14/11/2023
ጆርዳን ወይም ዮርዳኖስ በደቡብ ምዕራብ እስያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ፣ በሌቫንት ክልል ደቡባዊ ክፍል እና በአረብ ባሕረ ገብ መሬት ሰሜናዊ ክፍል የምትገኝ አረብ ሀገር ናት። በሰሜን ከሶሪያ፣ በምዕራብ ፍልስጤም፣ በምስራቅ ከኢራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ትዋሰናለች። በዚህ ስም የተሰየመችውም የዮርዳኖስን ወንዝ መሰረት በማድረግ ነው። ከኢትዮጵያ ጋርም ከጥንት ጀምሮ ጥሩ ግንኙነት አላት።
