የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት

የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት

Share

This is an official page for በኩዌት የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ?

ይህ የኢትዮጵያዊያን ቤተሰባዊ መረዳጃ ማህበር በኩዌት የፌስቡክ ፔጅ ያቋቋምንበት ዋናው አላማ እኛ በኩዌት የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ባሉብን ችግሮች ዙሪያ የምንወያይበት እና ወደ መፍትሄ የምንመጣበት በችግሮቻችን የምንረዳዳበት የአገራችን ገጽታ የምንቀይርበት እና አገራዊና ወቅታዊ መ መረጃዎችን የምንቀያየርበት ከኛም አልፈን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ እህት ወንድሞቻችን የተለያየ ችግሮች ሲደርስባቸው በምንችለው አቅም ሆነ አሳብ የምንረዳዳበት የዋትስአፕ ግሩፕ (WhatsApp Group) ያለን ሲሆን ይህ የዋትስአፕ ግሩፕ አቅሙ ውስን በመሆኑ ይህን የፌስቡክ ፔጅ በመክፈት ማንኛውም በኩዌት ነዋሪ የሆነ ፍቃደኛ ኢትዮጵያዊ ፔጃችንን ላ

Photos from የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት's post 28/06/2016


የድረሱልኝ ጥሪ ሁለት ነብሶችን እንደማዳን ነዉ
(በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ )
ይህ የምትመለከቱት ወጣት በሊስትሮ ስራ የሚተዳደር ሲሆን ታንሽ እህቱን መቅደስ ምስጋናዉን ለማሰተማር ሲል ከሊስትሮ ሙያ በተጨማሪ ግድግዳ በማጠብ እና እቃ በመሸከም የሱን እና የእህቱን ህይወት ሲያስተዳድር የቆ ሲሆን አሁን ግን ሁለቱ ኩላሊቶቹ ስራ ስላቆሙ ለመታከም ቀርቶ የሚበሉት የሌላቸዉ ሲሆን በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ወጣት መኳንት ወደ ህንድ አገር ሂዶ መታከም እዳለበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቦርድ ወስኗል ለህክምናዉ ሚያስፈልገዉ ወጭ ደግሞ 600000 ብር በላይ ነዉ፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከረኩት አነዚህ ልጆች ቤተሰብ የሌላቸዉ ከመሆኑ በተጨማሪ ምንም አይነት ገቢ የሌላቸዉ እና እህቱ ገና የ9 አመት ህጻን ስትሆን የወንድሜን ነብስ አድኑልኝ እያለች ወገኖቿን ትማጸናለች ፣ ያለ ወንድሟስ ማን አላት፡፡
ሊስትሮ በመስራት እና ግድግዳ በማጠብ ሲያሰተምራት የነበረዉ ወንድሟ አሁን በህይወትና በሞት መካከል ላይ የሚገኝ ሲሆን የዚህን ወጣት ነብስ ትታደጓት ዘንድ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡
በዚሁ አጋጣሚ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን ላመሰግን እወዳለሁ እስካሁን ዲያሊስስ እያደረገ ያለዉን ወጭ የሸፈነ አሱ ስለሆነ !!!!
እኛስ የነገ ቤታችን ዛሬ እስራ !!!
+251944114215

share like invite comment and help this boy

13/11/2015

ኩዌት ውስጥ ለምትኖሩ በጎ ፈቃደኞች ፡፡
እኛም ሰለወገኖቻችን ምን ማድረግ እንዳለብን እንመካከር ፡፡
በኩዌት የኢትዮጵያውያን ቤተሰባዊ ግሩፕ በሚል በጎ አላማ ተሰባስበን ብዙ ነገሮችን እየሰራን ቆይተናል አሁን ደሞ ያለንበት ወቅትከ 15 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በረሃብ እየተሰቃዩ እንዳሉ እየሰማን ነው ፡፡
ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ሁላችንም እንደኢትዮጵያዊነት ወገንን በቻልነው የማገዝ አላፊነት የሁላችንም ሰለሆነ ሁሉም የአቅሙን ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው ፡፡ ሰለሆነም እኛም በኩዌት የምንኖር ኢትዮጵያኖች ምን ማድረግ እንዳለብን እና በቀጣም ሰለምንሰራው ስራ እንድንወያይ ፈቃደኛ የሆናችው ሁሉ ስልካችውን በውስጥ መሰመር እያሰቀመጣችውልን በዋትሳብ ቤተሰባዊ ግሩፑ ላይ ተወያይተን የአቅማችንን እናድርግ ፡፡

