Ethiopian Dialogue Forum - EDF

Ethiopian Dialogue Forum - EDF

Share

EDF was established by Ethiopians deeply concerned about the future of their historical ancestral land and the well-being of its diverse population.

In its capacity as a think-tank, EDF has carried out more than 24 conferences and published hundreds of

Photos from Ethiopian Dialogue Forum - EDF's post 09/17/2024

Ethiopian Dialogue form would like to express the sympathy to the families of Professor Beyene Petros.
Picture at the EDF forum in Washington DC.

FESP's 13th conference Part II 08/04/2024

FESP's 13th conference Part II የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ ፲፫ኛ ጉባኤForum for Ethiopian Scholars & Professionals 13th Conferenceጥልቅ ውይይትስለፖለቲካ ባህልና የሽግግር ፈተናዎችColloquium on Political Culture & ...

FESP's 13th conference 08/03/2024

FESP's 13th conference የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ ፲፫ኛ ጉባኤForum for Ethiopian Scholars & Professionals 13th Conferenceጥልቅ ውይይትስለፖለቲካ ባህልና የሽግግር ፈተናዎችColloquium on Political Culture & ...

08/12/2023
Photos from Ethiopian Dialogue Forum - EDF's post 02/27/2023
Photos from Ethiopian Dialogue Forum - EDF's post 02/27/2023

የቦረናንና የጉጂን ህዝብ እንታደግ

እኛ የኢትዮጵያ የውይይትና የመፍትሄ መድረክ አባላት በዚህ ወቅት ውድ ወገናችን የሆነው የቦረና ህዝብና የጉጂ ህዝብ በከፍተኛ ድርቅ በመመታቱ ረሃብ ላይ እንደወደቀ ስንረዳ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ዛሬም ድረስ ከዝናብ ጥገኝነት ባለመላቀቁ የዝናብ ስርጭት ሲዛባ ወይም ድርቅ ሲሆን ሁል ጊዜም ለችግር ሲጋለጥ ይኖራል፣ የሰው ህይወት ያልፋል፣ እንስሳትም ይሞታሉ። የአደጋ መከላከል ተቋማት አደጋዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲመጡና የድርቅ ምልክቶች ሲታዩ ፈጠን ብለው የመከላከልና የመመከት ስራ ስለማይሰሩ ችግሮች እየከፉ የብዙዎችን ህይወት ይቀጥፋሉ። ይህ ችግር የሚያሳየው መንግስት ሁል ጊዜም ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱን ነው።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ዝናብ ጠፍቶ ስለነበር ይህ አካባቢ ለከፋ ችግር እንደሚጋለጥ የታወቀ ነበር። ይሁን እንጂ ሁኔታዎች ሳይባባሱ ችግሮችን በየደረጃው መቅረፍ እየተቻለ መንግስት ቸልተኛ በመሆኑ አሁን ላይ ችግሮች በጣም ከፍተዋል። በተለይ የቦረናና የጉጂ ህዝብ ኑሮው ሁሉ በእጅጉ ከከብት እርባታ ጋር የተቆራኘ ሲሆን ድርቅ ሲመጣ ከብቶቹን ያጣል በዚህም ወዲያው ለረሃብ ይጋለጣል። ዛሬ ቦረና ውስጥ ወደ ሶስት ሚሊየን እንስሳ አልቋል ተብሏል። ይህ የሚያሳየው ችግሩ እጅግ ጥልቅና ግዙፍ መሆኑን ነው። ስለሆነም በዚህ አካባቢ ያለውን የህዝቡንና የእንስሳቱን ህይወት ለመታደግ የሃገር ውስጥ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና አለማቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች እርዳታችሁን እንድታደርጉ በትህትና እንጠይቃለን። መላው የድርጅታችን አባላትና መላው ህዝባችን ይህንን ክፉ ጊዜ በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንድናልፈውም እንመክራለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከዚህ ችግር እንዲታደጋት እንለምናለን

Photos from Ethiopian Dialogue Forum - EDF's post 02/03/2023

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሄ መድረክ (EDF) እና እምቢልታ ድርጅት በጋራ ያወጡት መግለጫ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን ፖለቲካዊ ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን!

