!!

17/10/2021

ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
≈ዶ/ር ምህረት ደበበ

1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመስግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመስግን።

9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ-ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው
ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።

Fasil Yenealem🇪🇹 (@FasilYenealem) | Twitter 16/10/2021


#ልብ ያለው ዝም ብሎ አያልፍም!
የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሰረቀ። ዘበኛው ይዞት ነበርና ሊያመልጥ ሲል የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።
#ዳኛው የወንጀሉን ክስ ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!😳
"የሆነ ነገር፥ ማለትም ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"
ልጁ - እያፈረ "አዎን ሰርቀአለሁ"
ዳኛው - "ለምን?"
ልጁ - "አስፈልጎኝ"
ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"
ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም" 🙄
ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"
ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"
ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"
ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ"
ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅኽም?"
ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን
መጥፎ ውሳኔ ወሰንሁ"
ጥያቄው ሲጠናቀቅ #ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።
እንዲህም አለ
"ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ
በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን። ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር
ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ
ጀመረ።
በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ።
ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።
ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣለት ወሰነ።
የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው!
የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።
የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።
---------------------------------------
በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል?
የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው 😢
ይህ መልዕክት ልብህን ከነካ እባክህን ለአንድ ሰው ዳቦ ግዛ።
አንተ እያለ ሌላው ጾም ማደር የለበትም።
በዙሪያህ ካሉ ከብዙዎች አንድ ሰው መርጠህ አስደስተው!
!
ከብዙዎች ትሻላለህና ካለህ ጥቂት ነገር ላጡት አካፍል!
ይህንን ከባድ ጊዜ ተጋግዘን እንለፈው🙏

ይህንን በማረጋችሁ ፈጣሪስብላቹኃልና

በማድረግ ለሁሉም አድርሱ

በማድረግ አዳዲስ መረጃዎች በየቀኑ ይደርሶታል።


አስተያየታችሁ t.me/fasilyenealem 👈በዚህ ይደርሰኛል።

http://twitter.com/fasilyenealem

Fasil Yenealem🇪🇹 (@FasilYenealem) | Twitter The latest Tweets from Fasil Yenealem🇪🇹 (). ኢትዮጵያ ትቅደም

30/09/2021

እንደዚህ ብናስበውስ....

| ኤልያስ ሽታኹን

*የኖቤል ሽልማት መስራቹ አልፍሬድ ኖቤል ሞቷል ተብሎ ጋዜጣ ላይ ወጣ፡፡ ሞቷል የተባለው ኖቤል የገዛ የሞቱን ዜና በገዛ ቤቱ ቁጭ ብሎ አነበበው፡፡ የተሳሳተ ዜና ነበር፡፡ ወንድሙ ነበር የሞተው፡፡ ኖቤል ግን ጋዜጣው ላይ የወጣው ርዕሰ አንቀጽ ነበር ያስደነገጠው፡፡

"በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ብዙ ሰዎችን በአንዴ የሚፈጀ ፈጠራ በመፈልሰፍ ሀብታም ለመሆን የበቃው ዶ/ር አልፍሬድ ኖቤል በትናንትናው ዕለት አረፈ" ይላል ጋዜጣው፡፡

ኖቤል ከዚህ በኃላ እንቅልፍ አጣ፡፡ ቢሞት ኖሮ ዓለም የሚያስታውሰው በዚህ ስም ነበርና ከነበረበት ቅዠት የተሳሳተው ጋዜጣው አነቃው በዚህም ሳቢያ ዓለም በሰላም እና በደግ በደጉ እንዲያስታውሰው "ኖቤል" ሽልማትን መሰረተ፡፡ ለዓለም እና ለሰው ልጆች መልካም ያበረከቱ የሚሸለሙበት ትልቁ ሽልማት ተባለለት፡፡

እንደዚህ ብናስበውስ

የከተማው ሰዎች የሚሳለቁበት ሰው ቢፈልጉ አንድ ሞኝ አገኙ፡፡ "ከዚያ ከተራራው ካለው በረዶ በላይ ከሚቀዘቅዘው ኩሬ ለረዥም ሰዓት ከዋኘህ ገጣሚ ትሆናለህ" አሉት፡፡
እሱም ያሉት አደረገ፡፡ ገጣሚ ግን አልሆነም፡፡
ሳቁበት፡፡ ተጠቋቆሙበት፡፡ ቆይቶ ነው እያፌዙበት መሆኑንም ያወቀው፡፡ ሞኝ አይደለ፡፡

አኮረፋቸው፡፡ ተቀየማቸው፡፡ ትቷቸው ሸሸ፡፡ ውሎውን ጫካና ከሸንተረሮቹ ከተራሮቹ አደረገ፡፡ ከሰው ተሸሸገ፡፡
ሲያኮርፋቸው በብቸኝነት ሲከርም ብዙ አሰበ፡፡ አሰላሰለ፡፡

ሲመለስ ወደከተማው የሀገሩ ትልቁ ገጣሚ ሆኖ ነበር፡፡
ገባኝ ያለውን ሲናገር ሁሉ አፉን ከፍቶ ይሰማው ጀመር፡፡ የኢራኑ የግጥም አማልክት መሃል ደረሰ፡፡ ብቸኛ ሲሆን የተመኘውን ሆነ፡፡
* ታላቁ ገጣሚ ባባ ጣሂር፡፡

