Ethiopian Embassy Rabat

Ethiopian Embassy Rabat

Share

This is the official Facebook handle of the Ethiopian Embassy in Rabat, Morocco

Photos from Ethiopian Embassy Rabat's post 13/05/2026

ዋልያዎቹ በመክፈቻ ጨዋታቸው ከግብጽ ጋር አቻ ተለያዩ
በሞሮኮ አስተናጋጅነት ዛሬ በተጀመረው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ግብፅን የገጠሙት ዋልያዎቹ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በመሐመድ ስድስተኛ ኮምፕሌክስ የተካሄደው ጨዋታ ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር።
ኢትዮጵያ የምድቧን ሁለተኛ ጨዋታ ከሦስት ቀናት በኋላ ከአዘጋጇ ሞሮኮ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡

05/05/2026

እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ
ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው።
Happy 85th patriots day!!!⚔️⚔️⚔️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
April 27 is a holiday that Ethiopian heroes overthrew fascist invasion and fully restored Ethiopia's sovereignty.

05/05/2026

እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ

ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው።

አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው። ዓላማውም ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ ነው። ለግል ወይም ለቡድን በተለየ የሚገኝ ነገር የለውም። ለሀገር ከሚገኘው ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ከሚደርስ የዜጋ ድርሻ በቀር።

እናትና አባት አርበኞች ከፋሺስት ጋር የተዋጉት ለሀገር እና ለወገን ብለው ነው። በግል ጥቅም ለማግኘትማ ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት አቋራጭ ነበር። ግን አላደረጉትም።

የአርበኝነት ትግሉ ከሦስት ጠላቶች ጋር የተደረገ ነበር። ከራስ ፍላጎት፣ ከባንዳና ከወራሪ ፋሺስት ጋር። አርበኝነት የራስን ጥቅም ለሀገር ጥቅም ሲባል መተው ነው። አርበኝነት የግል ክብርን፣ የግል ሥልጣንን እና የግል ጥቅምን መሠዋት ነው። ይሄንን ለመቀበል ከጠላት በፊት ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል።

ባንዳዎች ማለት ራሳቸውን ማሸነፍ ያቃታቸው ናቸው። የግል ጥቅምንና ክብርን ማሸነፍ ሲያቅታቸው የሀገራቸውን ክብርና ጥቅም ይሸጣሉ። ባንዳነት ማለት ሀገርን ለራስ ጥቅም በመሸጥ የሚከናነቡት የውርደት ካባ ነው። አርበኞች ከባንዳዎች ጋር ታግለዋል። ባንዳዎች በአንድ በኩል ሀገራችሁን ሽጣችሁ እንደኛ በግል ተጠቀሙ ይሏቸዋል። በሌላ በኩል መንገድ እየመሩ ወራሪውን ያመጡባቸዋል። ያም አልሆን ሲላቸው ሕዝቡን በሐሰተኛ ወሬ ልቡን ይሰልቡባቸዋል።

ዛሬም ሦስቱም ጠላቶች አሉ። መልክና ስም ብቻ ቀይረዋል። በሌላም በኩል ዛሬም በየመስኩ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አሉ።

የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ብሔራዊ አርበኞችን ይፈልጋል። የራስ ፍላጎትን፣ ባንዳነትን እና ወራሪን እምቢ የሚል አርበኝነት።

የኢንዱስትሪ አርበኞች፣ የግብርና አርበኞች፣ የጸጥታ አርበኞች፣ የፖለቲካ አርበኞች፣ የንግድ አርበኞች፣ የዲፕሎማሲ አርበኞች፣ የመንግሥት አገልጋይ አርበኞች፣ የሕክምና አርበኞች፣ የትምህርት አርበኞች፣ ወዘተ. ያስፈልጉናል።

ይሄንን በዓል የምናከብረው የየራሳችንን የአርበኝነት ደረጃ በመገምገም ነው። ለኢትዮጵያ ምን ያህል አርበኞች ነን?