ቀን ጥር 24፣2015 ዓመተ ምህረት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፊደል ቀርጻ ያስተማረች፣ ዜጎች በበጎ ሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ብዙ የደከመች፣ የሃገር ልዕልና ሲነካ በግንባር ቀድማ ብዙ ዋጋ የከፈለች፣ በሃገረ መንግስት ግንባታው ላይ ደማቅ አሻራዋን የተወች፣ የኢትዮጵያ ባለውለታ የሃይማኖት ተቋም ከመሆኗም በላይ ዛሬ የሚሊዮኖች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መሰባሰቢያ ጥላ ናት።

ይህቺ ቤተክርስቲያን በተለይ በዚህ ክፉ ወቅት የሃገራችን ህዝብ ሳይከፋፈል አንድነቱንና ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ጠብቆ የእርስበርስ መከባበርን ባህል አድርጎ እንዲኖር በየ እለቱ ደፋ ቀና የምትል ተቋም ናት። በዚህ ክፉ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ የሚኖረው ከመንግስትና ከፖለቲካው አካባቢ ባለው ግፊት ሳይሆን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት መቻቻልን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን ከፍ አድርገው በማስተማራቸው ነው።

ይህቺ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያውያን የደስታ ጊዜም ሆነ የመከራ ጊዜ በሃገራችን ሕዝብ ዘንድ የማይዘነጋ በጎ ተግባር ከመፈጸሟም በላይ ከፍ ሲል እንደተገለጸው ሃገር በውጭ ወራሪ ሃይሎች ስትደፈር ሀገርህንና ነጻነትህን እንዲሁም ማንነትህን ጠብቅ፣ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳህ እያለች ስትቀሰቅስና ስታጀግን፣ በጾም በጸሎት አምላኳን ስትማጸን የቆየች ናት። በዚህም ምክንያት ትውልድ ሁሉ የማይረሳውን ውለታ የጣለች ቤተክርስቲያን ናት። የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ አስር ጊዜ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም እንዲነሳ የሚያደርገው በታሪካችን ውስጥ የዚህች ቤተክርስቲያን አስተዋጽዖ አያሌ በመሆኑ ነው። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናኖቿን ሁሉ በሰላም ጊዜ ልማት ላይ አንዲያተኩሩ፣ በወረራ ጊዜ ወታደር እንዲሆኑ፣ ዘወትር ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁ እየመከረች ልጆቿን ሁሉ አራሽ፣ቀዳሽ፣ተኳሽ እያደረገች ያሳደገች ግሩም
እናት ናት እኮ ናት። የዛሬው ትውልድ ኢትዮጵያ ሃገሬ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛ ሃገር ናት፣ የጀግና ህዝብ ልጅ ነኝ እንዲል፣ መላው አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ብርሃን እንዲያዩ በተሰራው ታሪክ ውስጥ ደማቁ ታሪክ የተጻፈው በዚህች ቤተክርስቲያን ቀጥተኛ ተሳትፎ ነው።

ይሁን እንጂ ታዲያ በተለይ ባለፉት ሀምሳ አመታት ግድም በቅድሚያ በኢህአዴግ ሲቀጥል ደግሞ በኦህዴድ ብልጽግና መራሹ መንግስት አማካኝነት በሃገራችን ውስጥ በዘር በቋንቋ የከፋፈለ አደገኛ አገዛዝ ተዘርግቶ ሃገራችን በዚህ የከፋ አሳት ላይ ተጥዳ ባለችበት ወቅት እንደ ሃገር እንደ መልህቅ ሆኖ በዚህ ማእበል መሃል ያቆመን የሃይማኖት ተቋማት እሴቶቻችን በመሆናቸው የሃይማኖት ተቋማት ችግር ውስጥ ሲገቡ የሃገራችን መሰረት በከፍተኛ ሁኔታ መናጋቱ አይቀሬ ጉዳይ ነው።