እንደዚህ ብናስበውስ

* ኦገስት ስትሪንበርግ የተባለው ሰውየ በክፉ ስራው ምክንያት አንድ ምርጥ ደራሲ ለዓለም አበርክቷል፡፡ ያ ክፉ ስራው ምን እንደሆነ በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለውም፡፡
ግን የኖርዌው ታላቁ ፀሐፌ ተውኔት እና መራሄ ተውኔት ትልልቅ ድርሰቱን የሚጽፈው የጠላቱን
የ'ኦገስት ስሪንበርግ' ፎቶ ፊት ለፊቱ አስቀምጦ ነበር፡፡ መነሸጫው ማሰላሰያው የዚሁ ሰው ፎቶ ነበር፡፡ የበደለውን ሰውየ እያየ ነበር ብዙ ሀሳብ የሚመጣለት፡፡ ጠላቱ ይነሽጠው ነበረ፡፡

ደራሲ ሄነሪክ ጆሀን ኢብሰን፡፡
"the father or realism" ተብላል በዘመኑ፡፡
(1828 ተወልዶ 1906 ላይ በ78 ዓመቱ አርፏል)

እንደዚህ ብናስበውስ

* በባርነት ዘመኑ ሁሉ ደግ የሚላት የጌታውን ሚስት ነው፡፡ ጌታው ቢጨክንበትም ሚስቱ ግን ታቀርበው ነበርና ፊደል ታስተምረው ነበር፡፡ ይሄንን የደረሰባት ባሏ አብዝቶ ተቆጣት፡፡ "ባሪያ ነው እኮ፡፡ አንቺ ካስተማርሽው ያውቃል፡፡ ካወቀ ይጠይቃል፡፡ ከጠየቅ ባርነቱን ይጠላል፡፡ እና እንዴት ታስተምሪዋለሽ?" ብሎ ተቆጣት፡፡ ለካ ባሪያው ፍሬድሪክ ዳግላስ ከጓዳ ሰምቶ ኖሮ ከጠላቱ ቁጣ የዘላለም ብርሃን በራለት፡፡ "ዕውቀት"

አሻፈረኝ አለ፡፡ ተማረ፡፡ አወቀ፡፡ በጥቁሮች ታሪክ ትልቁ ታጋይ ዳግላስ ተባለ፡፡
(1817-1895 በ78 ዓመቱ አርፏል)

እንደዚህ ብናስበውስ

* አደራ በል ጓደኛው ነው ለዓለም ውለታ የዋለለን፡፡ ታዋቂው ደራሲው ፍራንስ ካፍካ ብቸኝነት ነበር መለያው፡፡ ጥቂት ጓደኞች ብቻ ናቸው የነበሩት፡፡ በሳምባ ነቀርሳ ነው የሞተው፡፡ በአጫጭር እና በረጅም ልብወለዱ ታዋቂ ነው፡፡ የጻፋቸው ስራዎች ሁሉ ተሰብስብስበው እንዲቃጠሉ በኑዛዜው ላይ ተናግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን 'ማክስ ብሮድ' የተባለው ጓደኛው አደራውን በላ፡፡ ያለካፍካ ፍቃድ እንዲታተሙ አደረገ፡፡ እንዲነበቡ ዓለም እንዲገረምባቸው ሆነ፡፡ አንባብያን ሁሉ "ይሄን የመሰለ ጽሑፍ ነበር ይቃጠል ያለው" ብለው ካፍካ ላይ ተገረሙበት፡፡ ጓደኛውን በልባቸው አመሰገኑት፡፡

(1883-1924 በ40 ዓመቱ አረፏል)

እንደዚህ ብናስበውስ

* አድባረ ግጥም ጸጋዬ ገብረመድኅን የእናቱ መሬት በጉልበተኞች መሬት ተነጥቀው አጥር ፈርሶባቸው ከብቶቻቸው ይበተኑባቸው ስለነበር ነው፡፡ እንደልጅ ይነደው ነበርና ይሄን በህግ ሊያስመልስ በቺካጎ ህግ አጥንቶ መጣ፡፡

ሲመለስ የእናቱ መሬት ብቻ ሳይሆን የሀገሬው ደሀ መሬት ሁሉ በጉልበተኞች ተወርሷልና ትግሉን
ለተበደሉ ድሆች ሁሉ አደረገ፡፡

ያውም በጥበብ አደባባይ፡፡ ያውም በግጥም አደባባይ፡፡ ለእናቱ ፍትሕ የተነሳው ጸጋዬ ወኔ ለእናት ሀገሩ ዘለቀ፡፡
(1928-1998)

* * *
ዋቢ
* ግሩም የዓለማችን ምርጥ ታሪኮች
ግሩም ተበጀ
*የመንፈስ ከፍታ
በረከት በላይነህ
*ጣዝማ:- አስደናቂው የደራሲያን ሕይወት
ንጉሤ አየለ እና ደጀኔ ጥላሁን
*ሸገር ራድዮ
መቆያ
*ከሕግ ፊት እና ሌሎችም
GOETHE-INSTITUT
*ምስጥረኛው ባለቅኔ
ሚካኤል ሽፈራው

Want your business to be the top-listed Government Service in Jerusalem?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Jerusalem
972