02/06/2026
የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah, Consulate & Embassy, 8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325, Jeddah.
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንስላ ጽ/ቤት - ጅዳ ::
Consulate General of The Federal Democratic Republic of Ethiopia Jeddah القنصلية العامة لجمهورية اثيوبيا الاتحادية الديمقراطية بجدة
02/06/2026
01/06/2026
የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።
Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.
Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.
The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.
On this historic day:
* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;
The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.
It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.
30/05/2026
በዘንድሮው የ1447 ዓ.ሒ (2018 ዓ.ም) የሐጅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ሁጃጆች የሐጅ ስነ-ሥርዓታቸውን በስኬት አጠናቀቁ።
(ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ጄዳ) የዘንድሮው የሐጅ መርሃ-ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጀነራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በተገኙበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ለዚህ ታላቅ ስኬት የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ በጋራ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ሁጃጆችን በጊዜ በመመዝገብ፣ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ ተደራሽ በማድረግ፣ በጤና አጠባበቅና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ባሳየው የላቀ አፈፃፀም ከሳዑዲ አረቢያ የሀጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ከፍተኛውን የአልማዝ (Diamond) ሽልማት በዘንድሮው የሐጅ ማጠናቀቂያ መርሃ-ግብር ላይ ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በሳዑዲ አረቢያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራና የሐጅ መርሃ-ግብር አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
29/05/2026
. 📌ታድሶ የመጣ ፓስፖርት📌
*********************
አዲስ ፓስፖርት ተሰርቶ የመጣላችሁ ዜጐቻችን የስም ዝርዝራችሁን በማየት እና ተራ ቁጥራችሁን በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመቅረብ ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ቆንስላ ጽ/ቤቱ ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ፡-
አመልካቾች ፓስፖርት ለመውሰድ ስትመጡ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ላይ ከስማችሁ ትይዩ የተመለከተውን የኮድ ቁጥር መዝግባችሁ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችዃል፣
በተጨማሪም ሙሉ ዝረዝሩን በቆንስላ ጽ/ቤቱ የቴሌግራም ቻናል በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
27/05/2026
. 📌ማስታወቂያ📌
*********************
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲያስፖራ ደንበኞች የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመርን በተመለከተ መኖሪያቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፋይዳ ያልተመዘገቡ ወይም ተመዝግበው ከሀገር ውጭ ከሆኑ በሕጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት እግዱን ለማስለቀቅ ከፈለጉ ከኢትዮጵያ ውጭ መኖራቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ለምሳሌ- የትምህርት ማስረጃ & የህክምና ማስረጃ & የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ & ከውጭ ሀገር የተሰጠ ውክልና የመኖሪያ ፈቃድ/የሎው ካርድ & የስራ ፈቃድ በህጋዊ ወኪሎቻቸው በኩል (ውክልናው ወኪሎቹ ውጭ መሆናቸውን የሚገልጽ ከሆነ) በማቅረብ መስተናገድ ይችላሉ።
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
24/05/2026
በሳኡዲ ዐረቢያ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጄዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሽሜሲ የዲፖርቴሽን ማዕከል በመገኘት ከ 3000 በላይ ዜጎችን የጉብኝት እና የመመዝገብ ስራ ዘመቻ አከናወነ።
(ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ጄዳ) በክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ የተመራ የቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማት እና ሰራተኞች፣ የጅዳ ኢትዮጵያዊያን ኮሚዩኒቲ አባላት እንዲሁም በጄዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተውጣጣ ቡድን በማቆያ ጣቢያው በመገኘት ዜጎችን የመጎብኘት: ዜግነት የማጣራት፣ ልዩ ድጋፍ የሚሹትን የመለየት እንዲሁም የጉዞ ሰነድ የጉዞ ሰነድ የማዘጋጀት 3000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት ተሰጥቷል:: በመርሀ ግብሩ ላይም ክቡር አምባሳደር እንዳሉትም ዜጎች የስደትን አስከፊነት እና በመንገድ ላይ የሚደርስባቸውን እንግልት ተረድተው እና በሀገራቸው ተረጋግተው ሂወታቸውን እንዲቀጥሉ ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ እና እያደረገ እንዳለ ገልፀዋል። ለዚህም ከ 9 ወር በላይ ሳይቋረጥ ለቀጠለው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ተግባር ትኩረት አድርጎ ለሚሰራው የዲፕሎማሲ ማሳያ እንደምሳሌ በመጥቀስ አስረድተዋል። በተጨማሪም ዜጎች በውጭ ሀገር ሲኖሩ የሚኖሩበትን ሀገር ህግ፣ስርዐት እና ባህል ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የእረፍት ግዜያቸው መስዋት በማድረግ በስራ ዘመቻው ለተሳተፉ በሙሉ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል::
22/05/2026
በሳዑዲ ዓረቢያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከዲር፣ የ1447ኛውን ዓመተ ሂጅራ የሐጅ ሥነ-ሥርዓት ለማከናወን ጄዳ ከተማ ገቡ።
(ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ጄዳ)፡- በሳዑዲ ዓረቢያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከዲር፣ የ1447ኛውን ዓመተ ሂጅራ የሐጅ ሥነ-ሥርዓት ለማከናወን ጄዳ ከተማ ገብተዋል። አምባሳደሩ ጄዳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ እንዲሁም የዘንድሮውን የሐጅ እንግዶችን በክብር እንዲቀበሉ እና ችግር የሚደርስባቸውን ሁጃጆች እንዲከታተሉ በቆንስላ ጽ/ቤቱ በተቋቋመ የሀጅ ሥነ-ሥርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ አምባሳደሩም ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
21/05/2026
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከአረቢያን ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ጋር ውይይት አካሄደ።
(ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጄዳ) የጅዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት የቢዝነስ ዲፕሎማሲ የሥራ ዘርፍ፣ ከArabian Plastic Industry Chief Commercial Officer ከሆኑት አቶ Tareq Atef Al Sunna ጋር ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በጽሕፈት ቤቱ ውይይት ባደረገበት ወቅት ኩባንያው በሀገራችን ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በበየነ-መረብ (Online) ለመወያየት ያለውን ፍላጎት ገልጾ ነበር።
በዚህም መነሻነት፣ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የዙም (Zoom) ስብሰባ እንዲመቻች ተደርጎ የጋራ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ ከአረቢያን ፕላስቲክ በኩል አቶ Tareq Atef Al Sunna ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ኩባንያቸው በተለይም በአውቶሞቲቭ (automotive)፣ በቤትና ሕንጻ ልማት (real estate)፣ በማኑፋክቸሪንግ (manufacturing)፣ በማዝናኛ (entertainment)፣ በፋይናንስ (financing)፣ በሙያዊ አገልግሎቶች (professional services)፣ እንዲሁም በንግድ (trading and distribution) ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩል ደግሞ አቶ እስራኤል ተስፋዬ “ለምን በኢትዮጵያ ኢንቨስት ይደረጋል?” በሚል ርዕስ ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል። በማብራሪያቸውም የሀገሪቱን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ በቀላሉ ሊሰለጥን የሚችል ሰፊ የሰው ኃይል፣ የመንግስትን የሪፎርም እርምጃዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አቅምን፣ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችን እንዲሁም ያሉትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች በዝርዝር አብራርተዋል።
በማጠቃለያውም ከሁለቱም ወገኖች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ አቶ Tareq Atef Al Sunna ኢትዮጵያን ለመጎብኘትና በቀጣይም ግንኙነቱን ይበልጥ በማጠናከር የኢንቨስትመንት ፍላጎታቸውን ከግብ ለማድረስ በቅርበት መሥራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
21/05/2026
በጅዳ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ከ350 በላይ ለሚሆኑ አመልካች ወላጆች የህጻናት ሊሴ-ፓሴ አገልግሎት ሰጠ።
(ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጄዳ) በጄዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ከ350 በላይ የሚደርሱ ህፃናት ወደ ሀገር ቤት ይዘው ለመግባት ላመለከቱ ወላጆች የሊሴ ፓሴ አገልግሎት ተሰጠ። አገልግሎቱ የተሰጠው ቀደም ሲል ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ለነበሩ አመልካቾች ሲሆን፣ በዚህ የዘመቻ ስራ ላይ የቆንስላ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሙሉ ባደረጉት ተሳትፎ ስኬታማ አገልግሎት መስጠት ተችሏል። በቀጣይ አመልካቾች በምዝገባ ቅደም ተከተላቸው መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል ።
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
21/05/2026
. 📌ማስታወቂያ📌
*********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325
Jeddah
495JEDDAH21411
Opening Hours
| Monday | 8:30am - 3pm |
| Tuesday | 8:30am - 3pm |
| Wednesday | 8:30am - 3pm |
| Thursday | 8:30am - 3pm |
| Sunday | 8:30am - 3pm |