እርግጥ ነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ የሃይማኖት ተቋም በታሪካችን የገጠሟት አያሌ ፈተናዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ የገጠሟትን ፈተናዎች ሁሉ እየበጣጠሰች ተሻግራ እዚህ ደርሳለች ፡፡ በአንድ በኩል የሃገርን ልዕልና ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም የነጻነት አርበኛ ሆና እንደኖረችው ሁሉ ሃይማኖቷን እና ትውፊቶቿን ሁሉ ከጥፋት የታደገች ቤተክርስቲያን ናት።

የሚያሳዝነው ነገር በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነሳው ክፉ ፍላጻ ዛሬም መልኩን ቀይሮ ይታያል። ምን አልባትም ይህቺ እናት ቤተ ክርስቲያን በዘመናት መካከል ከገጠሟት ፈተናዎች ሁሉ በላይ ዛሬ የከፋ አደጋ ገጥሟታል ብለን እናምናለን። በእኛ እምነት በመላው ሕዝባችን ትግልና በራሧ በቤተክርስቲያኒቱ አባላት ጠንካራ ትግልና ትምክህቷ በሆነው አምላኳ እርዳታ ይህንን ፈተና ትወጣለች ብለን እናምናለን። ይህንን ካልን በኋላ ግን የኢትዮጵያ መንግስት
ይህቺን ህጋዊት ቤተክርስቲያን ሊበጠብጥ ብሎም የሀገራችንን ሰላም ሊያውክ የተነሳን ኃይል ሃይ ማለትና ጸጥታ ማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ አለበት።

ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት መከተል መብቱ የተጠበቀ ነው። ይሁን እንጂ ሲኖዶስ ያወጣው ትእዛዝ በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ ስለሚሰራ ለዚህ አልታዘዝ ያለ ሰው የቤተክርስቲያኒቱን ሃብትም ሆነ የሃይማኖት ቦታዎች መጠቀም አይችልም። ምክንያቱም ስርዐተ ቤተክርስቲያንና ቀኖናው መከበር አለበትና። ነገር ግን ከሰሞኑ የታዘብነው ነገር ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት ለመቀራመት የሚደረገው መሯሯጥና በተለይም
የሃይማኖት አባቶችን ማዋከብና ማሰር ማንገላታት በቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በሃገሪቱ ሰላም ላይ የተቃጣ ህገ ወጥ የሆነ ድፍረት በጥብቅ እናወግዛለን።

በሌላ በኩል የቤተክርስቲያኒቱ አባላትና መሪዎች ችግሩን በሰከነ መንፈስ እያዩ ለመብታቸው በጥበብና በማስተዋል ታግለው ይህቺን የሃገር ባለውለታ ቤተክርስቲያን ከመከፋፈልና ከጥቃት እንዲታደጉ ጥሪ እናደርጋለን። ማናቸውም የሃይማኖት ተቋማትም ቢሆኑ ከሃይማኖታዊ ዶክትሪኖቻቸው ባሻገር እዚህች ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን በደልና የገጠማትን ሲስተሚክ ፖለቲካዊ ጥቃት እንዲያወግዙ ጥሪ እናደርጋለን።

