የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት

የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት

Compartir

Información de contacto, mapa y direcciones, formulario de contacto, horario de apertura, servicios, puntuaciones, fotos, videos y anuncios de የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት, Public & Government Service, Calle Gabela, Chihuahua.

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 02/10/2025

የክልሉ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ምቹ የስራ አከባቢን ለመፍጠር ያከናወናውን የቢሮ እድሳት እና ማስፋፊያ አጠናቆ አስመርቋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የፌደራል እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (መስከረም 22/2018) ዓ.ም

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) እንደገለፁት የክልሉ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የተቋቋመበትን ዋና አላማ ለማሳካት እያከናወናቸው ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በቂ እውቀት ያለውን ዜጋ ለመፍጠር እንዲቻል ተቋማቱን ማጠናከር እና ማስፋት ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ የሚገኙ ሌሎች ተቋማቶች ተሞክሮውን በመውሰድ ቢሮዎቻቸውን ለስራ ምቹ እንዲያደርጉ እና ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣን እና ጥራት ያለው እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰሎሞን ሶካ እንዳሉት ሀገራችን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ጀምራ በመጨረስ እና አዳዲስ ስራዎችን በመጀመር የህዝቦችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተጋች ነው ብለዋል።

የክልሉ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ከዚህ በፊት በነበረው ምልከታ ተቋሙ የቢሮ እጥረት ያለበት እና ፅዱ አለመሆኑን ከተመለከትን በኋላ በፍጥነት መታደስ እና ማስፋፊያ ሊደረግበት እንደሚገባ ከተቋሙ ጋር በማቀድ በአንድ አመት ውስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ትውልድን የሚቀርፁ እና ክህሎት እና እውቀት ያለው የሰው ሀብትን የሚያበቁ ተቋማት ምቹ ቢሮዎች እና ፅዱ አካባቢ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም የክልሉ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት በሚመጥነው መልኩ መታደሱ የሚበረታታ እና በቀጣይም ይህ ተግባር በሌሎች ተቋማትም መጠናከር ያለበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሯች ባያክ በበኩላቸው ቢሮው እና ተጠሪ ተቋማቱ ጥራት ያለው አሰራር እንዲኖራቸው ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

በተለይም ክህሎት መር ተግባራትን ከማከናወን ጎን ለጎን ተቋማትን የመገንባት እና የማሻሻል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የአገልግሎቱ ዳይሬክተር አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ እንደገለፁት ተቋሙ የተጣለበትን ሀላፊነት በጥራት እና ፍጥነት ማከናወን እንዲችል ምቹ አካባቢን መፍጠሩ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።

ከዚህ በፊት የቢሮ እጥረት ያለ በመሆኑ እና አካባቢው ፅዱ ባለመሆኑ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት አዳጋች እንደነበር ገልፀዋል።

የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር እንዲሁም ሀብት በማሰባሰብ ተቋሙን የማደስ እና ማስዋብ ስራ ለመስራት መቻሉን አስረድተዋል።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 25/02/2025

የጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የቢሮ እድሳት እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ለቢሮ እድሳቱ የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉም ተመላክቷል።

ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (የካቲት 18/2017 ዓ.ም)

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ እንደገለፁት ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል የቢሮ እድሳት ማድረጉ አስፈልጓል ብለዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት የእድሳትና የቢሮ ማስፋፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የቢሮ እድሳቱ ሰራተኞች ከደሞዛቸው፣ ከሚያገኙት ውሎ አበል እና ከምዘና ማዕከላት መሰብሰቡን ጠቁመው ከታዋቂ ግለሰቦችና ባለሀብቶች የቁሳቁስ ድጋፍ ማግኘታቸውንም አስረድተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የተቋሙ ቦርድ አባል መስሪያ ቤቶች የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም አመልክተዋል።

የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ተቋሙ ለስራ ምቹ እንዲሆን እንዲሁም የተደራጀና ጥራት ያለው ስራ መስራት እንዲችል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ኡቶንግ ገልፀዋል።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 06/02/2025

የጋምቤላ ሞያብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት በ 29/05/2017 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የምያ መስኮች በ ጎደሬ ወረዳ ምዘና(coc) በመስጠት ላይ ይገኛል ።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 01/02/2025

የክልሉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግልትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎትን ለማጠናከር እየተሰራ እንደሚገኝ የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የእንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የሌሎች ተቋማት የስራ ሀላፊዎች የጋምቤላ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የስራ ሁኔታን ተመልክተዋል።

የጋምቤላ ክልል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የቢሮ እድሳት እያደረገ ይገኛል።

ተቋሙ ለስራ ምቹ እንዲሆን እንዲሁም የተደራጀና ጥራት ያለው ስራ መስራት እንዲችል እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የአገልግሎቱ ዳይሬክተር አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ እንደገለፁት ተቋሙ የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል የቢሮ እድሳት ማድረጉ አስፈልጓል ብለዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት የእድሳትና የቢሮ ማስፋፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም አገልግሎቱን ጠንካራ በማድረጉ ረገድ በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር ዶ/ር እንዳሉት ተቋሙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት እንዲሻሻል ለማድረግም ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በተለይም የአገልግሎቱ ህንፃ እድሳት የቢሮ እቃዎች ድጋፍ፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎች ለአገልግሎቱ እንደሚደረጉም አስታውቀዋል።

በምልከታና ውይይቱ ላይ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሯች ባየክ እንዲሁም የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት ተገኝተዋል።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 14/01/2025

