Mortena Jeru Werda Communication

Call Directions

Mortena Jeru Werda Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mortena Jeru Werda Communication, Government Organization, Moretena Jeru, north Shewa, Martinez, CA.

A leading role in the Queen's Communication Information Sector: Integrating our vision for the success of our mission by raising public awareness of basic police strategies and programs by raising public awareness of basic police strategies and programs

10/24/2026
10/24/2026
የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/ቤት የወረዳው የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ በጀት 637 ሚሊየን 129 ሺህ 912 ብር በማፅደቅ ተጠናቀቀ።እነዋሪ፤ጥቅምት 14/2019ዓ.ም (ሞጅወመኮ)==============...
10/24/2026

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/ቤት የወረዳው የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ በጀት 637 ሚሊየን 129 ሺህ 912 ብር በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

እነዋሪ፤ጥቅምት 14/2019ዓ.ም (ሞጅወመኮ)
===============
በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 14ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የወረዳው የ2019 ዓ.ም የ2019 በጀት ዓመት የሴክተሮች እቅድ፣ የአንደኛ ሩብ ዓመት የሴክተሮች አፈጻጸም ግምገማና በበጀት ዓመቱ ለስራ የሚውል ከ637 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄድ የነበረው ጉባኤ ተጠናቋል።

የ2019 በጀት ዓመት የሴክተሮች እቅድ፣ የአንደኛ ሩብ ዓመት የሴክተሮች አፈጻጸም ግምገማን በፕላንና ልማት ጽ/ቤት የፕላንና ልማት ቡድን በአቶ መክብብ ጌታነህ ቀርቦ ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል።

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ዲና የበጀት ረቂቁ ለምክር ቤቱ አባላት በማቅረብ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የወረዳው ምክር ቤት ለ2019 በጀት አመት 637 ሚሊዮን 129 ሺህ 912ብር በመሆን አጽድቋል።

ኃላፊው እንዳሉት ከበጀቱ ለመደበኛ ከውስጥ ገቢ ማለትም ለማዘጋጃ ቤቶች፣ለጤና እና ለት/ት ተቋማት ሰብስበው የሚጠቀሙት መሆኑን ለም/ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ኃላፊው አክለው ከመደበኛ ከተመደበው 637 ሚሊየን 129ሺህ 912 ብር ውስጥ 553 ሚሊየን 173 ሺህ 815 ብር ለደመወዝ ሲሆን የበጀቱ 86.9% መሆኑና ቀሪው በጀት ለወረዳው ለካፒታል እና ለስራ ማስኬጃ ስራዎች እንደሚውል አቶ ተመስገን ለም/ቤቱ አመላክተው የተመደበው ውስን በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ከመጠቀም ባለፈ የውስጥ ገቢ በተገቢው መሰብሰብ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከም/ቤቱ አባላትና ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ብዙሐን አሰፋ ባለፉት ሶስት ወራት እንደ ወረዳ አበረታች የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና መሠል ስራዎች እንደተሰሩ ለም/ቤቱ ሰፊ የግንዛቤ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም እንደ ሀገር የመጀመሪያና የሆነውና የወረዳችን አርሶ አደሮች የልፋት ውጤት የሆነው የጅሩ አግሪ ቢዝነስ ካምፓኒ ሁሉም የወረዳው ማህበረሰብ የካምፓኒውን አላማ በመረዳት፣ በማሳወቅ እና የድርጅቱ አባል መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቀጣይ ወረዳውን በማልማት ረገድ ያሉን ማዘጋጃ ቤቶች በራሳችን አቅም ማልማት እንዳለብን በመጥቀስ በተለይ ኢንቨስትመንት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የግብርና ስራችን፣የሰላም ጉዳይ እና አንዳንድ የወረዳችን ቀበሌዎች የመንገድና መሠረተ ልማት ተጠቃሚ የማድረግ ጉዳይ በቀጣይ በልዩ ትኩረት የሚሰሩ መሆኑን አቶ ብዙሐን አመላክተዋል።

አስተዳዳሪው አክለው የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል አንዱ ት/ቤት ምገባ፣ገጽታን የማሻሻል እና የም/ቤቱ አባላት ለት/ት ስራ ውጤታማነት የበኩላቸው እገዛ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ በመስጠት እና የወረዳው ም/ቤት ጉባኤውን ተጠናቋል።

በመጨረሻም የምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ብርቱካን ዘነበ የማጠቃለያ ሀሳብ ለም/ቤቱ የሰጡ ሲሆን በተለይ በገቢ አሰባሰብ፣የመሠረተ ልማት ተደራሽነት፣የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በባለቤትነት መጠበቅ፣ገበያ ማጠናከር እና የቀበሌ ም/ቤቶች በማጠናከር ዙርያ በቀጣይ በትኩረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ‎‎እነዋሪ 13/2019 ዓ.ም (የሞጅወመኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የ20...
10/23/2026

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ
‎
‎እነዋሪ 13/2019 ዓ.ም (የሞጅወመኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል
‎
‎በግምገማው የአራቱም ጤና ጣቢያ ሀላፊዎች፣የእናቶች ተጠሪዎች፣የኤች ኢቲ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
‎
‎የሞረትና ድሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸዋቀና አጣለ እንደገለጹት በሁሉም ተግባራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና ማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ በትኩረት በመስራት በቀጣይ መሻሻል እንዳለበትና ሁሉም ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም የጤና አገልግሎት ሰጭ በየደረጃው ያላችሁ ባለሙያና ኃላፊዎች ከድክመቶቻችን በመማር በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረን በቅንጅትና በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
‎
‎የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ አየለ እንደገለፁት፣ በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት መመዝገብ መቻሉ እንደሚያበረታታ ጠቅሰው፣ ይህም ከባለፈው አመት ግምገማ የተነሳ ቁጭትና ትኩረት ውጤት መሆኑን ገልፀዋል። በተለያዩ ፈተናዎች መካከል ሆነው ማህበረሰቡን በማገልገላቸው የጤና ተቋማት ሊመሰገኑ እንደሚገባ ገልጸው፣ ጥሩ አፈጻጸም ላላቸው የጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ የእውቅናና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል።
‎
‎

10/23/2026
10/23/2026

Address

Moretena Jeru, North Shewa
Martinez, CA
251116880051

Telephone

+251116880051

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mortena Jeru Werda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share