03/06/2026
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ (ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ከተማ የሚገኘውን የኮሎን ( KOLON) ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካምፓኒ ጎበኙ፡፡(ግንቦት 26 ቀን 2018)
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ (ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ከተማ በሚገኘው የኮሎን ( KOLON) ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካምፓኒ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ሚን-ቴ ኪም(Min-Tae Kim) እና ከሥራ ባለደረቦቻቸው ጋር ፍሪያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት የኮሎን ( KOLON) ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካምፓኒ የቢሮ ሰራተኛ የሆኑት ካንት ህቱን(Khant Htun) የካምፓኒውን ታሪካዊ አመሰራረት፣ዓላማ፣ ተልዕኮ እና ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
በመቀጠልም በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ (ዶ/ር) አገራችን በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የምትገኝ ወደ አፍሪካ መግቢያ በር የሆነች፣ ከተለያዩ ዓለማት ጋር የተሳሰረች እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የአየር መንገድ ትራንፖርት እና እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ ያላት፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብና 70% አምራች የሰው ኃይል ያላት፣ የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነች፣ ጠንካራ የመንግስት ድጋፍ ያለባት፣ የንግድ ሊበራላይዜሽን ያደረገች፣ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ምቹ የኢንቨስትመንት መልክዓ ምድር ለመፍጠር የቢዝነስ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ዘርግታ የምትገኝ አገር መሆኗን በመጥቀስ የኮሎን ( KOLON) ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካምፓኒ በአገራችን ጨርቃጨርቅና አልባሳት የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማራ ጠይቀዋል፡፡
በመጨረሻም የኮሎን ( KOLON) ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካምፓኒ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በቀጣይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች በማጥናት ውሳኔያቸውን እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል፡፡
03/06/2026
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ (ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ ሎቴ ሆቴል የኮሪያ-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳተፉ፡፡ (ግንቦት 25 ቀን 2018)
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ (ዶ/ር) በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴዑል ከተማ ከተካሄደው የ2026 የኮሪያ -አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን በደቡብ ኮሪያ ሎቴ ሆቴል ‘‘የኮሪያ-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ‘‘ በሚል ርዕሰ-ጉዳይ በደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተዘጋጀ ውይይት ላይ አገራችን በመወከል ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ ከአፍሪካ አህጉር የመጡ የተለያዩ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ተቀማጭነታቸው በደቡብ ኮሪያ የሆነ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች፣ የደቡብ ኮሪያ መልህቅ ኩባንያ ኃላፊች፣ በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ አገሮች የንግድ ምክር ቤቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተመራማሪዎችና ፕሮፌሰሮች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
‘‘Driving Synergies through Korea-Africa Economic cooperation-FromK-content to New Markets‘‘, ‘‘Korea-Africa Business Cooperation: Present and Future‘‘ እና ‘‘Critical Minerals and Energy Cooperation for Korea-Africa Co-prosperity‘‘ በሚሉ የውይይት አጀንዳዎች በፕሮፌሰሮችና በተመራማሪዎች ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
አምሳ የአፍሪካ አገራት ያፀደቁት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AFCFTA) መፈረሙ፣ ከ8,500 በላይ የሚሆኑ እቃዎችና አገልግሎቶች ሰርቲፊኬት ኦፍ ኦሪጂን የተሰራላቸው መሆኑ፣ የኢንዱስትሪ ሽርክና የእሴት ሰንሰለት የተፈጠረ መሆኑ፣ ዲጂታል ፈጠራ እና አረንጓዴ ኢንዱስትሪ እየተፋፋ በመሆኑ እና ፋይናንስና ኢንቨስትመንት የማመቻቸት ሥራ እየተሰራ ስለሚገኝ የአፍሪካ አህጉር ለደቡብ ኮሪያ ኢንቬስተሮች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለመሆን የሚያስችል አቅም ያለው ስለሆነ የኮሪያ መልህቅ ኩባንያዎች በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
እንዲሁም ከአሁን በፊት የነበሩና ወደፊትም ሊኖሩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ ተግዳሮቶችን ያካተተ ማብራሪያ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በደቡብ ኮሪያ በኩልም አሁን እየተፈጠረ ያለውን ዓለማዊ ጂኦ ፖለቲካዊ አዝማሚያ በሚገባ በመገንዘብ የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶችና የደቡብ ኮሪያ መንግስት በጋራ በአፍሪካ አህጉር የሚኖራቸውን የኢኮኖሚ የጋራ ተጠቃሚነት ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ወደ ተግባር ለመግባት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
01/06/2026
Ethiopia and its unstoppable people have once again stunned the world! In the 7th National Election, over 54 million proud Ethiopians flooded the polls, proving yet again that we are a proud mystery — impossible for outsiders to predict or control.