በጋምቤላ ክልል ዜጎች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተመዘኑ መሆን እንዳለባቸዉ ተገለፀ።

በልምድ ለተገኘ ዕዉቀት ምዘናን በተመለከተ በከተማዉ ለሚገኙ ባለሆቴሎች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ የዉይይት መድረክ ተካሂዷል።

ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት (ጥር 6/ 2017 ዓ/ም)

የክልሉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ በዉይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት በልምድ ለተገኙ ዕዉቀት ምዘና አስፈላጊነቱ ከኢ-መደበኛ ወደ መደበኛ ለማሸጋገር ፣ የስራ እድል ለማመቻቸት፣ ፍትሃዊነት ለማስፈን ፣ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት፣በባህል የተገኙ ልምዶችን እዉቅና ለመስጠት ነዉ ብለዋል።

ተያይዞም ምደባ ፣ቅጥር ፣ዝዉዉር ፣የረዥም ጊዜ የትምህርት ዕድል ፣ማህበራዊ አካታችነት እና የራስ መተማመንን ያበረታታል ብለዋል።

በከተማዉ ባሉ ሆቴሎች በልምድ ተሰማርተዉ የሚሰሩ ሰራተኞች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ወደ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት በመምጣት ተመዝነዉ የዕዉቅና ሰርተፍኬታቸዉን መያዝ እንዳለባቸዉ ኃላፊዉ አሳስበዋል።

በልምድ የተገኘን እዉቀት ዕዉቅና መስጠት ሂደት ሴቶች፣ስደተኞችን ፣ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ አካላት እንዲሁም ለተፈናቃዮች ዕድል የሚሰጥ ነዉ ብለዋል።

በባህልና ቱሪዝም ቢሮና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደርባቸዉ በበኩላቸው በከተማዉ ያሉ ሆቴሎች ከግንባታዉ ጀምሮ እስከ አገልግሎት አሰጣጥ ድረስ ያለዉ ሂደት ጥራቱን የጠበቀ ሆቴል መሆን አለበት ብለዋል።

የሆቴሉ ሰራተኞች ከጤና ሁኔታ ጀምሮ እንዲሁም በልምድ የተገኘ እዉቀትን በምዘና ዕዉቅና መስጠት የሆቴሉንም ደረጃ ለማስጠበቅ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ባለሆቴሎች ለተገልጋዩ ዉብ እና ማራኪ እንዲሁም ተወዳዳሪ ለመሆን መስራት አለባቸዉ ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸዉ በልምድ ለተገኘ እዉቀት ምዘና መደረጉ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልፀዋል።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 03/01/2025

በጋምቤላ ክልል ብሄራዊ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓትን ውጤታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሯች ባየክ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) አመዘጋገብና አጠቃቀም ዙሪያ ለተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም)

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሯች ባየክ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ በክህሎት እና ዘመኑ በዋጀው ቴክኖሎጂ ባለመመራቱ በርካታ ፈተናዎች ሲያጋጥሙ ቆይተዋል ብለዋል።

በክልሉ ያሉት የግልና የመንግስት ተቋማት መደበኛና አጫጭር የሙያ ስልጠና ሰልጣኞች በኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ስርዓት በተቋምም ሆነ በግል ስልኩ ላይ ተመዝግበው ተገቢውን ዝርዝር መረጃ ሊሞሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተለይም የስራ አጥ መለያ ቁጥር ይዘው ወደ ስልጠና እንዲገቡ ለማድረግና ዘመኑ የፈቀደው የስራ ገበያ መረጃ ተጠቅሞ በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ስልጠናው ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀዋል።

በክልሉ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ተቋማት የመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎችን በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ላይ ተመዝግበው የስራ አጥ መለያ ቁጥር ይዘው መሰልጠን አለባቸው ብለዋል።

በመጨረሻም ተመርቀው ስራ በሚፈልጉበት ጊዜ ያጠረና በተመረቁበት ሙያ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የክልሉ የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ በበኩላቸው ብሄራዊ የስራ ገበያ መረጃ ስርአት ግንባታ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ወቅታዊና የተደራጀ የስራ መረጃን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል አሰራር ነው ብለዋል።

ብሄራዊ የስራ ገበያ መረጃ ስርአት በተለይ ወጣቶችን በሁሉም የስራ መስኮች ተጠቃሚ በማድረግና በአገሪቷ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ላቅ ያለ አስተዋፆኦው ያለው መሆኑን አብራርተዋል።

በመሆኑም የመረጃ ስርዓት ግንባታው እውን የሚሆነው ሁሉም ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ሚና ሲወጡ መሆኑንም አቶ ኡቶንግ ተናግረዋል።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 14/12/2024

የጋምቤላ ሞያብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት በ 2/04/2017 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የምያ መስኮች በጋምቤላ ከተማ ምዘና(coc) በመስጠት ላይ ይገኛል ።

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 09/12/2024

የጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ምዘና ቦርድ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን በማድረግ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ፡፡፡
የ መያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት (ህዳር 28/ 2017 ዓ.ም)

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 04/11/2024

የጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መ የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት አዲስ ከተሾመት አመራር ሮች ጋር ትውውቅ አድርገዋል ።


ጥቅምት 25/2/2017ዓ.ም

Photos from የ ጋምቤላ ክልል የ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት's post 09/07/2024
¿Quieres que tu empresa sea el Servicios Gubernamentales mas cotizado en Chihuahua?

Haga clic aquí para reclamar su Entrada Patrocinada.

Localización

Página web

Dirección


Calle Gabela
Chihuahua
31313