Nod to govt to private visa transfer seen - Kuwait Times 29/10/2015

የምሰራች ቪዛ 18 ይዛችሁ ካምፓኒ መቀየር ላልቻላችሁ

የዚህ ፌስቡክ ተከታታዮች ከዚህ ቀደም የኩዌት መንግስት የመንግስት ፕሮጀክት ቪዛ የያዙ ወደ ሌላ የግል ድርጅት እዳይቀየር መከልከሉ ይታወሳል። ቪዛ 18 ይዛችሁ ካምፓኒ መቀየር ያልቻላችሁ ወደ ፈለጋችሁ ካምፓኒ መቀየር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል ::

http://news.kuwaittimes.net/website/nod-to-govt-to-private-visa-transfer-seen/

Nod to govt to private visa transfer seen - Kuwait Times KUWAIT: Informed sources said Social Affairs and Labor Minister and State Minister for Planning and Development Affairs Hind Al-Subaih will issue a decision to allow the transfer of residencies of workers registered on government contracts to the private sector. The decision stipulates that KD 300 m…

Photos from የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት's post 26/10/2015

የኢትዮጵያዊያን በኩዌት ቤተሰባዊ መርዳጃ ማህበር አባሎች ወደ በኢትዮጵያ ለሚገኘው የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር የሚላኩትን ዕቃዎች በማሸግና ለካርጎ ካምፓኒ በማዘጋጀት ሂደት ላይ ...

Mobile uploads 26/10/2015

በኢትዮጵያዊያን ቤተሰባዊ መርዳጃ ማህበር በኩዌት የተላከውን 109 ኪሎ አልባሳት የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር ተረከቡ ::

"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"

የኢትዮጵያዊያን ቤተሰባዊ መርዳጃ ማህበር በኩዌት በ2007 ዓ/ም ካከናወናቸው ምግባረ ሰናይ ተግባሮች አንዱ በኢትዮጵያ የሚገኘው የወደቁትን አንሱ የነዳያን መረጃ ማህበር ለሚባለው ጣሪና ቀባሪ የሌላቸው አዛውንቶች ግብረ ሰናይ ድርጅት በቤተሰባዊ ግሩፓችን የተሰበሰበውን 109 ኪሎ የተለበሱና አዲስ ልብሶች፤ አንሶላዎችና የንፅህና መጠበቂያዎች በ20/06/2015 ተልኮ ከተወሰኑ መጓተቶች በዋላ የወደቁትን አንሱ የነዳያን መረጃ ማህበር የሚመለከታቸው አካላት ተቀብለዋል ፡፡

የወደቁትን አንሱ የነዳያን መረጃ ማህበር አመራሮችም ለኢትዮጵያዊያን በኩዌት ቤተሰባዊ ማህበር አባላት በሙሉ በበጎ አድራጎታቸው ድርጅት ስር ባሉ ተርጂ አረጋዊያን ስም ከፍተኛ ምስጋኛቸውን በማቅረብ በቀጣይም በእንደዚህ ዓይነት በጎ ምግባር ያላችሁን ተሳትፎ እንድትቀጠሉ ምንም እንኳን በመካከለኛው ምስራቅ (አረብ አገር) ያሉባችሁን ችግሮች ተቋቁማችሁ ከአገር ውጪ ብትኖሩም ወገኖቻችሁን ሳትዘነጉ በራሳችሁ ተነሳሽነት እያደረጋችሁት ላለው ስራ ከፍተኛ ምስጋናችን በድጋሚ ይድረሳችሁ ለሌሎችም በተመቻቸ ሁኔታ ላይ ላሉ ወገኖች ተምሳሌት የሚሆን ስራ ነውና የምትሰሩት ፈጣሪ ይርዳችሁ በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በተጨማሪም ከታች ያለውንም የምስጋና ደብዳቤ ልከውልናል በዚሁ አጋጣሚ መላው የኢትዮጵያዊያን በኩዌት ቤተሰባዊ መርዳጃ ማህበር አባላት ላደረጋችሁት መልካም ትብብር በቤተሰባዊው ማህበር ስም ምስጋናው ይድረሳችሁ በሁለተኛ ዙር ፕሮግራማችንም በቅርቡ እንደሚጀምርና ዝርዝር ሁኔታውን በዚሁ FB ፔጃችን እንደምናሳውቅ እንገልፃለን፡፡