ዛሬም የግል ፍላጎት የሚያሸንፋቸው ደካሞች አሉ። ሀገርን አፍርሰው የግል ቤት መሥራት የሚመኙ። ትልቁን መርከብ አፍርሰው ትንንሽ ታንኳዎችን ለመሸጥ የሚመኙ። ለቅንጥብጣቢ ነገር ውርደትን ለመሸከም የማይሰቀቁ።

ዛሬም ወራሪዎች አሉ። በአካል ሀገርን ለመውረር ካሰፈሰፉት በተጨማሪ ድህነት፣ ኋላቀርነትና ሌብነት የሚባሉ እንደ ሰርዶ ሀገርን ወርረው ሽባ የሚያደርጉ ጠላቶች አሉ። ሀገርን ለባዳ ከሚሸጡት ባንዳዎች እኩል፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚሸጡ ባንዳዎች አሉ። አገልግሎትንና የሕዝብን ሀብት የሚሸቅጡ ባንዳዎች አሉ።

ብሔራዊ አርበኝነት ማለት እነዚህን ሦስት ጠላቶች ታግሎ ማሸነፍ ማለት ነው። ዛሬ የምናየውን የኢትዮጵያ ለውጥና ዕድገት ማስመዝገብ የተቻለው ብሔራዊ አርበኞች በየአካባቢው በመኖራቸው ነው። ብሔራዊ አርበኞች ሦስቱን ጠላቶች እያሸነፉ ቢሆንም ገና ሙሉ በሙሉ ድልን አልተቀዳጁም።
ድሉ እንደ ሚያዝያ 27 የሚታወጀው ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትስትሆን ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ከሚገኙ ኃያል ሀገሮች አንዷ ስትሆን ነው።

ይሄንን ድል እውን ለማድረግ ኢትዮጵያን የሚወዱ የኢትዮጵያ አርበኞች ሁሉ እንዲነሡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 27፣ 2018 ዓ.ም

Photos from Ethiopian Embassy Rabat's post 28/04/2026

የኢትዮጵያና ሞሮኮ የሴት ነጋዴዎች ማህበራት ውይይት አካሄዱ
=============================
ሚሲዮናችን ከራባት ሳሌና ኬኒትራ ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ማህበራት ም/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የበይነ መረብ መድረክ የአዲስ አበባ የሴት ነጋዴዎች ማህበር ከሞሮኮ አቻዎቸው ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ልምድ ልውውጥ በጋራ በሚሰሩባቸው ዘርፎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ በሁለቱ አገራት የሴቶች ንግድ ማህበራት መካከል ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም አንዲሁም በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ ምርቶች፣ በባህላዊ አልባሳት፣ በቡና ፣ በእደ ጥበባት ስራዎች እና በጤና ዘርፍ ላይ ትብብሮችን ለመፍጠር ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም በሁለቱም ወገኖች መካከል የንግድ ጉብኝቶችና ኤግዚቢሽኖች በማዘጋጀት ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማደረስ ከስምምነት ተደርሷል።
በውይይቱ ከአገራችን የአዲስ አበባ ሴቶች ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አቻምየለሽ አሸናፊ እና ባልደረቦቻቸው የተሳተፉ ሲሆን፣ በሞሮኮ ወገን ራባት ሳሌና ካኔትራ ክልል የተለያዩ የሴት ነጋዴዎች ማህበራት አመራሮችና አባሎቻቸው ተገኝተዋል ። የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሚ/ር ሃሳን ሳኪ እንዲሁም ክብርት አምባሳደር ናርዶስ አያሌው በመድረኩ መልዕክት በማስተላለፍ ተሳታፊዎችን አበረታትተዋል። MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 22/04/2026
Photos from Adwa Victory Memorial-የዓድዋ ድል መታሰቢያ's post 17/04/2026

በሞሮኮ መሀመድ ስድስተኛ ዩኒቨርሲቲ (UM6P) የተቋቋመውና ወጣቶችን ወደ አፍሪካዊ ባህል፣ ታሪክ እና ተቋማት ለማቀራረብ ዓላማውን ያደረገው African ID የተሰኘው የተማሪዎች ክበብ 25 የሚሆኑ አባላት በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት እና በአገራችን የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች መጎብኘት ችለዋል። ተማሪዎቹ የአፍሪካውያን ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፣ በቆይታቸው በአገራችን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችንም ለማየት ዕድል አግኝተዋል። Adwa Victory Memorial-የዓድዋ ድል መታሰቢያ The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia@followers