በመጨረሻም ሃገራቸን ውስጥ አንድ ጊዜ በብሔር፣ አንድ ጊዜ በነገድ፣ ሌላ ጊዜ በሃይማኖት፣ የሃገራችንን ህዝብ እያመሰ ያለው ከፋፋይ የሆነው የፖለቲካ አሰላለፍና ህገ መንግስት ለውጥና ለተሻለ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ኢትዮጵያውያን ሁሉ አምርራችሁ እንድትታገሉ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያውያን ጌጣችን የሆነውን ህብረ ብሄራዊ ገጻችንን እየተንከባከብን የአብሮነት ባህላችን እንዳይሸረሸርና ጨርሶ እንዳይጠፋ ነቅተን መጠበቅ ይኖርብናል። በሌላ በኩል ሀይማኖትን የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ መንግስት የሚጫወተውን እኩይ ሥራ በጥብቅ እያወገዝን ህበረተሰቡ የእምነት ቤቶቹንና ሃይማኖታዊ እሴቶቹን ነቅቶ እንዲጠብቅ ጥሪ እናደርጋለን።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለካቢኒያቸው የሰጡትን ማብራሪያ በጽሞና አዳምጠናል። በዚህ ንግግራቸው ላይ እንደወትሮው ሀገር አፍራሽና ነፃ ኀልውናን የሚፈታተኑ ቃላቶችን በመጠቀማቸው እጅግ አዝነናል። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እጅግ አሳንሰው ለዚህች ግዙፍ ቤተክርስቲያን ብጣቂ መሬት ሰጥተናታል እያሉ ሲመጻደቁ ማየት ብዙዎችን አስቆጥቷል። በመሰረቱ ኢትዮጵያ ሃገራችን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያገኘችው በረከት በእጅጉ
ይልቃልና። ይህቺ ቤተክርስቲያን በልማት በኩል ያላት አስተዋጽዖ፣ በቱሪዝም የምታስገባው ገቢ እንደምን ሊዘነጋ ይችላል?። ያለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባዶ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዓላዊነትና እድገት ያደረገችው አስተዋጾ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአደባባይ ካዱት እንጂ እጅግ እጅግ የላቀ ነው። ተሰጠ የሚባለው ቁራጭ መሬት ቀድሞውንም የቤተክርስቲያን የነበረ
ይዞታ እንጂ የዚህ መንግስት መመጻደቂያ ችሮታ አይደለም። እንዲያውም ቤተክርስቲያኒቱ ገና ያልተከበረላት ይዞታ እንዳለ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
በሌላ በኩል እኚህ ሰው በሃገራችን ውስጥ የፖለቲካ ለውጥ እንዳይታሰብ በከፍተኛ ሁኔታ የሾሟቸውን ሚንስትሮች ሲያስፈራሩ፣ ሕዝብን ሊያሸማቅቁ ሲሞክሩ ተስተውለዋል። ምን አልባት የሾሟቸው ሚንስትሮች ለመብታቸው የማይታገሉ ከሆነ እነሱን ያስፈራሩ እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመብት ጥያቄ ለማፈን የሚያደርጉት ማስፈራራት የሃላፊነት ጎደሎነትንና የትዕቢትን ጥግ ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተቃጣብህ
አንድነትህን፣ሰላምህን፣ ሃይማኖትህን ከሚያናጋ ሴራ ነቅተህ እንድትከላከል ከወዲሁ እናሳስባለን።
በመጨረሻም በሃገራችን ውስጥ በየጊዜው በምንሰማው እልቂትና መፈናቀል እጅግ ለተጎዱት ወገኖቻችን ሁሉ ቶሎ ማገገምን የሞቱትን ደግሞ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እንመኛለን።

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያ፤የውዪዪትና፤መፍትሔ፤መድረክ
Ethiopian Dialogue Forum
9900 Greenbelt RD. E #343 - Lanham, MD 20706

Dr. Abdissa Zerai - ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአመለካከት ለዉጥ (Paradigm Shift)፣ ለእድገትና፣ ለብሔራዊ መግባባት። 04/01/2022

https://youtu.be/A9uDkirZGK4

Dr. Abdissa Zerai - ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአመለካከት ለዉጥ (Paradigm Shift)፣ ለእድገትና፣ ለብሔራዊ መግባባት። የውይይቱ ዋና ማጠንጠኛ ሃሳብ እስካሁን የሄድንባቸው መንገዶች የሃገርንና የህዝብን ህልውና አደጋ ላይ እየጣሉ ስለሆነ መሰረታዊ የሆነ የአስተሳሰብና የአሰራር ልውጠት ካልተካሄደ በስ....

Want your business to be the top-listed Government Service in Washington D.C.?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Washington D.C., DC