Mobile uploads 02/10/2015

ቴዲ አፍሮ

Mobile uploads 23/09/2015

ኢድ ሙባረክ- Eid Mubarak
لكل مسلم متمنيا لكم عيدا سعيدا للغاية

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል አድሀ በአል በሰላም አደርሳችሁ፡፡

በዓሉ የፍቅር ፤የጤና ፤ የተቸገሩትን የምንረዳበት፤ የታመሙትን የምንጎበኝበትና የሰላም ይሁንልን፡፡

በኩዌት የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር

Mobile uploads 16/09/2015

ጫትና መዘዙ በኩዌት
እህቶቻችን በማያውቁት ወንጀል እስከ 5 ዓመት እየታሰሩ ነው

ዕለተ እሮብ 09 Sep 2015 በኩዌት አየር ማርፊያ ኢትዮጵያዊቷ አምስት ኪሎ ጫት ይዛ ለመግባት ስትሞክር መያዟንና ለተጨማሪ ምርመራ ወደሚመለከተው አካል መላኳን የኩዌት ጋዜጦችና ድረገፆች ዘግበዋል ፡፡

ይህን መሰል ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈፀመ መሆኑና የኢትዮጵያዊያን ስም በኩዌት ጋዜጦችና ደረ-ገፆች በተደጋጋሚ መውጣቱ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል ሆኖም ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም ሆኗል ጉዳዩን የሚያጣራም ሆነ ወደ መፍትሄ የሚወስድ መንገድ ጠፍቷል ፡፡

ጫት በኢትዮጵያና በአብዛኛው የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በነፃነት የሚሸጥና የሚጠቀሙት ሲሆን በኩዌት አገር ህግ ግን በአደንዣዥ ዕፅ ዝርዝር ተመዝግቦ የሚገኝ የተከለከለ በአደንዣዥ ዕፅ ነው፡፡
በአብዛኛው በኩዌት አገር ይህንን አደንዣዥ ዕፅ ይዘው ሲገቡ በኩዌት የኢምግሬሽን ደህንነቶች የሚያዙት በቤት ውስጥ የሚሰሩ እህቶቻችን ሲሆኑ እነዚህ እህቶቻችንን ከሁለት ዓመትና ከዛም በላይ በመስራት ለእረፍት ወደ አገራቸው ሄደው ቤተሰቦቻቸውን ጎብኝተው በሚመለሱበት ጊዜ በኢትዮጵያ ቦሌ አውሮፕላን ማርፊያ እየጠበቋቸው ወደ ኩዌት እንደሚሄዱ ካጣሩ በዋላ እባክሽን ለወንድሜ ፤ለእህቴ በርበሬና ሽሮ ነው ይዘሽልኝ ሂጂ በማለትና ሌሎችም ምክንያቶችን በማቅረብ እነዚህም የዋህ እህቶቻችን በበጎነት ለመርዳትና ለመተባበር ባደርጉት ስራ ኩዌት ኤርፖርት ሲደርሱ ምንም በማያውቁት ነገር ወደ እስርቤት ተወሰደው ወንጀሉን ለማጣራት የመደብደብና ሌሎችም ወንጀሎች ይደርሰባቸዋል በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ የሚገቡና አህምሮአቸውን የሚስቱ ጥቂት አይደሉም ፡፡
በአረብ ቤት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰርተው ቤተሰቦቻቸውና እራሳቸውን ለመርዳት የሚያደርጉት የህይወት ተጋድሎ ሳያንሳቸው በማያውቁት ጉዳይ የግል ጥቅም ባሰከራቸው ወንጀለኞች የህይወታቸው መስመሩን ሲስት ያሳዝናል ይህም ወንጀል በአገሪቱ ህግ እስከ 5 ዓመት እስራት የሚያሳስርና ብዙ እህቶቻችንን በማያውቁት ጉዳይ የሚያስረዳላቸው በማጣት በእስር እንድሚገኙም ይታወቃል ፡፡
ይህንን የተፈጨ ጫት ሌላ ምግብ አስመስለው ለምስኪን እህቶቻችን በመስጠት በማያውቁት ጉዳይ ወንጀለኛ እንዲሆን የሚያደርጉዋቸውና ይህንን ስራ የሚሰሩት ከዚህ ቀደም በኩዌት አገር የጫት በማዘዋወር ህገወጥ ስራ ይሰሩ የነበሩና እና ወደ አገሪቱ ሊያስገቡ ሲሞክሩ ተይዘው የእስር ጊዜአቸውን ጨርሰው ከኩዌት የተባረሩ የአገራችን ዜጎች ናቸው ይህ ነገር አብዛኛውን ኢትዮጵያዊም ሆነ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚያውቁት ጉዳይ ቢሆንም ከኩዌት እንደተለመደው ማንኛውም ችግር በዜጎች ላይ ሲደርስ በዝምታ ማለፉ ነው ሆኖም ዝምታው ቢበቃና ስለመፍትሄው በግልጽነት ብንነጋገር ይህን መሰል ችግር ኢትዮጵያ ሆነው የሚሰሩትን በህግ መጠየቅ የሚቻልበትን ሁኔታ እንዲፈጠርና አብዛኛውን እህቶቻችንም ምንም አይነት ነገር ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት ሰው ተቀብለው እንዳይመጡ ማስተማርና ማንቃት የሁላችንም ሀላፊነት ነው እያልን በመፍትሄው ጉዳይ ላይ ሁላችንም ልንነጋገርበት ይገባል እስኪ አሳባችሁን ኮሜንት ላይ ብታካፍሉንና ብንወያይበት መልካም ይመስለናል ፡፡

