06/05/2026
ትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ በኦፍላይን የሚሰራና ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን ማመንጨት የሚችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አዋለ።
ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የዕለት ተዕለት የሥራ ጫና በእጅጉ የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት (Fully Offline) የሚሰራ እና ራሱን ችሎ ተግባራትን የሚያከናውን ኤጀንቲክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Agentic AI Teacher Assistant) መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።
የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ መተግበሪያ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ (Cloud) ቴክኖሎጂ ላይ የማይተማመን፣ ይልቁንም በአካባቢያዊ ኮምፒውተር (Local Machine) ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሰራና በውስጥ አቅም የበለጸገ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
የ AI መተግበሪያው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን መጽሃፍቶች በሙሉ ዳታሴት (Dataset)አድርጎ በመውሰድ፣ መጻሕፍቱን ሙሉ በሙሉ እንዲመረምርና እንዲገነዘብ (Model Fine-Tuning) ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ተገልጸዋል።
መተግበሪያው የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ያዘጋጃል፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ያመነጫል፣ እንዲሁም ማስተማሪያ ስልቶችን (Pedagogical Strategies) በራሱ ማቀናጀት ይችላል። ይህም መምህራን በተለመዱ የዕለት ተዕለት የቢሮክራሲ ተግባራት የሚያጠፉትን ውድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ያስቀርላቸዋል ብለዋል።
መተግበሪያው መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ቀጥታ ለሚኖራቸው ግንኙነት በቂ ጊዜ እንዲያገኙ ከመርዳቱም ባሻገር፣ የመምህራንን የማስተማር ብቃትና አቅም (Capacity Building) ስለሚያጎለብት የትምህርትን ጥራት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ዶ/ር ዘላለም ጠቅሰዋል።
ቴክኖሎጂው ምንም ዓይነት ከፍተኛ የሃርድዌር ዝርዝር (High-end specifications) ሳይጠይቅ በቀላሉ በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ቀላል ሞዴል (Lightweight LLM) መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚነው ተናግረዋል።
መተግበሪያው በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማስገኘቱን የገለጹት ኃላፊው፣ ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ መምህራንና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱንም አብራርተዋል።
የአይሲቲ ክፍሉ አማካሪ ሙሉነህ አጥናፉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ይህ የኤ አይ መተግበሪያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያካሂደው አጠቃላይ የትምህርት ዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
የኤ አይ መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ በኦፍላይን (Offline Mode) የሚሰራ በመሆኑ የሚኖሩት የቴክኖሎጂ ጥቅሞች የዲጂታል ልዩነትን ማጥበብ (Bridging the Digital Divide): መተግበሪያው በተለየ ሁኔታ የኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው ወይም በጣም ውስን በሆነባቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለምንም መቆራረጥ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።
ይህም በከተማና በገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የትምህርት ጥራት ልዩነት (Digital Divide) በከፍተኛ ደረጃ ለማጥበብ እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል።
የመሠረተ ልማት ወጪን ማስቀረት (Zero Infrastructure & Subscription Costs) በተመለከተም መተግበሪያው አንዴ ኮምፒውተር ላይ ከተጫነ በኋላ ምንም ዓይነት ወርሃዊ የኢንተርኔት ካርድ፣ የኔትዎርክ ዝርጋታ ወይም የኤ አይ አጠቃቀም ክፍያ እንደማይጠይቅም አስረድተዋል።
ይህ የኤ አይ መተግበሪያ የመምህራኑን የመማር ማስተማር ሥራ ዘመናዊና ቀላል ከማድረጉም ባሻገር፣ ተማሪዎች በተከታታይ ምዘና (Continuous Assessment) የተሻለ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ውጤታቸውን እንደሚያሻሽል አብራርተዋል።
በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው የ Ethiopia Education Transformation Operation for Learning (ETOL) ፕሮጀክት ለዚህ የኤ አይ መተግበሪያ የሙከራ ደረጃ (Pilot) ትግበራ እና ቀጣይ የማስፋፋት ሥራዎች አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተገቢውን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ (Infrastructure Establishment) በማመቻቸት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግም ዶ/ር ሙሉነህ አመልክተዋል።
Ministry of Education Ethiopia
05/28/2026
ኢ/ር ታከለ ኡማ በትውልድ ቦታው ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስገነባ።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ጎሮሶሌ ከተማ፣ በዓይነቱ ለየት ያለና ዘመናዊ የሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከተለያዩ ድርጅቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በማስገንባት ለአገልግሎት መዘጋጀቱ ተገለፀ።
ይህ "በረዋቅ" የተሰኘው ትምህርት ቤት የቀድሞው ማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር ያስገነቡት መሆኑ ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው ይህ አዲስ የትምህርት ተቋም፣ በሀገሪቱ ካሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በተለየ መልኩ እጅግ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑ ተመልክቷል።
ትምህርት ቤቱ የውስጥና የውጪ ውበቱን የጠበቀ ከመሆኑም በላይ፣ ለአስተማሪዎች መኖሪያ ቤት፣ ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት (Smart Libraries)፣ የላቦራቶሪ ክፍሎች፣ እንዲሁም የእግር ኳስና የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ያካተተ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትምህርት ክፍሎቹ ውስጥ የኤልኢዲ (LED) ስክሪኖች የተገጠሙላቸው ሲሆን፣ ይህም በርቀት (Virtually) ጭምር ለማስተማር የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የአንድ ክፍል የተማሪዎች ቁጥርም የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ ሲባል ከ40 በታች እንዲሆን ተደርጎ የተዋቀረ ነው።
Fast Mereja
05/28/2026
በምርጫው ቀን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ዝግ ይሆናሉ።
የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም ከሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የትምህርት ተቋማት ዝግ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
ሰራተኞች ድምጽ እንዲሰጡ ለመተባበር የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና የግል ተቋማትም በዕለቱ ተዘግተው ይውላሉ ፤ ሥራም አይኖርም።
ነገር ግን፦
- ሆስፒታሎች
- ሆቴሎች
- ሬስቶራንቶች
- የትራንስፓርት አገልግሎት ሰጪዎች በዝግ ቀናት ላይ የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ያከናውናሉ።
የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
05/26/2026
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸም ረቂቅ ደንብን አጸደቀ።
በዚህም ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ፣ አስፈላጊ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።
ደንቡ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመንግስት የበጀት ድጋፍ በታወቀ የጥቅል በጀት ስርዓት ላይ በመመስረት፣ የፋይናንስ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን እና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ወጪ በራሳቸው የመሸፈን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያሳድጉ ያግዛል።
በተጨማሪም፣ በተቋማቱ መካከል ተመጣጣኝ የመማርና ማስተማር ጥራት፣ የአገልግሎት ፍትሃዊነት እና ኃላፊነት የተሞላበት አሰራር እንዲጠናከር ያስችላል።
05/26/2026
👉 6 haytô kee 8 haytô footimak Rakaakay caddoh aqayyaarek aqayyaareh uddurih maysaxxaga.
👉 የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ማስታወቂያ።
05/17/2026
በአፋር ክልል በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በዘንድሮው ዓመት 105 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ
በአፋር ክልል በትምህርት ቤቶች የሚታዩ የመሰረተ ልማት እና የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት በተጀመረው የ'ትምህርት ለትውልድ' ንቅናቄ በዘንድሮው ዓመት ብቻ 105 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ሙሳ አደም (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በትምህርት ቤቶች የሚታዩ የመሰረተ ልማት እና የግብዓት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመረው የ'ትምህርት ለትውልድ' ንቅናቄ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ነው።
ንቅናቄው ወላጆች የልጆቻቸው ትምህርት ቤት የራሳቸው ጉዳይ እንደሆነ አምነው በባለቤትነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱ ማድረጉንና ተማሪዎች ከዛፍ ስር ትምህርት ተላቀው ውጤት እንዲያስመዘግቡ እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በንቅናቄው በዘንድሮው ዓመት ብቻ 105 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸው፤ በተሰበሰበው ገቢም የትምህርት ቤት ግንባታ እና በርካታ ቁጥር ላላቸው ትምህርት ቤቶች እድሳት እንደተደረገ አስታውቀዋል።
በዚህም ተማሪዎች ዛፍ ስር ከመማር እንዲላቀቁ እንዲሁም ጣሪያው ከሚያፈስና ፀሐይ ከሚያስገባ የመማሪያ ክፍሎች ወጥተው ምቹ በሆኑ የመማሪያ ክፍሎች እንዲማሩ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡
ከእድሳት ባለፈም አዳዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ለማከናወንና መምህራን ለማስተማሪያ የሚጠቀሙባቸው መሰረታዊ ግብዓቶች እንዲሟሉላቸው ለማድረግ ንቅናቄው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
ጋዜጣ ፕላስ
#ጋዜጣፕላስ #ትምህርትለትውልድ #አፋር #ኢትዮጵያ
05/16/2026
የትምህርት ምዘናና ምርምር ለትምህርት ጥራት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በላቀ ደረጃ እንዲያበረክት እየሠራ መሆኑን አገልግሎቱ ያስታወቀ ሲሆን ባለድርሻ አካላትንም አመስግኗል።
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከሚያዚያ 26 - ግንቦት 07/2018 ዓ.ም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ በ359 ትምህርት ቤቶች ስካሄድ የነበረዉ የመሠረታዊ የንባብና የስሌት (EGRA እና EGMA) ጥናትና ምርምር መረጃ በተሳካ ሁኔታ ተሰብስቦ ተጠናቋል።
ስለሆነም መረጃው በጥራት እና በታቀደው የጊዜ ገደብ ተሰብስቦ እንዲጠናቀቅ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ክቡራን የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን፣ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን፣ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎችን እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሰ-መምህራንንና መምህራንን ከልብ እናመሰግናለን።
የጥናት ውጤቱ መረጃው ተተንትኖ፣ ሪፖርት ተዘጋጅቶ፣ ግኝቶቹና ምክረ ሐሳቦቹም ተለይተው ሲቀርቡ በባለድርሻ አካላት ከተተቸ በኃላ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በይፋ የሚቀርብ ይሆናል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
05/15/2026
📄 የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ
📌ይህ ሰነድ የማረጋገጫ ሂደቱ ስልታዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚረዱ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል።
📋 ክፍል 1፡ የግድ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (11 ዓይነቶች)
ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ የሰው ኃይል መረጃዎች፦
📌ብሄራዊ መታወቂያ፡ ከተመዘገበበት ስልክ ቁጥር ጋር።
📌የቢሮ መታወቂያ፡ ወቅታዊ የሆነ።
📌የቅጥር ደብዳቤ፡ የመጀመሪያ ቅጥር ሰነድ።
📌የዝውውር ሰነድ፡ ከሌላ መሥሪያ ቤት የመጡ ከሆነ።
📌የደረጃ እድገት፡ የተሰጡ የደረጃ እድገት ደብዳቤዎች።
📌የአገልግሎት ማራዘሚያ፡ ጡረታ ወጥተው ለሚሰሩ ብቻ።
📌የትምህርት ማስረጃዎች፡ ሁሉም የትምህርት ደረጃዎች።
📌የጡረታ ፎርም፡ የተሞላ የጡረታ መረጃ።
📌የስራ ልምድ፡ የቀድሞ የስራ ልምድ ማስረጃዎች።
📌የሹመት ደብዳቤ፡ ተሿሚ ለሆኑ አመራሮች።
📌የድልድል/ምደባ ደብዳቤ፡ አዲስ ድልድል ተደርጎ ከሆነ።
💍 ክፍል 2፡ ተጨማሪ የማህበራዊ ሁኔታ ሰነዶች
📌የጋብቻ ሰርተፍኬት
📌የልጆች የልደት ሰርተፍኬት (ልጆች ካሉ)
⚙️ ክፍል 3፡ የአሰራር ቅደም ተከተልና መመሪያዎች
✍ሂደቱ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሄድ ተቋማት የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይኖርባቸዋል፦
📌መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፡ በቀን ለአንድ መረጃ ሰብሳቢ 7 ሰራተኞችን በማደራጀት ቀኑን አስቀድሞ ማሳወቅ።
📌የአካል መገኘት፡ በወሊድ፣ በህመም ወይም በአመት እረፍት ላይ ያሉ ሰራተኞች በአካል ቀርበው መመዝገብ አለባቸው።
📌የሰው ኃይል መመደብ፡ ስራውን የሚከታተል፣ ጥንቃቄ ያለውና የIT እውቀት ያለው ባለሞያ መመደብ።
📌 መረጃዎችን - በጊዜ፣ በጥራትና በማደራጀት የዲጅታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ለማሳካት የድርሻቸውን እንወጣ። መልዕክታችን ነው።