01/06/2026
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴኡል ከተማ በተካሄደው በ2026 የኮሪያ–አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተሳተፉ!(ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም)
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ በተካሄደው በ2026 የኮሪያ–አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተሳትፈዋል:: በስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በኮሪያ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ነጻነትና ሉአላይዊነት ለማስጠበቅ ወታደሮቸ መላካን በማስታወስ በደቡብ ኮሪያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ወዳጅነት በመስዋእትነት ላይ የተመስረተ መሆኑን ገልጸዋል።
በሰብስባው ላይ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በአፍሪካና በደቡብ ኮሪያ መካከል ሁለንተናዊ ትብብርና አጋርነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። አምባሳደር ደሴ በዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት (smart mobility)፣ በከተማ ልማት ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፎች ላይ ደቡብ ኮሪያና የአፍሪካ ህገራት በትብብር መስራትን ያለውን አስፈላጊነት አጉልተው ገልጸዋል። አምባሳደሩ አያይዘውም ደቡበ ኮሪያ በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ በከተማ ፕላን እንዲሁም በመረጃና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ያላት የዳበረ ልምድ ለአፍሪካ ማጋራት አዲስ አበባ ጨምሮ በፍጥነት እያደጉ ያሉ የአፍሪካ ከተሞች ዘላቂ እና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ማዕከላት አንዲሆኑ እንደሚያስችል አብራርተዋል።
አንዲሁም የአየር ንብረትን በመከላከል ረገድ በደቡብ ኮሪያና በአፍሪካ ህገራት መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ አንዲቀጥልም አምባሳደር ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራችን የአየር ንብረትን በመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች እየወስደች እንደምትገኝ በመግለጽ ይህንን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ አሳውቀዋል።
በተጨማሪም አምባሳደር ደሴ የኮሪያ ኩባንያዎች በአፍሪካ፣ በተለይም ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እያደረገች ባለችው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያጠኑ አበረታተዋል። በደቡብ ኮሪያ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የገበያ ተደራሽነት ለማስፋት እና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ፍይዳን ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመጨረሻም ደቡብ ኮሪያ ለአፍሪካ የልማት ጥረቶች እንደ መሠረተ ልማት፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ባሉ ዘርፎች የምታደርገውን ድጋፍ እንድታጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
31/05/2026
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴኡል ከተማ በተካሄደው በ2026 የኮሪያ–አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ “ senior officials” ስብሰባ ተሳተፉ!(ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም.)
በኮሪያ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴኡል ከተማ በተካሄደው በ2026 የኮሪያ–አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ “ senior officials” ስብሰባ ተሳትፈዋል::
31/05/2026
Happening Now | 2026 Korea–Africa Foreign Ministers’ Meeting: Senior Officials’ Meeting
27/05/2026
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ ይሁንልን።
መልካም በዓል!
26/05/2026
አምባሳደር ደሴ ዳልኬ(ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ በደቡብ ኮሪያ የካምቦዲያ አምባሳደር ኩዮን ፖን ራታናክ (Khuon Phon Ratanak) ጋር ውይይት አደረጉ፣(ግንቦት 18፣2018)
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር ደሴ ዳልኬ(ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ የካምቦዲያ አምባሳደር ከሆኑት ኩዮን ፖን ራታናክ (Khuon Phon Ratanak) ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም አምባሳደር ደሴ ዳልኬ(ዶ/ር) ለአምባሳደሩ ስለሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች በማስረዳት የሀገራችንን አቋም የማስገንዘብ ስራ ሰርተዋል፡፡ እንዲሁም አምባሳደር ደሴ በኢትዮጵያና ካምቦዲያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ወዳጅነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡
በደቡብ ኮሪያ የካምቦዲያ አምባሳደር ኩዮን ፖን ራታናክ (Khuon Phon Ratanak) በበኩላቸው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ስለቀረባቸው ማብራሪያ ምስጋና በማቅረብ ወቅታዊ ሁኔታ መረዳታቸውና ለሀገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እንደሚያስተላልፉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አምባሳደር ኩዮን ፖን ራታናክ ካምቦዲያና ኢትዮጵያ መካከል በሁለትዮሽና ባለብዙ መድረኮች የሚያደርጉት ትብብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
25/05/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) የአፍሪካ ቀንን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልእክት:-
መልካም የአፍሪካ ቀን ለመላው አፍሪካዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን!
የዛሬ 63 አመት አባቶቻችን እዚሁ አዲስ አበባ ተሰብስበው ነጻ የሆነች፣ የተባበረች አፍሪካን ለማለም ደፍረው፣ ያ ህልማቸው አሁንም ብሩህ ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ኩሩ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ከእያንዳንዱ አፍሪካዊ ሀገር ጋር በተመሳሳይ የአንድነት መንፈስ ትከሻ ለትከሻ ትቆማለች።ስራው ገና አልተጠናቀቀም። ከቃላት ወደ ተግባር፣ ከተስፋ ቃል ወደ እድገት እንሸጋገር።
የአፍሪካ ታላቅ ሃብት ምንጊዜም ህዝቦቿ ናቸው፣ እና አንድ ላይ፣ እንነሳለን!
#የአፍሪካ ቀን #አፍሪካ #ኢትዮጵያ