Ethiopian Embassy in Rome

Ethiopian Embassy in Rome

Condividi

This is the official page of the Ethiopian Embassy in Rome Official page of the Ethiopian Embassy in Rome.

12/06/2026

"ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!

‎በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው።

‎በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

‎ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው።

‎የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!"
‎ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

‎ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
‎ethiocoders.et/

Photos from Ethiopian Embassy in Rome's post 12/06/2026

H.E. Ms. Demitu Hambissa Bonsa, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of Ethiopia to Italy and Permanent Representative to FAO, IFAD, and WFP, confers with IFAD President Álvaro Lario.
The high-level discussion focused on transforming rural livelihoods, scaling up climate-smart farming, and boosting investments for young agricultural innovators in Ethiopia. Both sides reiterated their commitment to turning climate challenges into sustainable economic opportunities for millions of smallholder farmers.

Photos from Ethiopian Embassy in Rome's post 10/06/2026

በጣሊያን ካሲኖ ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ከኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ
========

(ሰኔ 02/2018 ዓ.ም.) በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ከጣሊያን ካሲኖ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከርና የቀጣይ የOutreach ፕሮግራም ትግበራ መሰረት ለመጣል ያለመ የውይይት መድረክ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና አመራሮች፣ የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በታደሙበት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተካሂዷል።

በጣሊያን በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በትምህርት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ካሲኖ ዩኒቨርሲቲ 394 ተማሪዎችን በማስተናገድ ትልቁን ቁጥር ይይዛል።

በዕለቱ በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሃምቢሳ ወቅታዊ የአገራችንን ጉዳዮች በማንሳት፣ ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና ላይ የምትገኝ መሆኗን ገልጸው፣ በውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት፣ ልምድና ቴክኖሎጂ ወደ አገር ቤት በማሸጋገር ለአገር ልማትና ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የቆንስላ አገልግሎትና አሰራር እንዲሁም አገልግሎቱን በቅርበት ለተማሪዎቹ ተደራሽ የሚሆንበት ሁኔታ ለመክፈት ይህ ቀን የመጀመሪያውን ስራ የሚከናወንበት መሆኑን በመጥቀስ ኤምባሲው ለተማሪዎች የሚያስፈልገውን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አምባሳደሯ ያለቸውን ሙሉ እምነት አንስተዋል::

የካሲኖ ዩኒቨርሲቲ ሬክተር ፕሮፌሰር ማርኮ ዴል ኢዞላ (Prof. Marco Dell'Isola) በበኩላቸው፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል በማመቻቸት በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ለወደፊትም በጋራ መሥራት በሚገቡ ጉዳዮችና በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ላይ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በትምህርታቸው ጠንካራና መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው መሆናቸውን በማድነቅ፣ ይህ ዕድል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያላቸውን ተስፋ ጠቁመዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያም አገልግሎት ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቆንስላ አገልግሎት በቦታው ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

Photos from The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia's post 10/06/2026
Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 09/06/2026
Photos 06/06/2026
Photos from Office of the Prime Minister-Ethiopia's post 05/06/2026
Photos from Ethiopian Embassy in Rome's post 05/06/2026

Representing one of Africa’s largest livestock sectors, H.E Demitu Hambisa Bosa, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of Ethiopia to Italy and Permanent Representative to FAO, IFAD, and WFP, shared powerful, field-tested lessons on transitioning smallholder farmers away from antimicrobial reliance while protecting production and livelihoods.

She shared her insightful message during a crucial panel exploring "The Future of Antimicrobial Use in Livestock: The Economic Cost of Action or Inaction" hosted by the Food and Agriculture Organization (FAO) in Rome.

Vuoi che la tua azienda sia il Servizio Di Governo più quotato a Rome?

Clicca qui per richiedere la tua inserzione sponsorizzata.

Ubicazione

Indirizzo


Via Andrea Vesalio 16-18
Rome
00161

Orario di apertura

Lunedì 09:00 - 17:00
Martedì 09:00 - 17:00
Mercoledì 09:00 - 17:00
Giovedì 09:00 - 17:00
Venerdì 09:00 - 17:00