Photos from የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት's post 11/09/2015

በጣም ደስ የሚል የዘመን መለወጫ ዋዜማ ነበር ፤ እግዚአብሔር ይመስገን !!!

Photos from የኢትዮጵያዊያን መረዳጃ ቤተሰባዊ ማህበር በኩዌት's post 11/09/2015

እንኳን አደረሳችሁ!!

በአልን ከእህቶቻችን ጋር........
የኩዌት ቤተሰባዊ ማህበር አባላት ቀደም ባሉት ሳምንታት በያዝነው እቅድ መሰረት የበአልን ዋዜማ በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጉዳያቸው እስከሚያልቅ ከሚጠብቁ እህቶቻችን ጋር ደስ በሚልና ባማረ መልኩ የምሳ ግብዣና በቡና ማፍላት ፕሮግራም ያከበርን ሲሆን ይህን ሃሳብ በማፍለቅ እንዲሁም ቀኑ ደርሶም ለፕሮግራሙ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱት የኩዌት ቤተሰባዊ ማህበር አባላት በሙሉ ፈጣሪ የወጣትነት ዘመናችሁን ባርኮ ከዚ በበለጠ መልኩ ዜጎቻችሁንና ሀገራችሁን የምትጠቅሙ ያርጋቹ!!

መልካም በአል !!

03/09/2015

ለጉሩባችን አባላቶች በሙሉ ።

እንደምታውቁት ከወራት በፊት ኢትዬጵያ ለሚገኙ እረጋውያን ከእናንተ የስበስብናቸው አልባሳቶች መላካችን ይታወቃል ።
ሆኖም መሀል ላይ በተፈጠረ የተቀባይ ስም ስህተት ቆይቶብን ባለፈው ሳምንት የተፈጠረው ስህተት ተስተካክሎ የላክነው እቃ ለአረጋውያኑ መርጃ ድርጅት ለወደቁትን አንሱ ገቢ ሆኖሃል ።
ከልባችው ላደረጋችውት በጎነት እና መልካም ስራ እያመስገንን በቀጣይም እብረን የበለጠ እንደምንስራ አንማናለን ።

Mobile uploads 28/08/2015
Want your business to be the top-listed Government Service in Kuwait City?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Kuwait City