25/07/2022
56.6 ቢሊዮን ዶላር እዳ‼️🤔
የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣት ይዟል።
የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር።
ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ።
የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ።
እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር።
የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ግማሽ ያክል መሆኑን ተከትሎ ባሉ ወቅታዊ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት አበዳሪዎች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የብድር አከፋፈሉ ዙሪያ ውይይት ይዘዋል።
ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ናቸው ስብሰባውን የሚመሩት።
የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ዕዳ ስለማሸጋሸግ ውይይት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት ነበር። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ጉዳዩን አጓተተው።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች ኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ ላለባቸው ዕዳ አስተያየት እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ናቸው።
የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዕዳ ኖሮባቸው ተጨማሪ ፈተና እየገጠማቸው ላሉ አገራት መፍትሔ መበጀት አለበት ሲሉ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል
24/07/2022
ኢትዮጵያ
እሷ እራሷ ኢትዮጵያን ትመስለኛለች።
"እኔነት ዬልቅ እኛ ከቀደመ ሀገር አሸናፊ ትሆናለች።" ደራርቱ ቱሉ!
24/07/2022
#በደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበሩ 45 የአማራ የልዩ ሀይል አባላት በ 20 ሺ ብር ዋስትና መፈታታቸው ተነገረ!!!
@በደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት በእስር የነበሩ 45 የልዩ ሀይል አባላት ከእስር ተፈቱ። የልዮ ሃይል አባላቱ ከታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የእስቴ ወረዳ ፖሊስ ተይዘው ታስረው መቆየታቸው ይታወሳል።
@በዚህም በወረዳው ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ከቆዩ በኋላ ፍርድቤቱ የታሰሩ የልዩኃይል አባላትን በነፃ ልቀቁ ቢላቸውም አንደገና የማጣራው ጉዳይ አለኝ በሚል የእስቴ ወረዳ ደብረታቦር ማረሚያ ቤት ይቆዬልኝ በማለት ደብረታቦር ማረሚያ ቤት አስገባቸው ።
@ከዚህ በኋላም ያለምንም ጥያቄ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተደርገዋል። የዞኑ ፍትህ ልዩኃይሎችን ወደ ብርጌዳቸው እንዲመለሱ ቢጠይቅም ተግባራዊ አልተደረገም ነበር ።
@ይሁን እንጂ እስረኞቹ ከወራት ስቃይ በኋላ በ 20 ሺ ብር ዋስትና መፈታታቸውን የአካባቢው የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠው
24/07/2022
#በካሊፎርኒያ የደረሰው የእሳት አደጋ በርካታ መኖሪያ ቤቶችን አወደመ‼️
@የእሳት አደጋው በትላንትናው ምሽት በግዛቷ መስፋፈቱን ተከትሎም ከ6 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መጠየቃቸው ነው የተዘገበው፡፡
@በአደጋው ቢያንስ አስር ህንጻዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ከ2 ሺህ በላይ ህንፃዎች አደጋ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
@አርብ የተከሰተውን የእሳት አደጋ የመከላከል ጥረት ቢደረግም እስከ ቅዳሜ ከሰዓት ባለው ጊዜ 6 ሺህ ሄክታር ቦታ ማቃጠሉን ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡
@አሁን ላይ የእሳት አደጋውን መስፋፋት ለማስቆም ከ400 በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየተረባረቡ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ የእሳት አደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ቀደም ሲል በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት የተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት በቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
አሁን ላይ በአውሮፓ ደኖች ላይ የተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት ተባብሶ ቀጥሏልም ነው የተባለው፡፡
የዓለም የሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ኃላፊ ፔቴሪ ታላስ ስለጉዳዩ በሰጡት መግለጫም፥ ከዚህ በኋላ የሙቀት ማዕበል በአውሮፓ የሚስተዋል ይሆናል፤ ከአሁኑ የባሰ ተፅዕኖም ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡
የሙቀት ማዕበሉ በብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ቤልጂዬም፣ ኔዘርላንድስ፣ ግሪክ፣ ስፔን እና ጣልያንን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት መከሰቱን ሲጅቲኤን እና ቢቢሲ ዘግበዋል፡፡
Esat tv
24/07/2022
#በምዕራብ ወለጋ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ1 ሺሕ 100 በላይ ንጹሐን መገደላቸው ሪፖርት ተደረገ!!!
@በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ1 ሺሕ 100 በላይ ንጹሐን መገደላቸውን ሪፖርት የተደረገው በጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
@በምዕራብ ወለጋ ከተገደሉት ሰዎች መካከል 28ቱ በአንድ ቀን የተገደሉ አመራሮች መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
በዞኑ ከተገደሉት ንጹሐን ውጪ ወደ ሦስት ቢሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት መታጣቱ ነው የተገለጸው፡፡ በጨፌው ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ደበላ የተገደሉት የአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ በንጹሐን ላይ ጥቃት ሲደርስ ለጥቃቱ መንግሥት ተጠያቂ የሚያደርገው ሸኔ የሚለውን ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለውን ቡድን ነው፡፡
Esat tv
24/07/2022
| ኢትዮጵያ 4ኛውን ወርቅ አገኘች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን የ5000 ሜትር ፍጻሜ 1ኛ ሆና በመጨረስ ለሀገሯ 4ኛውን የወርቅ ሜዳለያ አስገኝታለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ዳዊት ስዩም 3ኛ በመውጣት ለሀገሯ የነሃስ ሜዳለያ አስገኝታለች።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ 5ኛ በመሆን አጠናቃለች።
እንኳን ደስ አለን!
22/06/2022
የናፈቀኝ ያበጠውን ማስተፍንፈስ አሁን አማራ የመልስ ምት መስጠት ቢጀምር ይወገዝ ይሆናል እኮ?
እናያለን!!!
21/06/2022
በነገራችን ላይ ይሻሻል እንደሆን፣ ሁልጊዜ በአመፅ መንግስት መጣል ባህላችን እንዳይሆን በሚል ችላ ብለነው እንጅ የአብይን መንግስት ለመጣል ኦነግ በአንድ ቀን ከሚገድለው ህዝብ ያነሰ ቁጥር ብቻ ገብረን አብይን በሳምንታት መጣል እንችላለን።አቅሙም ከበቂ በላይ አለን
ይሄ መካሪ አልባ ሰው የዘነጋው ይህንን ነው።
21/06/2022
ጥያቄ አለኝ !!
ባለፈው በሰሜኑ ጦርነት ግዜ ዶክተር አብይና ቱሪናፋ ካድሬዎቻቸው ደጋግመው እንደነገሩን …
አብይና የመከላከያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ በሚገኘው የደህንነት ቢሮ መቆጣጠሪያ ክፍል ሆነው በሳተላይት አማካኝነት …እነ ደብረ ጺዎንን እንኳን ስብሰባቸውን ፈሳቸውን ሳይቀር እናዳምጣለን ሌት ከቀን ምን እንደሚሰሩ እያየናቸውን ነው ብለውን ነበር
ዛሬስ ይሄ መቆጣጠሪያቸው ወለጋ ላይ መሽጎ ደም እየጠጣ ያለውን ገዳይ የሼኔ …ቡድን የትና ምን እየሰራ እንደሆነ ይቆጣጠር ይመለከት ይሆን?? ወይስ ለኦነግ ግዜ ለግሞ ይሆን???
ይሰማል ብልጽግና …???
21/06/2022
killed civilians genocide amahara aby ahemmed group 😥😥😥😥😥