Photos from Ethiopian Embassy Rabat's post 17/04/2026

የኢትዮጵያና የሞሮኮ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች አምራቾች መካከል የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ
====================================================
ሚሲዮናቸ‍ን የኢትዮጵያና የሞሮኮ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች አምራቾች ማህበር በጋራ ትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ በዌቢናር ውይይት እንዲያካሄድ ባመቻቸው መድረክ በሁለቱ አቻ ተቋሞች መካከል ሰፋ ያለ ውይይት ከተካሄደ በኋላ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክሩ የመግባቢያ ስምምነቶችን ለመፈራረም፣ የጉብኝት ልውውጥ ለማካሄድ፣ የጋራ ኢንቨስትመንቶችን (Joint Ventures) ለማበረታት፣ የማምረት አቅምን የሚያጠናክሩ የቴክኒካል ልምድ ልውውጦችን ለማካሄድ ከስምምነት ተደርሷል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ልማት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አላምረው አያልነህ፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና ጋርመንት አምራቾች ማህበር ሴክሬታሪ ጄኔራል አቶ አጋዚ ገብረየሱስ የተሳተፉ ሲሆን፣ በሞሮኮ ወገን ደግሞ የታንጀር-ቴቱዋን-አል ሆሴማ (Tanger-Tetouan-Al Hoceima) ክልል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾች ኢንዱስትሪዎች ማህበር (AMITH) ፕሬዝዳንትን የሆኑት Mr Omar Kadaoui፣ እንዲሁም የሞሮኮ የጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች ኢንዱስትሪዎች ማህበር (AMITH) የክልሉ ፕሬዝዳንትን Mr. Yassine Arroud ተሳትፎ አድርገዋል። The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

Photos from The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia's post 16/04/2026
14/04/2026

ማስታወቂያ
ክቡራን ተገልጋዮቻችን ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ኤምባሲው የሰነድ ማረጋገጥ እና የውክልና አገልግሎቶችን በDigital MOFA መተግበሪያ ብቻ የሚሰጥ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
መተግበሪያውን ባሉበት ሆነው ከApp Store ወይም Play Store በማውረድ አገልግሎቶቹን ማገኘት እንደሚችሉ እየገለጽን፣ እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚችሉ እየገለጽን፣ ለእነዚኅ አገልግሎቶች ወደ ኤምባሲው በአካል መምጣት የማያስፈልግ መሆኑን እናሳስባለን። ለግንዛቤ ያህል በመተግበሪያው እንዴት ውክልና ሥልጣን መስጠት እና ማንሳት እንደሚቻል ከታች ባለው ምስል መመልከት ይቻላል።

11/04/2026
07/04/2026

The Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Rabat expresses its profound sorrow at the passing of Veteran Diplomat Ambassador Konjit Sinegiorgis, a distinguished and dedicated servant of Ethiopia’s foreign service. Ambassador Konjit, who began her career with the Ministry of Foreign Affairs in the 1950s, devoted decades of exemplary service to advancing Ethiopia’s diplomatic interests, holding key positions across bilateral and multilateral arenas.
H.E. Ambassador Nardos Ayalew and all staff of the Embassy in Rabat extend their heartfelt condolences to her family, friends, and colleagues, and pay tribute to her long-lasting legacy of professionalism, dedication, and service to the nation

𝐕𝐞𝐭𝐞𝐫𝐚𝐧 𝐃𝐢𝐩𝐥𝐨𝐦𝐚𝐭 𝐀𝐦𝐛𝐚𝐬𝐬𝐚𝐝𝐨𝐫 𝐊𝐨𝐧𝐣𝐢𝐭 𝐒𝐢𝐧𝐞𝐠𝐢𝐨𝐫𝐠𝐢𝐬 𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐬 𝐀𝐰𝐚𝐲

Veteran diplomat Ambassador Konjit Sinegiorgis, who had been receiving medical treatment, has passed away.

Ambassador Konjit joined the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs at a young age in the 1950s and went on to build a long and distinguished career spanning several decades. Throughout her service, she assumed major responsibilities across a wide range of diplomatic roles, making significant contributions to Ethiopia’s foreign service.

Widely recognized as Ethiopia’s second female Ambassador, following Yodit Imru, Ambassador Konjit served as Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary in Ethiopia’s diplomatic missions in Ottawa, Cairo, Tel Aviv, and Vienna during her career.

In addition to her bilateral assignments, she represented Ethiopia in key multilateral institutions. Notably, she served as Permanent Representative to the African Union and to the United Nations Economic Commission for Africa (ECA).

From June 2017 to September 2018, Ambassador Konjit also served as a Special Advisor in the Intergovernmental Authority on Development (IGAD)-led South Sudan peace process, where she contributed her extensive diplomatic experience to advancing regional peace efforts.

The Ministry of Foreign Affairs expresses its deep sorrow at the passing of Ambassador Konjit and extends its heartfelt condolences to her family, friends, and colleagues.

Want your business to be the top-listed Government Service in Rabat?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


4, Avenue Ahmed Balafrej, Rue Mohamed Ibnishaq, Souissi
Rabat
10100

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00